Cleaning and Janitorial Equipment and Service
በሻሻመኔ ከተማ አስተዳድር መልካ ኦዳ አጠቃላይ ሆስፒታል 2019 በጀት የተለያዩ ዕቃዎችን እና የኦክስጅን ሲሊንደር ማስሞላትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በሻሻመኔ ከተማ አስተዳድር መሪ ኦዳ አጠቃላይ ሆስፒታል 2019 በጀት የተለያዩ ዕቃዎችን እና የኦክስጅን ሲሊንደር ማስሞላትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
1. የጽሕፈት መሳሪያዎች
2. የጽዳት ዕቃዎች
3. የተለያዩ ኤሌክትሮኒክ ዕቃዎች
4. የሕንጻ መሳሪያዎች
5. የኤሌክትሪክ ዕቃዎች
6. ለመኪና ጥገና የሚውሉ ዕቃዎች
7. ለሰው ጤና የሚውል የኦክስጂን ሲሊንደር መሙላት
1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን መልካ ኦዳ አጠቃላይ ሆስፒታል በመቅረብ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 1000/አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ በመግዛት በነጠላ ወይም (ጥቅል ለመጫረት የሚፈልጉ ተጫራቾች ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
2. የጨረታው ሰነድ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ዋናውንና ኮፒውን በተናጠል በማሸግ ቢሮ ቁጥር 10 ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች የሚያስገቡት የጨረታ ማሰከበርያ ዋስትና ሲፒኦ 10000/አስር ሺህ ብር/ ሲሆን ሲፒኦ በባንክ የተረጋገጠ መሆን አለበት
4. ጨረታው በ16ኛው ቀን በ4፡00 ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሆስፒታላችን ይከፈታል።
5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ጋር አካተው መቅረብ ያለባቸው ሰነዶች የሚከተሉት ናቸው።
ሀ. ከሚቀርቡት ዕቃ ጋር የተዛመደና በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድና ገቢዎች የምዝገባ የምስክር ወረቀት።
ለ. የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ ለ15 ቀን ይሸጣል።
ሐ. ከፌዴራል አገር ውስጥ ገቢ ወይም ከክልሎች ግብር ሰብሳቢ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ወቅታዊ የግብር ግዴታዎችን የተወጡና በጨረታው መካፈል የሚችሉ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ አቅርቦት የምስክር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
መ. የታደሰ የንግድ ፈቃድ ቲን /TIN/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች የተጠቀሱትን ዕቃዎች በከፊል ወይም በሙሉ መጫረት ይችላሉ።
ሠ. ተጫራቾች የሚያሲዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ /CPO/ መጠን በጨረታ መመሪያ ላይ የተገለጸ ሲሆን ሲፒኦውን ከኦርጂናል ሰነድ ወይም በታሸገ ኤንቨሎፕ ከጨረታው ሰነድ ጋር አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
ረ. ተጫራቾች በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ የድርጅታቸውን ማሕተም እና ፊርማ ማስቀመጥ አለባቸው። ያልተመታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
ሰ. ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ሸ. ጨረታን ያሸነፈው አካል ከቢሮ ጋር ውል በመፈራረም በተፈራረመው ውል መሠረት ዕቃውን ማቅረብ ግዴታ አለበት።
ለተጨማሪ መረጃ ከዚህ በታች በተጠቀሰው ስልክ ቁጥር ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
ስልክ ቁጥር፡- 09 13 25 93 45
መልካ ኦዳ አጠቃላይ ሆስፒታል
Tender details
- Deadline: 2026-09-02
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ4፡00
- Bid opening: 2026-09-02 10:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30
- Region: Oromia
- Publishing entity: መልካ ኦዳ አጠቃላይ ሆስፒታል
- Bid bond: 10,000.00 ብር
- Bid document price: 1,000.00 ብር ለእያንዳንዱ ሰነድ
- Published on: Addis Zemen (Aug 18, 2026)
- Posted at: 2026-08-18T12:54:20.000Z