Cleaning and Janitorial Equipment and Service
የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት የስቴሽነሪ እና ፅዳት ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት የስቴሽነሪ እና ፅዳት ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ ተጫራቾች፦
1) የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ በጨረታ ለመወዳደር የሚያስችል ክሊራንስ፣ ህጋዊና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ያላቸውና በጨረታው ለመሳተፍ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያሳይ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን አለባቸው።
2) የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) የስራ ቀናት ውስጥ በስራ ሰዓት ገንዘብ ያዥ ቢሮ ወይም ሂሳብ ክፍል በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡ ቅዳሜና እሁድ የመስሪያ ቤቱ የስራ ሰዓት አይደሉም።
3) ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) የስራ ቀናት ውስጥ በጨረታ ሰነዱ ላይ ለተጠቀሱት ዕቃዎች ዋጋ ዝርዝር በመሙላት በአገልግሎቱ ዋና መስሪያ ቤት የግዥ ቡድን ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የተጫራቾች ዋጋ በግልፅ የሚነበብና ስርዝ ድልዝ የሌለው መሆን ይኖርበታል። ስርዝ ድልዝ ያለበት የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
4) ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዚያው ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡30 ይከፈታል።
5) ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ተጨማሪ ዕሴት ታክስን ጨምሮ የሚቀርቡትን አጠቃላይ ዋጋ 2% (ሁለት በመቶ) ለስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት (Refugees and Returnees Service) በሚል የተዘጋጀ የባንክ ማዘዣ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ (unconditional Bank Guarantee) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
6) ተጫራቾች የሚቀርቡትን የዕቃ ናሙና የጨረታ ሰነድ በሚስገቡበት ወቅት ይዞ በመምጣት የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት ከማለፉ በፊት ለግዥ ቡድን ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል።
7) የጨረታው አሸናፊ ውል በሚፈርምበት ወቅት የመልካም ስራ አፈፃጸም ማስከበሪያ / Performance Bond/ እቃዎቹን ለማቅረብ ያሸነፈበትን አጠቃላይ ዋጋ 10 (አስር በመቶ) ለስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት (Refugees and Returnees Service) በሚል በተረጋገጠ የባንክ ማዘዣ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ (unconditional Bank Guarantee) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
8) የጨረታው አሸናፊ ጥሪው በደረሰው በ10 ቀናት ውስጥ በአገልግሎቱ ዋና መስሪያ ቤት ቀርቦ የስራ ውል መፈረም አለበት፡፡
9) አሸናፊው ጥሪ በደረሰው በአስር ቀናት ውስጥ በአገልግሎቱ ዋና መስሪያ ቤት ቀርቦ ውል ካልፈረመ አሸናፊነቱ ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስዘው ገንዘብ ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ይሆናል።
10) አሸናፊ ተጫራች የሚያቀርበው ዕቃ ለውድድሩ አቅርቦ በተመረጠለት ናሙና መሰረት መሆን አለባቸው።
11) አሸናፊ ሆነው የተመረጡ ድርጅቶች የሚቀርቡት ዕቃ የጥራት ጉድለት ቢኖረው ለመቀየር የሚስማሙ መሆን አለባቸው።
12) አገልግሎት መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ
የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት
የእንቁላል ፋብሪካ አደባባይን ሳይሻገሩ ከፌዴራል ፖሊስ ክበብ ፊት ለፊት
ስልክ ቁጥር፡ 09-97-23-66-31 / 09-43-01-29-44
የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ቁጥር 1
Tender details
- Deadline: 2026-08-27
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00
- Bid opening: 2026-08-27 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Refugee and Returnee Service
- Buyer address: ከዋሽንግተን የህክምና ማዕከል 500 ሜትር ያህል ገባ ብሎ ወደ ቦሌ ሚካኤል በሚወስደው መንገድ ላይ
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 17, 2026)
- Posted at: 2026-08-18T12:03:54.000Z