Textile, Garments and Uniforms

አንቆርጫ ቅ/አ/አ/መ/ደ/ት/ቤት የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 001

በየካ ክፍለ ከተማ በወረዳ 10 ት/ጽ/ቤት አንቆርጫ  ቅ/አ/አ/መ/ደ/ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  1. ሎት 1 የደንብ ልብስ
  2. ሎት 2 እላቂ የቢሮ እቃዎች
  3. ሎት 3 አላቂ የትምህርት ዕቃዎች
  4. ሎት 4 የፅዳት እቃዎች
  5. ሎት 5 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች
  6. ሎት 6 የጥገና እቃዎች
  7. ሎት 7 ቋሚ እቃዎች
  8. ሎት 8 ቋሚ እቃዎች
  9. ሎት 9 ልዩ ልዩ ክፍያዎች

በዚህ መሰረት በጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች

  1. በዘርፉ የተሰማሩ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
  2. የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ
  4. በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ
  5. ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል የሚመለስ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ወይም CPO ሲፒኦ ብር በእያንዳንዳቸው
    • ሎት 1 ብር 5000.00 (አምስት ሺህ ብር ብቻ)
    • ሎች 2 ብር 4000.00 (አራት ሺህ ብር ብቻ)
    • ሎት 3 ብር 4000.00 (አራት ሺህ ብር ብቻ)
    • ሎት 4 ብር 6000.00 (ስድስት ሺህ ብር ብቻ)
    • ሎት 5 ብር 4000.00(አራት ሺህ ብር ብቻ)
    • ሎት 6 ብር 4000.00(አራት ሺ ብር ብቻ)
    • ሎት 7 ሎት 8 እና ሎት 9 ብር 7,500.00 (ሰባት ሺህ አምስት መቶ ብር) ማቅረብ አለባቸው።
  6. ዝርዝር ጨረታውን የያዘውን ሰነድ የማይመለስ ሁለት መቶ 200.00 ብር በመክፈል የአንቆርጫ ቅ/አ/አ/መ/ደ/ት/ቤት የፋይናንስ ድጋፍ የስራ ሂደት ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  7. ተጫራቾች የሚጫረቱትን እቃ ናሙና ለሚያስፈልገው ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ይኖርባችዋል።
  8. ሳምፕል ለማምጣት አስቸጋሪ ከሆነ በፎቶ ማቅረብ ይቻላል።
  9. ተጫራቾች ጨረታ አሸንፈው ውል ሲዋዋሉ የአጠቃላይ ዋጋውን ብር 10% ውል ማስከበሪያ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  10. የጨረታው ሰነድ ኮፒና ኦርጅናል በመለየት በተለያየ ፓስታ አሽገው ሲመጡ ሲፒኦ ደግሞ ጨረታው ኦርጅናል ባለበት
  11. ፖስታ ውስጥ በማስገባት አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  12. ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋ ዝርዝር ሰነድ ላይ ባለው ዋጋ በማቅረብ በግልጽ ሞልተው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ እስከ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ድረስ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 11፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  13. የጨረታው ሳጥን ማስታወቂያ ከወጣበት በ11ኛው ቀን በ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 4፡30 በፋይናንስ የስራ ሂደት ቢሮ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል። በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀናት በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል።
  14. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻችን ኮተቤ 32 ቁጥር ማዞርያ ከፍ ብሎ አንቆርጫ ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን ከፍ ብሎ

ስልክ፡- 011 866 4718/09

የአንቆርጫ ቅ/አ/አ/መ/ደ/ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-29
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): የጨረታው ሳጥን ማስታወቂያ ከወጣበት በ11ኛው ቀን በ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-29 10:30
  • Bid opening (note): የጨረታው ሳጥን ማስታወቂያ ከወጣበት በ11ኛው ቀን በ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ankorcha Kindergarten and Primary School
  • Buyer address: ኮተቤ 32 ቁጥር ማዞሪያ ከፍ ብሎ አንቆርጫ ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን ከፍ ብሎ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 18, 2026)
  • Posted at: 2026-08-18T12:52:43.000Z
← Back to all tenders