Stationery
የእድገት በህብረት ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተለያዩ እቃዎች ለመግዛት ይፈልጋል
StationeryOffice Supplies and ServicesTextile, Garments and Uniforms
Addis Ababa
More tags
Textile, Garment and LeatherShoes and Other Leather ProductsCleaning and Janitorial Equipment and ServiceEquipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsComputer and AccessoriesIT and TelecomOffice Machines and AccessoriesHealth Related Services and MaterialsHealth Care, Medical IndustryMedical Equipment and SuppliesPrinted Advertising MaterialsAdvertising and PromotionPrinting and PublishingMaterialsEducation and TrainingOthersMaintenance and RepairMachineryVehicle (garage service)FurnitureHouse and BuildingOffice Machines and ComputersMechanicalHand Tools and Workshop EquipmentOffice FurnitureFurniture and FurnishingAmharic2merkatoEdget Behebret Kindergarten , Elementary & Medium Level School
Description
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የእድገት በህብረት ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለ2019 ዓ/ም በጀት አመት የተለያዩ እቃዎች ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት-1 አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎች
- ሎት-2 የደንብ ልብሶች
- ሎት-3 አላቂ የፅዳት እቃዎች
- ሎት4 ቋሚ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
- ሎት-5 የተለያዩ ቋሚ የቢሮ እቃዎች
- ሎት-6 የህከምና እቃዎች
- ሎት-7 የህትመት ስራዎች
- ሎት-8 ልዩ ልዩ የትምህርት መሳሪያዎች
- ሎት-9 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች
- ሎት-10 የተለያዩ ጥገናና እድሳት ስራዎች
ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑ ግብር አጠናቃችሁ የከፈላችሁ ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ፣ የቫት ከፋይነት ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ፡
- ጨረታ ማስከበሪያ ብር ለሎት1 2000.00 ፣ ለሎት2 2000.00 ፣ ለሎት3 2000.00 ፣ ለሎት4 2000.00 ፣ ለሎት5 2000.00 ፣ ለሎት6 2000.00 ፣ ለሎት7 2000.00 ፣ ሎት 8 2000.00 ሎት 9 2000.00 በባንክ በተረጋገጠ CPO ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የምትችሉ፡
- ለጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በእድገት በህብረት ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ክፍል በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የምትጫረቱበትን እቃ ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ ከአንድ ቀን በፊት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የምታቀርቡትን ዋጋ ዝርዝር በሰነዱ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በግልፅ ሞልታችሁ በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ድረስ በስራ ሰዓት ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን በእድገት በህብረት ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ክፍል ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ ማስታወቂያው ከወጣበት በ10ኛው ቀን 9፡30 ሰዓት ታሽጎ በማግስቱ 4:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮቻቸው በተገኙበት እድገት በህብረት ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤትፋይናንስ ክፍል ውስጥ ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡ 11ኛው ቀን የበዓል ወይም የዕረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ለገሀር የዱሮ ፀረ ሙስና ጀርባ /ባህር ትራንዚት አጠገብ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 አጠገብ
ስልክ 0115583658/ 0115584806
የእድገት በህብረት ቅድመ አንደኛ አንደኛና
መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-27
- Bid closing time: 15:30
- Bid closing (note): ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን 9፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-28 10:00
- Bid opening (note): ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን 9፡30 ሰዓት ታሽጎ በማግስቱ 4:00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Edget Behebret Kindergarten , Elementary & Medium Level School
- Bid bond: ለእያንዳንዱ ሎት (ከሎት 1-9) 2,000.00 ብር
- Bid document price: 100.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Published on: Addis Zemen (Aug 17, 2026)
- Posted at: 2026-08-18T09:29:51.000Z