Cleaning and Janitorial Equipment and Service
የሸዋ ሮቢት ተሃ/ልማት ማረ/ቤት ማዕከል የተለያዩ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001 /2019 ዓ.ም
የሸዋ ሮቢት ተሃ/ልማት ማረ/ቤት ማዕከል የተለያዩ አላቂ የጽዳት ዕቃዎች ለተለያዩ የሙያ ስልጠና አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን ለተለያዩ ቧንቧና ኤሌክትሪክ የጥገና ዕቃዎች እና የህግ ታራሚዎች ቀለብና የወጥ ማጣፈጫ ማለትም ከዚህ በታች የተመለከቱትን ፣
- ለሲቪል ሠራተኞች የተለያየ አልባሳትን ፤
- የተለያዩ የጽህፈት መሣሪያዎች፣
- የተለያዩ ህትመቶች፣
- ለሙያ ስልጠና አገልግሎት የሚውሉ ቁሣቁሶች ማለትም የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ፤ የብረታ ብረት ማሰልጠኛ ዕቃዎች፣ የህንፃ ግንባታ ማሰልጠኛ እቃዎች፣ የተለያዩ የሽመና ሙያ ማሰልጠኛ እቃዎች እና የተለያዩ የICT ሙያ ማስልጠኛ እቃዎች
- የህግ ታራሚዎች ቀለብና የወጥ ማጣፈጫ
- የተለያዩ አላቂ የጽዳት ዕቃዎች የከብቶች መኖ እና የማገዶ እንጨት
- አነስተኛ የእጅ ሥራ መርጃ መሣሪያዎች እና መፃህፎች
- የግብርና ግብዓት እና ፀረ-ተባይመድሀኒት
- የተለያዩ የቧንቧ እና የኤሌክትሪክ የጥገና ዕቃዎች
ስለዚህ ዕቃዎቹን በጥራት ለማቅረብ የሚያስችል
1. በዘርፉ የዘመኑ የታደሠ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ እና የምዝገባ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል፣
2. ከሚያቀርቡት ዕቃ ወይም አገልግሎት ጋር በሙያው ዘርፍ የተመዘገበ፣
3. ከገንዘብ ሚኒስቴር አቅራቢዎች የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
4. የግብይት መጠኑ ከ800,000.00 /ስምንት መቶ ሺህ ብር / በላይ ለሚሆኑ ግዥዎች ከገቢዎች ሚኒስቴር ተጨማሪ እሴት ታክስ ቲን ነምበር፣ ኦን ላይን ተመዝጋቢ ሲሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል እና ተገቢውን ግብር መክፈሉን ማረጋገጫ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል፡፡
5. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር / በመክፈል የጨረታ ሠነዱን ሸዋሮቢት ማዕከል ማረ/ቤት ግዥ ክንውን ቡድን ቢሮ መግዛት ይችላሉ።
6. ተጫራቹ የተሰጠውን የጨረታ ቅፅ በአግባቡ መሙላት አለበት።
7. ተጫራቾቹ ለእያንዳንዱ ለሚወዳደሩበት የጨረታ ሠነድ ማስያዝ የሚገባቸው የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ እንደሚከተለው መሆኑን ማወቅ ይኖርባቸዋል።
- ለሲቪል ሠራተኞች አልባሳት ግዥ ብር 15,000.00
- ለጽህፈት መሣሪያዎች ግዥ በ 5,000.00
- ለተለያየ ህትመቶች 2,000.00
- ለተለያየ የሙያ ስልጠና ዕቃዎች ግዥ ብር 20,000.00
- የህግ ታራሚዎች ቀስብና የወጥ ማጣፈጫ ብር 40,000.00
- የተለያዩ አላቂ የጽዳት ዕቃዎች የማገዶ እንጨት እና የከብቶች መኖ ግዥ ብር 52,000.00
- ለአነስተኛ የእጅ መርጃ መሣሪያዎች እና መፅሀፎች ግዥ ብር 11,000.00
- ለግብርና ግብዓት እና ፀረ-ተባይ ግዥ ብር 30,000.00
- የተለያዩ የቧንቧ የኤሌክትሪክ እና የህንፃ ጥገና ዕቃዎች ግዥ ብር 8,000.00
ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ በተመከረ ሠርቲፋይድ ሲፒኦ፣ ቢድ ቦንድ ለ90 ቀን ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
8. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች ናሙና ለተጠየቀባቸው ማቅረብ ይኖርባቸዋል። አስፈላጊ መረጃዎችን ሁሉ በማካተት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ የጨረታ ሠነዱን ዋናውንና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
9. ማንኛውም ተጫራች ናሙና ማስያዝ ያለበት ጨረታው ከመከፈቱ በፊት አንድ ቀን ቀደም ብሎ ሲሆን መስሪያቤቱ ያቀረበውን ናሙና በማንኛውም የስራ ቀናትና ሰዓት በመምጣት ማየት ይችላሉ።
10. የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት በ10 ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ እለት 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ በኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
11. የጨረታ አሸናፊ ሆነው የተመረጡት ድርጅቶች የጨረታ ውጤት ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማረሚያ ቤቱ ግዢ ክንውን ቡድን ቢሮ በመቅረብ ያሸነፉበትን ዋጋ 10% የመልካም የሥራ አፈፃፀም በማስያዝ ውል መፈፀም ይገባቸዋል
12. ማረ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::
13. ለጥቃቅን እና አነስተኛ ማህበራት የራሳቸው የሆነ የስራ ውጤቶች ባመረቱት ምርት ላይ 3% ልዩ አስተያየት ይደረጋል።
14. ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልገዎ ስልክ ቁጥሮች፡- 336 641 998፣ 033 664 0752 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ ስልክ፡- ቁጥር - 033 664 0753
ማሳሰቢያ፡- የዚህ ጨረታ ማስታወቂያ መክፈቻው ቀን የበዓል ቀን ቅዳሜና እሁድ ላይ ከዋለ የሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ተዘግቶ ይከፈታል፡፡
የሸዋ ሮቢት ተሃ/ልማት ማረ/ቤት ማዕከል
Tender details
- Deadline: 2026-08-26
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት በ10ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-26 12:00
- Bid opening (note): የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት በ10ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: Shewa Robit Rehabilitation Development Center
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ ሰነድ
- Published on: Addis Zemen (Aug 17, 2026)
- Posted at: 2026-08-18T07:27:29.000Z