Cleaning and Janitorial Equipment and Service
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት የተለያዩ የጽዳት ዕቃዎች፣ የቢሮ እስቴሽነሪ ዕቃዎች፤ የሠራተኞች የደንብ ልብስ፣ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የመኪና ጎማ እና ቋሚ የቢሮ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት የተለያዩ የጽዳት ዕቃዎች፣ የቢሮ እስቴሽነሪ ዕቃዎች፤ የሠራተኞች የደንብ ልብስ፣ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የመኪና ጎማ እና ቋሚ የቢሮ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም፡- ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የመስፈርት ሁኔታዎች በቅድሚያ መሟላት ይኖርባቸዋል።
1. የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው መሆኑ፤
2. በኢትዮጵያ የግብር ሕጎች በተደነገገው መሰረት የግብር እና የታክስ ግዴታ መወጣት ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፤
3. ከጥቃቅን አነስተኛ ተቋማት የተጻፈ የድጋፍ ደብዳቤ በተጨማሪ በሀገር ውስጥ ዕቃዎች ላይ የተሳተፉ ስለመሆኑ ከአምራቾች ጋር የተደረገ ውል (ማስረጃ) ማቅረብ የሚችሉ፤
4. የቫት ከፋይነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
5. በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
6. ውል ማስከበሪያ የሚመለስ 10% በባንክ በተረጋገጠ (cpo) ማቅረብ የሚችሉ፤
7. የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ (cpo) ማቅረብ ማስያዝ አለባችሁ፤ (ሎት 1) 71,783.00 (ሎት 2) 88,592.00 (ሎት 3) 110,033.00 (ሎት 4) 3,933.00 (ሎት 5) 43,106.00 (cpo) ማቅረብ የሚችሉ፤
8. ከላይ የተገለጸው ዝርዝር የያዘ የማይመለስ 400.00 (አራት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አቃቃ ክ/ከተማ ወረዳ 8 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት 4ኛ ፎቅ ፋይናንስ ጽ/ቤት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
9. ተጫራቾች በሚጫረቱበት ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በግልጽ በመሙላት ኦርጅናል እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማድረግ ሁለቱንም ፖስታ በአንድነት በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሽግ ይህ ማስታውቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ለዚሁ ጨረታ ለማገልገል በተዘጋጀው ሳጥን አራተኛ ፎቅ ፋይናንስ ጽ/ቤት በመቅረብ ማስገባት ይቻላል።
10. ጨረታው የሚከፈተው በ11ኛውቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አቃ/ቃ/ክ/ከተማ ወረዳ 8 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት 4ኛ ፎቅ ይከፈታል፡፡ ሆኖም የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት አያግድም።
11. ተጫራቾች በሚጫረቱበት ዕቃ ጨረታው ከመከፈቱ ከአንድ ቀን በፊት ሳንፕል (ናሙና) ማቅረብ አለባቸው።
12. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ከሆነ ጨረታው ተቀባይነት የለውም።
13. ዘግይቶ የደረሰ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፤
14. ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ወረዳ 8 አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል።
15. ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ አድራሻ፡- አቃቂ ቃልቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 አስተዳደር ቀሊቲ ቶታል ወይም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሳሎ ቅርንጫፍ ፊት ለፊት 4ኛ ፎቅ ፋይናንስ ጽ/ቤት
ስልክ ቁጥር 011-434-02-54
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-28
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታውቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-28 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታውቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Akaki Kality Sub City Woreda 8 Administration Finance Office
- Buyer address: የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 አስተዳደር
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 400.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 17, 2026)
- Posted at: 2026-08-18T11:55:45.000Z