Stationery
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አስተዳዳር የፋይናንስ ጽ/ቤት የተለያዩ የእቃና አገልግሎት ግዥ አይነቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
StationeryOffice Supplies and ServicesCleaning and Janitorial Equipment and Service
Addis Ababa
More tags
Textile, Garments and UniformsTextile, Garment and LeatherShoes and Other Leather ProductsEquipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsComputer and AccessoriesIT and TelecomOffice Machines and AccessoriesOffice FurnitureFurniture and FurnishingHouse FurnitureProducts and ServicesAgriculture and FarmingRaw Materials and SuppliesMachinery and EquipmentLabour Outsourcing ServicesTransportation ServiceWarehousing, Transit and Transport ServiceEvent Organizing and PlanningAdvertising and PromotionPrinted Advertising MaterialsPrinting and PublishingCatering and Cafeteria ServicesOthersMaintenance and RepairVehicleRentAmharic2merkatoKolfe Keraniyo Sub City Administration Woreda 04 F/E/D/Bureau
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ኮ/ቀ/ክ/ከ/ወ/4/ፋ/የጨ/ቁ 001/19
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አስተዳዳር የፋይናንስ ጽ/ቤት የግዥ የስራ ሂደት በ 2019 በጀት ዓመት በወረዳ ውስጥ ለሚገኝ ባለ በጀት መ/ቤቶች በበጀት ዓመቱ ለሚያከናውነው የእቃና አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም በሎት / ምድብ የግዥ አይነቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት1 አላቂ የቢሮ እቃዎች (ስቴሽነሪ) ግዥ
- ሎት2 የጽዳት እቃዎች ግዥ
- ሎት3. የደንብ ልብስ ግዥ
- ሎት 4 ኤሌክትሮኒክስ ግዥ
- ሎት5. ቋሚ እቃ ግዥ እና የተለያዩ የሚጠገኑ ተገጣጣሚ እቃዎች ጥገና
- ሎት6 የአትክልት ዘር እና የግብርና ዕቃዎች ግዥ
- ሎት7 የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ
- ሎት8 የመድረክ ዲኮር
- ሎት9 የህትመት አገልግሎት
- ሎት10 የመስተንግዶ አገልግሎት
- ሎት 11 የኮምፒውተር፣የፕሪንተር ፣ፍቶ ኮፒ
- ሎት 12 የጉልበት ስራ
በመሆኑም መ/ቤታችን ከላይ ከተራ ቁጥር 1-12 በተዘረዘሩት የግዥ ምድቦች መወዳደርና መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች /አቅራቢ/ አወዳድሮ ግዥውን ለመፈፀም ይፈልጋል።
- የዘመኑ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያለው እና የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው።
- የግብር ከፋይነት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበ እና ተጫራቾች የተመዘገቡበትን ኮፒ ማቅረብ የሚችል
- ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት ተመዝጋቢዎች መሆን አለባቸው።
- የሚቀርበው የዋጋ ሰነድ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት።
- ጨረታው ሲከፈት የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ ማለትም ሎት1፡-23,721 ሎት2፡ 8,953 ሎት3፡-44,706 ሎት4፡13,000 ሎት5-10,000 ሎት6፡12,000 ሎት7፡10,000 ሎት8፡ 5,000 ሎት9፡-12406 ሎት10- 4368 ሎት11፡- 23453 ሎት12፡- 26,494 በCPO መቅረብ አለበት።
- በስራ ከህሎት የተደራጁ ኢንተርፕራይዝ ከሆነ በተደራጁበት ዘርፍ ላይ ብቻ ልዩ ድጋፍ የሚደረግላቸው ሲሆን ካደራጃቸው ጽ/ቤት ሀላፊ በተፈረመ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከስራ ዘርፍ ውጭ ለሆኑት እንደማንኛውም ነጋዴ የሚስተናገዱ ይሆናል።
- አሸናፊው ተጫራች በሰነዱ ውስጥ በተመለከተው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርቦ ውል መዋዋል አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርበውን ሰነድ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን በየሎቱ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ፡- ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ።
- ከሎት 1-3 ለተገለጹት ዕቃዎች ሰነዱን በሚያስገቡበት ቀን ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡ ናሙና ያላቀረበ ድርጅት ከውድድር ውጪ ይሆናል፡፡እቃው በናሙናው ላይ ያለውን የጥራት ደረጃ ይዞ ካልተገኘ ተመላሽ ይደረጋል።
- ገዢው አካል የሚገዛውን እቃ እስከ 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል።
- ለአሸናፊ ተጫራቾች በሰነድ ውስጥ የተካተተውን ጊዜ ገደብ ውስጥ ማለትም እስከ 10 ቀን ድረስ ቀርበው የውል ማስከበሪያ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፉበትን እቃ 10% ሲፒዮ አሰርተው ውል መዋዋል አለባቸው።
- ተጫራቾች ተወዳድረው ያሸነፉባቸውን እቃዎች በወቅቱ ማቅረብ ካልቻሉ ያስያዙት ሲፒኦ ይወረሳል ተመላሽ አይደረግም
- የእቃ ማስረከቢያ በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 04 የፋይናንስ ጽ/ቤት የግዥ ንብረት አስተዳደር ይሆናል።
- በሚቀርበው የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ የድርጅቱ ሀላፊ ወይም ህጋዊ ውክልና ያለው ከውክልናው ደብዳቤ አያይዞ ስምና ፊርማ የድርጅቱ አድራሻ እና ስልክ ቁጥር መኖር አለበት።
- መ/ቤቱ ተገቢ ነው ብሎ ካመነበት ከጨረታው አሸናፊ ድርጅት ጋር እስከ 6ወር ድረስ ውሉን ባያድስም የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ከወጣበት የመጀመሪያው ቀን አንስቶ ለሚቆጠር 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆይና በ11ኛው ቀን ጠዋት4፡00 ስዓት ታሽጎ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 04 የፋይናንስ ጽ/ቤት የግዥ ስራ ሂደት ቢሮ ውስጥ ይከፈታል።
- የዕቃ ማጓጓዣ ብር አሸናፊው ተጫራች ይሸፍናል።
- ጨረታው የሚከፈትበት ኛው ቀን የእረፍት ቀን ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በተከታዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
- ተጫራቾች ሰነድ በሚያስገቡበት ጊዜ ከመስሪያ ቤቱ የተሸጠላቸውን ሰነድ ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር መመለስ አለበት።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነድ መውሰድይችላሉ።
አድራሻ፡- ከአየር ጤና ወደ አለም ባንክ በሚወስደው መንገድ ከትሮፒካል ከፍ ብሎ ወረዳ 4 ህንፃ 1ኛ ፎቅ ፋይናንስ ፅ/ቤት ለበለጠ መረጃ 011-8-33 84 81/ 011-3-69-37-20
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አስተዳዳር የፋይናንስ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-29
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-29 10:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ጠዋት 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Kolfe Keraniyo Sub City Administration Woreda 04 F/E/D/Bureau
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 400.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 18, 2026)
- Posted at: 2026-08-18T12:16:35.000Z