Stationery

በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከከተማ የወረዳ 5 ጤና ጣቢያ የተለያዩ ደረጃቸውን የጠበቁ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከከተማ የወረዳ 5 ጤና ጣቢያ ለ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ ደረጃቸውን የጠበቁ ዕቃዎችን በ1ኛ ዙር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት1  የጽህፈት መሳሪያዎች
  • ሎት2 የደንብ ልብስ ግዢ
  • ሎት 3 አላቂ የጽዳት እቃ፤
  • ሎት-4- ልዩ ልዩ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችና ቋሚ ዕቃ (ጄኔሬተር )
  • ሎት 5 የህክምና መድኃኒቶችና፤ የላብራቶሪ ሪኤጅንቶች
  • ሎት 6- ልዩ ልዩ የጥገና ስራዎች ፤( የህንፃ ውስጥ ጥገና እና የማስፋፊያ ስራዎች )

በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች እና ግለሰቦችን በጨረታው እንዲወዳደሩ እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

ከላይ ከተራ ቁጥር 1-6 ለተጠቀሱት ግዥዎች አግባብነት ያለው ፤

  1. ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና በዘርፉ የተሰማሩ ፤
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ፤
  3. ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር አቅራቢዎች ዝርዝር ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
  4. የቫት/ ተመዝጋቢ መሆናቸው የሚገልጽ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፤
  5. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፤
  6. በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

 

  1. የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1- ብር // 5,000 // አምስት ሺህ / ብር ከህጋዊ ባንከ የተረጋገጠ (ሲፒኦ ብቻ) ማስያዝ ይኖርበታል።
  2. የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 2- ብር // 5,000 // አምስት ሺህ/ ብር ከህጋዊ ባንከ የተረጋገጠ (ሲፒኦ ብቻ) ማስያዝ ይኖርበታል።
  3. የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 3 ብር // 5,000// አምሰት ሺህ/ ብር ከህጋዊ ባንከ የተረጋገጠ (ሲፒኦ ብቻ) ማስያዝ ይኖርበታል።
  4. የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 4- ብር // 20,000 // ሃያ ሺህ/ ብር ከህጋዊ ባንከ የተረጋገጠ (ሲፒኦ ብቻ) ማስያዝ ይኖርበታል።
  5. የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 5 ብር // 10,000 // አስር ሺህ /ብር ከህጋዊ ባንከ የተረጋገጠ አድ (ሲፒኦ ብቻ) ማስያዝ ይኖርበታል።
  6. የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 6 ብር /20,000 // ሃያ ሺህ / ብር ከህጋዊ ባንከ የተረጋገጠ (ሲፒኦ ብቻ) ማስያዝ ይኖርበታል።
  7. ለሎት -5- ከመድሃኒትና ቁጥጥር ባለስልጣን የአቅራቢነት ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
  8. ለሎት 4- እና ቴክኒካል ሰነድ ፤ኦሪጅናል እና ኮፒ እና ፋይናንሺያል ሰነድ ኦሪጅናል እና ኮፒ ተለያይቶ መታሸግ እና መቅረብ ይኖርበታል።
  9. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ወረዳ 5 ጤና ጣቢያ የ/ግ/ቡድን ቢሮ በመቅረብ በየሎቱ የማይመለስ ብር 300.00 ( ሶስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።

ተጫራቾች የተጠቀሱትን ዕቃዎች የሚያቀርቡበትን ሰነድ የአንዱን ዋጋ ከነቫት እና ጠቅላላ ዋጋ ከነቫቱ በመግለፅ ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻ በማድረግ በታሸገ ፖስታ ሙሉ አድራሻቸውንና የጨረታውን አይነት (ሎት) በመጥቀስ ወረዳ 5 ጤና ጣቢያ /የግ/ቡድን/አስ/የስራ ሂደት ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ከቀኑ 11 ሠዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

10. የጨረታውን ሂደት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን ከቀኑ 3፡00 ታሽጎ በ3፡30 ሠዓት ላይ በወረዳ 5 ጤና ጣቢያ ሁለገብ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ።

11. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት እቃ ናሙና ለሚቀርብባቸው ዕቃዎች ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡ ለቋሚ ዕቃዎች ግዢ ፎቶእና ዝርዝር መግለጫ ማኑዋል መቅረብ ይኖርበታል፡፡ናሙና ያልቀረበላቸው ሰነዶች ለውድድር የማይቀርቡ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡ናሙና 6 ወር ካለፈው መጠየቅ አይቻልም።

12. አሸናፊ ተጫራቾች ዕቃውን ሲያስገቡ ከጠዋቱ 2፤30--5፤30 ሰዓት ሲሆን ከሰዓት ከ7፤30--9፤30፤ሰዓት ብቻ መሆኑን እያሳወቅን ከተጠቀሰው ሰዓት ውጪ የሚመጡትን የማናስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን።

Ø የጨረታው አሸናፊ የሆነው ድርጅት አሸናፊ መሆኑን በደብዳቤ ከተገለጸለት በኋላ ከሰባት(7) የስራ ቀን በኃላ ቀርቦ ያሸነፈበትን የውል ማስከበሪያ 10% ህጋዊ ሲፒኦ በማስያዝ ውል መዋዋል ይኖርበታል፡፡ እቃዎቹን በተቋሙ ንብረት ክፍል ድረስ አጠናቀው ማቅረብ ግዴታ ነው።

መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ ፡- ኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 5 ጤና ጣቢያ ልዩ ስሙ

ከኤፍኤም ሬዲዮ ጣቢያ ከፍ ብሎ(72 ሰባራ ድልድይ)

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡-0113697443

በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከ ከተማ የወረዳ 5 ጤና ጣቢያ


Tender details

  • Deadline: 2026-08-28
  • Bid closing time: 09:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 3፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-28 09:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 3፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Kolfe Keranyo Sub City Woreda 5 Health Office
  • Buyer address: ኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 5 ጤና ጣቢያ ልዩ ስሙ ከኤፍኤም ሬዲዮ ጣቢያ ከፍ ብሎ (72 ሰባራ ድልድይ)
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 300.00 ብር በየሎቱ
  • Published on: Addis Zemen (Aug 17, 2026)
  • Posted at: 2026-08-18T11:17:45.000Z
← Back to all tenders