Printed Advertising Materials

በኢትዮጵያ ጉምሩከ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የተተው ዕቃዎች ግልፅ ጨረታ ቁጥር ግ-07/2019 ጨረታ

በኢትዮጵያ ጉምሩከ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስመጪዎች በተሻሻለው የጉምሩከ አዋጅ ቁጥር 1160/2011 መሰረት የተተው ወይም የተወረሱ ዕቃዎችን በእቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 መሠረት የተተዉ ንብረቶችን

  • 3 PLY TOP CORRUGATED CARTON BOX PRINTED AND 5-PLY BOTTOM CORRUGATED CARTON BOX: HAIR CLIPPER GEEMY,PERFUME & MEN TROUSERS ELECTRIC CRANE SCALE AS TOUCH SCREEN OCA GLASS,M-TRIANGLE M2,7" LCD SCREEN DEFOAMING MACHINE WITH BUBBLE REMOVER & OTHERS አቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በዚህም መሠረት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጫረት የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

  1. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፤ ዓይነት፣ ብዛት፣ የጨረታ ሠነድ እና መመሪያ መገለጫ አንዲሁም የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ዘወትር ከሰኞ እስከ ሐሙስ ከጠዋት 2፡00 አስከ ቀኑ 6፡00 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 አስከ ቀኑ 10፡30 እና ዓርብ ከጠዋት 2፡00 እስከ ቀኑ 5፡00 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡30 እስከ ቀኑ 10፡30 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋት 2፡00 እስከ ቀኑ 5፡30 የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) በመክፈል ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ገቢ ሂሳቦች ቡድን መሙሰድ ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር በዘርፉ የፀና ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር: የተጨማሪ እሴት ታከስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ሆኖም ገምታዊ ዋጋቸው ከብር 500,000.00 በታች የሆኑ ማንኛውንም ዕቃ ለመገዛት የተጨማሪ እሴት ታከስ ምዝገባ ሠርተፍኬት ማቅረብ ሳያስፈልግ መወዳደር ይችላሉ።
  3. ማንኛውም ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረትበትን ጠቅላላ ዋጋ 5% ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንከ በተረጋገጠ CPO ጨረታ ከመከፈቱ በፊት በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ተጫራቾች የሚያስይዙት CPO በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሥም ETHIOPIAN CUSTOMS COMMISSION MOD]O BRANCH OFFICE በሚል ሲሆን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከአዲስ አበባ : አዳማ እና ሞጆ ቅርንጫፎች መዘጋጀት ስስበት፡፡ ተሳታፊዎች ዋጋ መሙላት የሚችሱት በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ተዘጋጅቶ ማህተም ያረፈበት ሠነድ ላይ ብቻ መሆን ይኖርበታል።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በመገዛት የሚወዳደሩበትን ዕቃ አሰቀድሞ ማየት ያለባቸው ሲሆን ዕቃውን ሳያዩ ለሚሞሉት ዋጋ ቅ/ጽ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም፡፡ በጨረታ ተሸጦ የተወሰደ እቃ ተመላሽ አይደረግም ለእቃውም የተከፈለ ገንዘብ አይመለስም።
  5. የግልፅ ጨረታ ተሳታፊ ተጫራቾች አያንዳንዱን ዕቃዎች ለመግዛት የሚያቀርቡት የመጫረቻ ዋጋ፣ የሞሉበት ሠነድ፣ በተራ ቁጥር 2 የተገለፁትን ማስረጃዎች ኮፒ አና ያቀረቡት የመጫረቻ ዋጋ 5% ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO በኢንቬሎፕ ወይም በፖስታ በማሸገ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣ ቀን ጀምሮ ለ8 ተከታታይ ቀናት አስከ የመጨረሻው ቀን ጠዋት 4፡45 ድረስ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዕዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይቻላል፡፡ የጨረታ ሣጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚመጡ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
  6. የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ የወጣበት ቀንን ጨምሮ በ8ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4:45 ታሽጉ በዚሁ ዕለት ጠዋቱ 5፡00 ላይ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለጨረታ በአዘጋጀው ቢሮ ውስጥ ይከፈታል።
  7. ማንኛውም በግልጽ ጨረታ የሚሳተፍ ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ዋጋ መቀየር ወይንም የሌላ ተጫራቾችን ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ አሻሽሎ ማቅረብ አይችልም፤ በጨረታ ሽያጭ ውድድር ላይ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤት አና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም፡ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ እራሱን ከጨረታ ውድድር ማገለል አይቻልም አና የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት አስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።
  8. የግልጽ ጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ስለማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ ዕቃን መረከብ አለበት፡፡ በ5 (ስምስት) ቀናት ውስጥ ገንዘቡ ገቢ ካልተደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል።
  9. በተራ ቁጥር 8 በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ አድርጎ ዕቃውን ያላነሳ/ያልተረከበ እንደሆነ ለሚቆይበት ለተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ ይከፍላል፡፡ ሆኖም ዕቃ በ2 (ሁለት) ወራት ውስጥ ካልመጣ አንደተተወ ተቆጥሮ በጨረታ ሽያጭ ይወገዳል።
  10. አሸናፊው ተጫራቾች ዕቃዎችን ለመረከብና ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሁሉ ራሱ ይሸፍናል።
  11. ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለጨረታ የአቀረበውን ዕቃ ብዛት ለመጨመርም ሆነ ለመቀነስ ሙሉ መብት አለው፡፡ በጨረታ ተሽጦ በጨረታ አሸናፊው የተወሰደ እቃ አይመለስም።
  12. ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዕቃዎቹን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ወይም ዘዴ ከአገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  13. ለተጨማሪ ማብራሪያ በሥልክ ቁጥር 022-236-90-94 ላይ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ

በገቢዎች ሚኒስቴር ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-25
  • Bid closing time: 10:45
  • Bid closing (note): የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ የወጣበት ቀንን ጨምሮ በ8ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4:45 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-25 11:00
  • Bid opening (note): የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ የወጣበት ቀንን ጨምሮ በ8ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 5:00 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Ethiopian Customs Commission
  • Buyer address: በአባይ ማዶ ዲያስፖራ መንገድ ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ካለው የአማራ ህንጻ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ጎን
  • Bid bond: 5%
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 18, 2026)
  • Posted at: 2026-09-18T09:55:57.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders