Cleaning and Janitorial Equipment and Service

የሰዴንሶዶ ወረዳ ፍርድ/ቤት በ2019 የበጀት አመት የተለያዩ የደንብ ልብስ፣ የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች (ፈሪኒቸር)፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችና የመሳሰሉት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የግዢ ጨረታ ቁጥር 001/2019 ዓ/ም መመሪያ

የሰዴንሶዶ ወረዳ ፍርድ/ቤት በ2019 የበጀት አመት የተለያዩ የደንብ ልብስ፤ የጽህፈት መሣሪያዎች ፤ የጽዳት ዕቃዎች ፣ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች (ፈሪኒቸር)፤የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ና የመሳሰሉት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፋልግ ከዚህ በታች የተገለፁትን መመሪያ በመከተል እና ከዚህ ጋር ተያይዞ በቀረበው ገጽ ዝርዝር ዕቃዎች መሠረት ተጨራቾች ይህንን የጨረታ መመሪያ አክብረው እንዲካፈሉ እናሳውቃለን።

1. ተጫራቾች በጨረታ ለመካፈል ህገዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፋሉ፤የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው ፤ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) እና የቲን ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባችዋል።

2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም በሌላም በሚመለከታቸው ፈቃድ ሰጪ አካላት አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው።

3. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኃላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለጹትን ማንኛውንም ሁኔታ መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለው ማለት አይችልም ።

4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበርያ ብር 5,000.00(አምስት ሺህ ብር ብቻ ) ባበንክ በተመሰከረለት (CPO) ማስያዣ አለባቸው።

5. አሸነፊዎች በሚገቡት ውል መሰረት ለመፈጸም ለውል ማስከበሪያ ያሸነፉትን ጠቅላለ ዋጋ 10% (አስር በመቶ) ወይም(CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

6. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰአት እስከ መስከረም 04/2019 ዓ.ም ከቀኑ 10፡30 ሰዓት ድረስ በሰዴንሶዶ ወረዳ ፍርድ ቤት ቢሮ ቁ. 14 በመቅረብ የማይመለስ 200.00/ሁለት መቶ ብር / ብቻ ለሰዴን ሶዶ ወረደ ፍርድ ቤት በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

7, ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣ ጀምሮ እስከ መስከረም 05/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ከቀኑ በ6፡30 ሰዓት በመስሪያ ቤቱ ቅጥር ግቢ በመቅረብ ለዚህ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ፡፡ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 6፡30 ታሽጎ በ 8፡00 ሰዓት ተጫረቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ለሰዴንሶዶ ወረደ ፍርድ ቤት ቢሮ 14 ቁጥር ይከፈታል ፡፡ሆኖም ባለቤቱ ወይም ህጋዊ ወኪሉ ባልተገኙበትም ይከፈታል ፡፡ ነገር ግን ህጋዊ ውክልና የሌለው ሰው ምንም ዓይነት ጥያቄ ወይም ሀሳብ ማቅረብ አይችልም

8. የጨረታ ሰነዱ በሠዓቱ በጨረታ ሣጥን ውስጥ ካልገባ ተቀበይነት የለውም።

9. የጨረታው ሠነድ ኦርጅናልና ኮፒው ለየብቻ በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ መግባት አለበት።

10. የጥቃቅንና አነስተኛ ማይክሮ ኢንተርፕራይዝ ለውድድረ የሚቀርቡት የዘመኑን ሂሳብ ኦዲት አስደርገው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

11. የጥቃቅንና አነስተኛ ማይክሮ ኢንተርፕራይዝ የጨረታ ማስከበሪ ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር ብቻ ) በባንክ በተመሰከረለት (CPO) ማስያዝ አለባቸው፡፡ ሆኖም ከመ/ቤቱ ጋር ውል ይፈራረማሉ።

12. ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስልክ ቁጥር፡- 0113 250 010 /46/ 0912 237 033/ 0910 090 257

ለበለጠ መረጃ አድራሻችን ከቱሉ ቦሎ ከተማ በስተ ደቡብ በኩል በ27 ኪሎ ሜትር ላይ ይገኛል።

የሰዴን ሶዶ ወረዳ ፍርድ ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-15
  • Bid closing time: 12:30
  • Bid opening: 2026-09-15 14:00
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Seden Sodo Woreda Court
  • Buyer address: ከቱሉ ቦሎ ከተማ በስተደቡብ በኩል በ27 ኪሎ ሜትር ላይ ይገኛል
  • Bid bond: 5,000.00 ብር
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 18, 2026)
  • Posted at: 2026-08-18T13:05:57.000Z
← Back to all tenders