Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ቁጥር 3 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የተለያዩ እቃዎችን ግዥ መፈፀም ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር 001/2019

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ቁጥር 3 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የሚከተሉትን እቃዎች ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

  • ሎት አንድ: አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
  • ሎት ሁለት፡የደንብ ልብስ
  • ሎት ሶስት፡-የፅዳት እቃዎች
  • ሎት አራት፡-የህትመት ስራዎች
  • ሎት አምስት: ቋሚ አላቂ እቃዎች
  • ሎት ስድስት፡-የመኪና ማስዋቢያ እቃዎች
  • ሎት ሰባት፡ ቋሚ እቃ፣የኮምውተር መለዋወጫ እቃዎች እንዲሁም የቢሮ ጥገና እቃዎች /Maintenance tool Kit
  • ሎት ስምንት፡-ውሃና ቆሎ
  • ሎት ዘጠኝ ፡-የአልሙኒየም የቢሮ ፓርቲሽን እና የቢሮ ማስዋብ/ እድሳት ስራ
  • ሎት አስር፡-ለህፃናት ማቆያ አገልግሎት ላይ የሚውል የህፃናት መንከባከቢያ ንፅህና መጠበቂያ ፤መጫወቻዎች፤አልጋ እና ልዩ ልዩ እቃዎች

በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

1. ከሚወዳደሩበት ዕቃ ወይንም አገልግሎት ግዥ ጋር ለመወዳደር ተያያዥነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃዎችን (ክሊራንስ) ከግብር አስገቢው መ/ቤት ማቅረብ የሚችሉ።

2. በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር አገልግሎት ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት ግዥ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

3. ለተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT )የተመዘገቡ መሆኑን እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(Tin Number) ሰርተፊኬት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

4. የአገር ውስጥ የድጋፍ አቅራቢዎች ምዝገባ ምስክር ወረቀት(በጥቃቅን አነስተኛ የተደራጁ ማህበራት) የተደራጁ መሆኑን እና ከአደራጃቸው አካል ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ለአጠቃላይ ከሎት አንድ እስከ ሎት ዘጠኝ ለእያንዳንዳቸው ሎቶች 5000/አምስት ሺህ ብር/ ሎት አስር 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በባንክ በተመሰከረለት (C.P.O)ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ C.P.O መሰራት ያለበት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ለአዲስ አበባ ቁጥር 3 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በሚል አድራሻ መሆን አለበት።

5. ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200.00(ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታ መክፈቻው ቀን ድረስ ሳሊተ ምህረት ቤ/ክርስቲያን ፊትለፊት ሜሪዲያን ህንፃ ከሚገኘው የአዲስ አበባ ቁጥር 3 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከግዥ ቡድን ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ:: የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያጠቃለለ እና ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው የጨረታ ሰነዱ ኦርጅናልና ኮፒውን ለየብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ አለባችሁ።

6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጥንቃቄ በማሸግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን ድረስ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይገባቸዋል:: ጨረታው በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት በመ/ቤቱ አዳራሽ 3ኛ ፎቅ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል:: እያንዳንዱ ተጫራች ለጨረታ ለመወዳደር በሚቀርብበት ወቅት ፋይናንሻ እና ቴክኒካል ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ የዋጋ ማቅረቢያ /ዝርዝር/ በተለያየ ፖስታ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ ኮፒ እና ኦርጅናል ተለይቶ በፖስታው ውጫዊ ገጽ መጻፍ አለበት።

7. ሰነዱን በሚመልስበት ወቅት ስልጣን ባለው አካል መፈረምና የድርጅቱ ማህተም መደረግ አለበት ነገር ግን የሚፈርመው አካል ተወካይ ከሆነ የውክልና ማስረጃ መያያዝ አለበት።

8. አንዱ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።

9. የጨረታው አሸናፊ የአሸናፊነት ደብዳቤ እንደደረሰው የውሉን ዋጋ 10% (አስር ፐርሰንት) CPO በውል ማስከበሪያነት በማስያዝ ከመ/ቤቱ ጋር ውል ይፈራረማል።

10. ተጫራቾች በሚወዳደሩባቸው ሁሉም ዕቃዎች ላይ የጨረታ ሰነዱን ሲያስገቡ ናሙናዎችንም ለንብረት አስተዳደር ክፍል ማስረከብ አለባቸው።

11. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታዉ ከተከፈተበት ጀምሮ ባሉት 90 ቀናት ይቆያል።

12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስልክ ቁጥር 0111 673 1504 / 0111 673 0650

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ቁጥር 3 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

አዲስ አበባ


Tender details

  • Deadline: 2026-08-29
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን ድረስ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-29 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን ድረስ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ቁጥር 3 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 18, 2026)
  • Posted at: 2026-08-18T13:30:40.000Z
← Back to all tenders