Building Construction
የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት አንድ/1/ ሳይት ላይ B+G+7 ለመስራት ባቀደዉ መሰረት ለመገንባት ብቁ የሆኑትንና ፍላጎት ያላቸዉን ደረጃ አንድ ስራ ተቋራጮችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Building ConstructionConstruction and Water WorksFinishig Works
South Ethiopia Regional State
More tags
Description
የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ (NCB) ማስታወቂያ
የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በ2019 ዓ.ም ለመስራት ካቀዳቸዉ ፕሮጀክቶች መካከል ከዚህ በታች በተቀመጠው አንድ/ 1/ ሳይት ላይ የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት B+G+7 ለመስራት ባቀደዉ መሰረት ለመገንባት ብቁ የሆኑትንና ፍላጎት ያላቸዉን ደረጃ አንድ ስራ ተቋራጮችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ
|
የሳይት ስም
|
ፕሮጀክት ዓይነት
|
ደረጃ
|
የጨረታ ማስከበሪያ/ሲ.ፒ.ኦ/ (ብር) |
የግዥ መለያ ቁጥር |
|
1 |
የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት |
B+G+7
|
GC-1/BC-1
|
1,000,000 /አንድ ሚሊዮን ብር/ |
01/2018 ዓ.ም
|
- ጨረታዉ የሚከናወነዉ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ (NCB) ሂደት ሲሆን የኮንስትራክሽን ሴክተር የተመዘገቡ፡ በሚመለከተዉ አካል የተመዘገቡና ሕጋዊ ሰዉነት ያላቸዉ፣
- ሕጋዊ እና በ2018 ዓ.ም የታደሰ የግንባታ ስራ ፍቃድ ያላቸዉ፣
- ሕጋዊ እና በ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/Tin no/ ያላቸዉ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ(VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ
- በጨረታ ላይ እንዲሳተፉ ከገቢዎች ጽ/ቤት የድጋፍ ደብዳቤ/clearance/ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግዢ አቅራቢዎች ምዝገባ የተመዘገቡ (Registered in PPA Supplier list)
- ፍላጎት ያላቸዉና ብቁ የሆኑ ተጫራቾች 12/12/2018 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ ባሉ የስራ ቀናት በወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ግዥ ክፍያና ንብረት አስተዳደር የሥራ ክፍል በመገኘት ተጨማሪ መረጃ ማግኘት እና የጨረታ ሰነዶችን መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- በጨረታዉ የመሳተፍ ፍላጎት ያላቸዉ ተጫራቾች
- የፅሁፍ ማመልከቻ ማቅረብ አለባቸዉ
- ሕጋዊ እና በ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፍቃድ እና የታደሰ የግንባታ ስራ ፍቃድ በማቅረብ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/Tin no/ ያላቸዉ ከዋናዉ ጋር የተገናዘበ፣ በፊርማ የተረጋገጠ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- የተቆራጩ ተወካይ ህጋዊ ዉክልና በሚመለከተዉ አካል ተረጋግጦ ሕጋዊ ዉክልና የተሰጠ መሆን አለበት፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ ብር 2,000 (ሁለት ሺህ ብር) በመክፈል የጨረታ ስነድ ከታች በተገለፀዉ አድራሻ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚመሩበትና አጠቃላይ የዉል ሁኔታዎች የሚገለፁበት መመሪያ የሚሆነዉ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ለግንባታ ሥራዎች የሚዉል መደበኛ የጨረታ ስነድ (standard bid document) እና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በግዥ መመሪያ 70/2017 ሆኖ የሚሰሩበትን ዋጋ በመሙላት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒዎችን ለየብቻ በፖስታ በማሸግ አና የድርጅቱን የድርጅታቸውን/ ማኅተም በማሳረፍ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- በወላይታ ዞን አስተዳደር ውስጥ የተለያዩ ግንባታ ስራዎች ላይ ጨረታ አሸንፎ በመስራት ላይ የሚገኙ የግንባታ ማህበራት በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ የፕሮጀክት አፈጻጸም ሰባ አምስት ፐርሰንት (75%) እና ከዚያ በላይ መሆኑን የሚገልጽ የድጋፍ ደብዳቤ ከውል ስምምነት ሰነድና በመጨረሻ ጊዜ የወሰዱትን የክፍያ ምስክር ወረቀት ጋር አያይዞ ከአሰሪ መ/ቤት ማቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች ከጨረታ ማቅረቢያ ቀነ ገደብ 3/13/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ወይም ከዚያ በፊት ባሉ ቀናት ውስጥ የጨረታ ማስያዣ ዋስትና በባንክ ክፊያ ማዘዣ (CPO) ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በ3/13/2018 ዓ.ም ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 8:00 በወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ስብሰባ አደራሽ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ወላይታ ከፍተኛ ፍ/ቤት ለጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ከላይ የተጠቀሰዉ የአሰሪ ፍ/ቤት አድራሻ የሚከተለዉ ነዉ፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ፋይናንስ ክፍል፡፡
ስልክ ቁጥር፡- 0939834828 ወይም 046-551-21-00 ግዥ ክፊያና ንብረት አስ/ር ክፍል ቢሮ ቁ.18
የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-08
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-09-08 14:00
- Region: South Ethiopia Regional State
- Publishing entity: Welayeta Zone High Court
- Bid bond: 1,000,000 /አንድ ሚሊዮን ብር/
- Bid document price: 2,000 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 18, 2026)
- Posted at: 2026-08-18T08:33:54.000Z