Cleaning and Janitorial Equipment and Service
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
ግልፅ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ ጨረታ መለያ ቀጥር 001/2019 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ሎት1 የፅዳት እቃዎች፣ ሎት2 አላቂ የፅህፈት መሳሪያ ፣ ሎት3 የደንብ ልብስ፣ ሎት 4 ባነር እና ኅትመት ስራ፣ ሎት 5 የመስተንግዶ አገልግሎት ፣ ሎት 6 ጭነት አገልግሎት፣ ሎት 7 የትራንስፖርት አገልግሎት፣ ሎት 8 የድንኳን አገልግሎት፣ ሎት 9 ሎት የደንብ ልብስ ስፌት ፣ሎት11 የእስፖርት ትጥቅ ፣ ሎት 12 ጥገና
ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርት የሚያሟሉ መሆን አለባቸው፡፡
1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑ ግብር ለመከፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢነት የተመዘገበና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
3. የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው፡፡
4. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል::
5. ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ማቅረብ የሚችል እና በጥቃቅን እና አነስተኛ የተደራጀ ከሆኑ መወዳደር በሚፈቀድላቸው ዘርፍ በቀጥታ ለጽ/ቤታችን የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል፡፡
ሎት1 የፅዳት እቃዎች 10.000 ብር ፣ ሎት 2 አላቂ የፅህፈት መሳሪያ 15,000 ብር ፣ ሎት 3 ደንብ ልብስ 20,000 ብር ፣ ሎት 4 ባነር እና ኅትመት 3,000 ብር ፣ ሎት 5 የመስተንግዶ አገልግሎት 3,000 ብር፣ ሎት 6 ጭነት አገልግሎት 5,000 ብር፣ ሎት 7 የትራንስፖርት አገልግሎት 4,000 ብር፣ ሎት 8 የድንኳን አገልግሎት 2,000 ብር ፣ ሎት 9 የደንብ ልብስ ስፌት 3,000 ብር፣ ሎት10 የኤሌክትሮኒክስ እቃ 5,000 ብር ፣ ሎት11 ጥገና 3,000 ብር የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎቱ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ ትንሹ ህንጻ ሁለተኛ ፎቅ እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቾች ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ትንሹ ህንጻ ሁለተኛ ፎቅ አስተዳደር እና ፋይናንስ ጽ/ቤት በመምጣት ዋጋው የተሞላበትን የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባችሁ::
8. ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ታሽጎ በሚቀጥለው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተሰጠው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የከፈታል፡፡
9. ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸው፡፡
10. ተጫራቾች ጨረታውን ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡
11. ተጫራቾች ባስገቡበት ናሙና መሰረት እቃዎችን የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡ ይህ ሆኖ ካልተገኘ ከናሙናው ውጪ ያመጡ ተጫራቾች ንብረታቸው ሙሉ በሙሉ ተወርሶ ለወረዳ አስተዳደሩ ገቢ ይደረጋል፡፡
12. የጨረታ ውጤት ከታወቀበት ቡኋላ ናሙና 6ወር ከሞላው ወደ አስተዳደሩ እስቶር ተወርሶ ገቢ ይደረጋል፡፡
13. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፉበትን እቃዎች በ5 ቀናት ውስጥ ለመስሪያ ቤቱ በራሱ ትራንስፖርት ማስረከብ ይኖረበታል፡፡
14. መ/ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው እቃ እስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 አስተዳደር እና ፋይናንስ ጽ/ቤት ቦሌ ቡልቡላ/ ከሳሪስ አቦ 3ኪ.ሜ ገባ ከቦሌ ሚካኤል 4ኪ.ሜ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ ትንሹ ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ::
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0926 783 334
ማሳሰቢያ፡- በመጨረሻም የጨረታ ሳጥን የሚገኝበት ቦታ ጨረታው ከተዘጋ ቡኋላ የሚቀርብ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-27
- Bid closing time: 17:30
- Bid closing (note): ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-28 12:00
- Bid opening (note): ጨረታው 10 ቀን ቆይቶ በሚቀጥለው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Bole Sub City Woreda 12 Administration FEDB
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 300.00 ብር በየሎቱ
- Published on: Addis Zemen (Aug 17, 2026)
- Posted at: 2026-08-18T12:28:09.000Z