Stationery

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የኤ/ግ/ወ/ገንዘብ ፅ/ቤት ለወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች በ2019 በጀት ዓመት የጽህፈት መሳሪያ፣ ቋሚ የቢሮ እቃዎች እና የመኪና ዕቃ መለዋወጫ በግልፅ የጨረታ አግባብ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ኤግገ/09/40/2018

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የኤ/ግ/ወ/ገንዘብ ፅ/ቤት ለወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች በ2019 በጀት ዓመት የጽህፈት መሳሪያ ፣ቋሚ የቢሮ እቃዎች እና የመኪና ዕቃ መለዋወጫ በግልፅ የጨረታ አግባብ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም መወዳደር የምትፈልጉ፡-

1. ተጫራቾች በዘርፉ የተመዘገበ እና በዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የግዥ መጠኑ ብር 200,000 እና ከዚህ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክሰ ከፋይነት መረጃ ማቅረብ የሚችል

2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሎት 1 ለጽህፈት መሳሪያና ለቋሚ የቢሮ እቃዎች 15,000 ብር፣ ሎት 2 ለመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች 15,000 (አስራ አምስት ሺህ ብር) እና ከዚያ በላይ ማሲያዝ እንደሚጠበቅባቸው ይኸውም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በፅ/ቤታችን ገቢ ደረሰኝ በመቁረጥ ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብራችሁ ማስገባት ይኖርባችኋል።

3. ተጫራቾች በጨረታ መክፈቻ ወቅት እንዲገኙ አይገደዱም ነገር ግን በጨረታው መገኘት አለብን ብለው ካሰቡ መገኘት ያለበት አካል የተጫረተው ባለቤት ወይም ህጋዊው ውክልና ያለው አካል ኦርጅናል የውክልና ማስረጃውን ይዞ መቅረብ ይኖርበታል።

4. ተጫራቾች ሁሉንም ዕቃ በየሎቱ ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ 1000 / አንድ ሺህ ብር/ በመክፍል መግዛት የሚችሉ ሲሆን በኤ/ግ/ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ዘወትር በስራ ሰዓት ከቢሮ ቁጥር 6 ማግኘት ይችላሉ።

5. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ12/12/2018 ዓ.ም እስከ 26/12/2018 ዓ.ም ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ16ኛው ቀን ማለትም 27/12/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ስዓት ይከፈታል።

6. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እና ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም ።

7. ተጫራቾች ለወሰዱት የተጫራች መመሪያ የጨረታ ሠነድ/ በእያንዳንዱ ገፅ ላይ የድርጅታቸውን ማህተም በማድረግ ሙሉ በሙሉ መመለስ ይጠበቅባቸዋል።

8. በየሎቱ በጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበው አሸናፊ ስለሚሆን ለእያንዳንዱ እቃ ዋጋ ሙሉ በሙሉ ጨረታው ላይ ዋጋ መሞላት አለበት ይህ ካልሆነ ግን ከውድድር ውጭ ይሆናል።

9. አሸናፊ የሆነው ተጫራች እያንዳንዱን እቃ በሚፈለገው የጽ/ቤቱ ንብረት ክፍል በሞዴል 19 ገቢ ማድረግ አለበት። ገቢ ላደረገበት እቃ ሞዴል 19 በመያዝ ክፍያ ይፈፀምለታል።

10. ጽ/ቤቱ ግዥውን በ20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡።

11. ፅ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

12. የኮምፒውተር ወረቀትና እስኪርቢቶ ናሙና የምናቀርብ ስለሆነ በናሙናው መሠረት መሙላት ይጠበቅባቸዋል።

ማሳሰቢያ፡- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ የሚከፈት ይሆናል። ጨረታውን በተመለከተ በስልክ ቁጥር 09 13 27 49 51 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የኤ/ግ/ወ/ገንዘብ ፅ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-02
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-09-02 10:30
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: North Shewa Zone Efratana Gidem Woreda F/Plan Bureau
  • Bid bond: 15,000.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Bid document price: 1,000.00 ብር ለእያንዳንዱ ሰነድ
  • Published on: Addis Zemen (Aug 18, 2026)
  • Posted at: 2026-08-18T13:03:10.000Z
← Back to all tenders