Vehicle and Machinery Sale
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በፌደራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 41 ንኡስ አንቀጽ 9 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የሚፈለግባቸውን የታክስ ዕዳ በሕግ በተቀመጠው የመክፈያ ጊዜ ባለመክፈላቸው ምክንያት በአንደኛ ዙር የግልፅ ጨረታ በማውጣት መሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች በሰንጠረዥ በቀረበው ዝርዝር መረጃ መሰረት ንብረትነታቸው፡
|
የተሽከርካሪመለያ ኮድ |
የግብር/ታክስ ባለዕዳው ስም |
የተሽከርካሪው ዓይነት |
የሰሌዳ ቁጥር
|
የሞተር ቁጥር
|
የሻንሲ ቁጥር
|
የተሽከርካሪ የጨረታ መነሻ ዋጋ |
የተ.እ.ታ ጨምሮ በተጫራቹ የቀረበ የተሽከርካሪ የጨረታ ዋጋ |
||
|
በተጫራች የቀረበ የአን ዱን ዋጋ በአሀዝ |
በተጫራች የቀረበ የአንዱን ዋጋ በፊደል |
ምርመራ |
|||||||
|
ኮድ 001 |
አቶ ዮሐንስ ገረመው ገሰሰ |
አውቶሞቢል(ሀይብሪድ ሬንጅሎቨር) |
አ.አ. 02-C32444
|
CJLR-211223C0200PT153 |
SALZA2BTXPH197397 |
7849752.8
|
|
|
ለ5ኛ ጊዜ ጨረታ የቀረበ |
|
ኮድ 002 |
አቶ አያሌው ሀይሌ ተ/ አረጋይ |
አውቶሞቢል(ሊፋን)
|
አ.አ-02-A18366 |
LFB479Q* 12050 |
LCN64ED50C0011618 |
617,451.53
|
|
|
ለ4ኛ ጊዜ ጨረታ የቀረበ |
|
ኮድ 003 |
አቶ ሰናይ ተድላ ጋሻው በዛ |
አውቶሞቢል(የስፖርት) |
አ.አ-02-24278
|
Unreadable
|
AE86-0063461
|
28,981.52
|
|
|
ለ4ኛ ጊዜ ጨረታ የቀረበ
|
|
ኮድ 004 |
አቶ ሰላሙ ሀብተ ኢየሱስ ገብሬ |
አውቶሞቢል(RENAULT) |
አ.አ-02-C24343
|
F33824D4FB712 |
VF1KCUWEF26132622
|
582,615.97
|
|
|
ለ3ኛ ጊዜ ጨረታ የቀረበ
|
|
ኮድ 005 |
አቶ ሙሴ ማርዲንግ አዝናቮሪዮ |
አውቶሞቢል (ማርቸዲስ)
|
አ.አ-02-57064 |
10499212042941
|
WDBEA92E2RF279587 |
1,489,442.27
|
|
|
ለ1ኛ ጊዜ ጨረታ የቀረበ
|
|
ኮድ 006 |
ቴዎድሮስ ዘውዴ ማሞ |
አውቶሞቢል /ያሪስ/
|
አአ-2-A71463 |
1KR-0486997 |
KSP90-5103008 |
581,147.79
|
|
|
ለ1ኛ ጊዜ ጨረታ የቀረበ |
|
ኮድ 007 |
ታለግን መሃመድ ያሲን |
አውቶሞቢል /ኮሮላ/
|
አአ-2-A12333 |
2NZ-4615563 |
JTDBW22E73149600 |
946,123.40 |
|
|
ለ1ኛ ጊዜ ጨረታ የቀረበ |
|
ኮድ 008 |
ዋሲሁን ከበደ አሊ |
አውቶሞቢል/ ቮልስ/ |
አአ-3-B67453 |
ADR-335902
|
WWWZZZ3BZWE182854 |
712,348.23
|
|
|
ለ1ኛ ጊዜ ጨረታ የቀረበ |
|
ኮድ 009 |
መቃሙ ኢልያስ አሊ |
ዲዛየር /የጭነት/ |
አአ-2-B09782 |
G13BB-679325
|
JSAFDA32V00120233
|
534,589.41
|
|
|
ለ1ኛ ጊዜ ጨረታ የቀረበ |
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ከላይ የተጠቀሱትን ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም ቢሮው ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች ሁሉ የጨረታ ሠነድ በመግዛት እንድትወዳደሩ ይጋብዛል፦
- ማንኛውም ድርጅት ወይም እድሜው ከ8 ዓመት በላይ የሆነ ሰው መወዳደር ይችላል። በተጨማሪም ማንነትን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ፣ ፋይዳ መታወቂያ፣ የታደሰ ፓስፖርት ወይም መንጃ ፍቃድ ማቅረብና እና ሌሎች ለዚሁ ጨረታ እንደ መስፈርት የተቀመጡትን መስፈርቶች ሁሉ መሟላት አለበት።
- ንብረቶቹን ለመጫረት የእያንዳንዱ እና ጠቅላላ የንብረቶቹ የጨረታ መነሻ ዋጋ ግምት በጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ እና በጨረታ ሠነዱ ላይ በአባሪ 01/አንድ/ተያይዞ በቀረበው ሠንጠረዥ ዝርዝር መረጃ መረዳት የሚቻል ሲሆን የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ 500 ብር(አምስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል አፍሪካ ሕብረት ፊት ለፊት ከአማጋ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ግዥና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት በመግዛት የንብረቶቹ መረጃ እና ስለንብረቶቹ ዝርዝር መመሪያዎች መመልከት ይችላሉ።
- ስለ ንብረቶቹ አሻሻጥና ዝርዝር መረጃ በተመለከተ በታክስ ዕዳ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ስር የሚገኘውን በታክስ ዕዳ የተያዙ ንብረቶች አስተዳደር እና ሽያጭ ቡድን አፍሪካ ሕብረት ፊት ለፊት አማጋ ህንፃ 3ኛ ፎቅ በአካል በመቅረብ መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች በግልጽ ጨረታው ለመሳተፍ በቅድሚያ የጨረታ ማስከበሪያ(ዋስትና) ለእያንዳንዱን የጨረታ መነሻ ግምት የተሠራላቸው ንብረቶች በጨረታ ሠነዱ ላይ እና በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያው በተመላከተው የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/10ኛውን በባንክ የተረጋገጠ ሲፒ.ኦ (CPO)“Addis Ababa city government Revenues Bureaue”ስም ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች ንብረቱን የሚገዙበት ዋጋ በግልጽ ሁኔታ በማስፈር በሰም በታሸገ ካኪ ፖስታ(በታሸገ ፖስታ አሽገው አድራሻ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ብሎ በመፃፍ ይህ የተሽከረካሪዎች የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን እስከ 16ኛው ቀን ወይም የመጨረሻው ቀን በበዓል ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን 2018ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ድረስ የሚቆይ ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛው ቀን ወይም የመጨረሻው ቀን በበዓል ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን 2018ዓም ከጠዋቱ 4፡30 ድረስ የጨረታ ዋጋቸውን 3ኛ ፎቅ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የግልጽ ጨረታ ሳጥን ማሰገባት አለባቸው።
- የተሽከርካሪዎች የግልጽ ጨረታው በ16ኛው ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ቀን ወይም የመጨረሻው ቀን በበዓል ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡45 ሰዓት 2018 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸውና ታዛቢዎች በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ወይም የመጨረሻው ቀን በበዓል ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡45 ሰዓት 2018ዓ.ም በቢሮው መሰብሰቢያ አዳራሽ 3ኛ ፎቅ ይከፈታል።
- የግልጽ ጨረታ አሸናፊው ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ሲ.ፒ.ኦ እና ሌላ ተጨማሪ የውል ማስከበሪያ ለንብረቱ በሰጡት ዋጋ ላይ የሚሰላ 10% እና ያሸነፋበትን ሙሉ ዋጋ ቢሮው በሚያሳውቀው የባንክ ሒሳብ ቁጥር ገቢ በማድረግ የባንክ ገቢ ደረሰኝ ለቡድኑ ዋናውን አሳይቶ ኮፒ ደረሰኝ በመስጠት እና የቢሮው የገቢ ደረሰኝ በማስቆረጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15/አስራ አምስት/ ቀናት ውስጥ አጠናቆ በመክፈል ንብረቱን መረከብ አለበት እንዲሁም ለጨረታ ተሸናፊዎች በአምስት ቀናት ውስጥ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
- የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 ቀናት ውስጥ አጠናቆ የማይከፍል ከሆነ ለጨረታው በዋስትና ያስያዘው ገንዘብ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ የጨረታው አሸናፊነቱን ይሰረዛል።
- ቢሮው ስለ ንብረቶቹ አሻሻጥ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉም የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር +251-011-557-6542/+251-011-557-3985
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ
በታክስ ዕዳ የተያዙ ንብረቶች አስተዳደር እና ሽያጭ ቡድን
Tender details
- Deadline: 2026-08-31
- Bid closing time: 10:30
- Bid closing (note): ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-31 10:45
- Bid opening (note): ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡45 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Addis Ababa City Administration Revenues Bureau
- Bid bond: 1/10ኛውን ለእያንዳንዱ
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 16, 2026)
- Posted at: 2026-08-17T14:59:53.000Z