Textile, Garments and Uniforms
የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት የደንብ ልብሶችን፤ የጽህፈት መሳሪያዎችን፤ የጽዳት ዕቃዎችን፤ የመኪና ጎማዎችን፤ ቋሚ የቢሮ ፈርኒቸሮችን እና ልዩ ልዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዢ ከአገር ውስጥ ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Textile, Garments and UniformsTextile, Garment and LeatherShoes and Other Leather Products
Oromia
More tags
StationeryOffice Supplies and ServicesCleaning and Janitorial Equipment and ServiceSpare Parts and Car Decoration MaterialsOffice FurnitureFurniture and FurnishingHouse FurnitureEquipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsComputer and AccessoriesIT and TelecomOffice Machines and AccessoriesAmharic2merkatoSouth West Shewa Zone FEDB
Description
የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2019
የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ለዞኑ መንግስታዊ መ/ቤቶች የ2019 በጀት ዓመት አንደኛ ዙር
- የደንብ ልብሶችን፤
- የጽህፈት መሳሪያዎችን፤
- የጽዳት ዕቃዎችን፤
- የመኪና ጎማዎችን፤
- ቋሚ የቢሮ ፈርኒቸሮችን እና ልዩ ልዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዢ
ከአገር ውስጥ ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ በጨረታው የተዘረዘሩትን መመሪያዎች አሟልተው መገኘት ይኖርባቸዋል፡፡ ለመሣተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መሣሪያዎች አሟልተው መገኘት ይኖርባቸዋል፡፡
- በንግድ ሥራ ዘርፍ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ፤ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የመንግስት ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት ወቅታዊ የሆነ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- በመንግስት ዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተካተቱና የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት አንድ/ደንብ ልብስ/ብር 60,000.00 (ስልሣ ሺህ ብር) ለሎት ሁለት /የጽህፈት መሳሪያዎች/ 80,000.00(ሰማንያ ሺህ ብር)፤ ለሎት ሦስት /የጽዳት ዕቃዎች/ 60,000.00 (ስልሣ ሺህ ብር) ፤ ለሎት አራት / ቋሚ የቢሮ ፈርኒቸሮችን/ 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ፤ለሎት አምስት የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን 150,000.00 (መቶ ሃምሣ ሺህ ብር) ፤ ለሎት ስድስት የመኪና ጎማዎች 120,000.00 (መቶ ሃያ ሺህ ብር) ፤ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ስም አሰርተው ሕጋዊ ከሆነ ባንክ የተረጋገጠ CPO ከሚያቀርቧቸው ሰነድ ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር በየዕቃው ምድብ ዓይነት (ሎት) የማይመለስ ብር 300(ሶስት መቶ) በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ5 ተከታታይ የስራ ቀናት በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ወሊሶ ከተማ የቢሮ ቁጥር 16 እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀረቡትን የጨረታ ሰነድ አንድ ኦርጂናል እና አንድ ኮፒ እስፔስፍኬሽኑ (specification) ሳይቀየር ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በተራ ቁጥር 5 በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ እስከ ነሓሴ 29/12/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ነሓሴ 29/12/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተራቁጥር 6 በተገለጻ ቦታ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ ከሚያስቸግሩ ዕቃዎች ውጪ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊው ባሸነፈባቸው ጠቅላላ እቃዎች ላይ 10% |አሥር በመቶ የውል ማስከበሪያ በሕጋዊ ባንክ የተረጋገጠ ማሸነፉ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት CPO በማስያዝ በመገኘት ውል መፈረም ይኖርበታል፡፡
- ከላይ በተራ ቁጥር 9 ላይ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ውል የማይፈፅም አሸናፊ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ የሚደረግ ሆኖ ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ መጠቀም ይችላል፡፡
- አሸናፊው ውል ፈርሞ በውል ስምምነቱ መሰረት ከላይ በተገለፀው አድራሻ በራሱ መጓጓዣ እቃዎቹን አቅርቦ ማስረከብ እና ገጠሚ የሚያስፈልጋቸውን ዕቃዎች ማስገጠም ይኖርበታል፡፡
- በጨረታው ውል መሠረት እቃዎቹን በሙሉ ካስረከበ ክፍያው ወዲያው ይፈፀማል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ 0113664634
የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-04
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-09-04 14:30
- Region: Oromia
- Publishing entity: South West Shewa Zone FEDB
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 300.00 ብር በየዕቃው ምድብ ዓይነት (ሎት)
- Published on: Addis Zemen (Aug 16, 2026)
- Posted at: 2026-08-17T14:25:49.000Z