Audio Visual, Photography and Filming Service and Equipment
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በስልጤ ዞን የአለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ዘመናዊ ካሜራ ከነ ሙሉ አክሰሰሪዎቹ ወይም ማቴሪያሉ "Canon EOS R5" ካሜራ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Audio Visual, Photography and Filming Service and EquipmentArtEquipment and Accessories
Central Ethiopia
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በስልጤ ዞን የአለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለአለም ገበያ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል ዘመናዊ ካሜራ ከነ ሙሉ አክሰሰሪዎቹ ወይም ማቴሪያሉ "Canon EOS R5" ካሜራ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-
- በመስኩ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የተጨማሪ እሴት ተክስ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ እና ከግብር ዕዳ ነፃ ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥ ታክስ ክሊራንስ ሊኖራቸው ይገባል እንዲሁም የመንግስት መስሪያ ቤቶች በሚያወጡት ጨረታ ላይ ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፣
- የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000(ሰላሳ ሺህ) ብር በህጋዊ ባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ.(CPO) ወይም በ “Letter of credit" ወይም በካሽ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- አሸናፊው ተጫራች በጨረታ ያሸነፋውን እቃ በራሱ ትራንስፖርት የግዢ ፈጻሚው መሥሪያ ቤት የንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይጠበቅበታል።
አንዱ ባቀረበው ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም። - ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ስለ እቃው (ካሜራው) መረጃ የሚገልጽ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 400 (አራት መቶ) ብር በመክፈል በአለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 (አስር) በመምጣት ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚችሉ መሆኑን እያሳወቅን የጨረታ ሰነዱን በሚገባ በመሙላት 01 (አንድ) ኦርጂናል እና 01 (አንድ) ኮፒ ለየብቻ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት በኋላ ባለው 16ኛው የስራ ቀን እስከ ቀኑ 6፡30 ሰዓት ድረስ በአለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚሁ ዕለት ከቀኑ 6፡30 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
- የተወዳዳሪ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታውን መክፈቻ ቀን አይለወጥም።
ለበለጠ መረጃ፦ በስልክ ቁጥር፡-09-08-19-14 58 ወይም 09-12-95-68 37 ይደውሉ።
በስልጤ ዞን የአለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-02
- Bid closing time: 12:30
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት በኋላ ባለው 16ኛው የስራ ቀን እስከ ቀኑ 6፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-02 14:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት በኋላ ባለው 16ኛው የስራ ቀን እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት
- Region: Central Ethiopia
- Publishing entity: Silte Zone Alem Gebeya City Administration finance office
- Bid bond: 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ) ብር
- Bid document price: 400 (አራት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Aug 18, 2026)
- Posted at: 2026-08-18T12:00:05.000Z