Equipment and Accessories
በአርሲ ዞን የጢዮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር፣ የጽህፈት መሣሪያዎች፣ ለመንግስት ሠራተኞች የደንብ ልብስ፣ የጽዳት እቃዎች እና የመኪና ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Equipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsComputer and Accessories
Oromia
More tags
IT and TelecomOffice Machines and AccessoriesOffice Supplies and ServicesHouse FurnitureFurniture and FurnishingOffice FurnitureStationeryTextile, Garments and UniformsTextile, Garment and LeatherShoes and Other Leather ProductsCleaning and Janitorial Equipment and ServiceSpare Parts and Car Decoration MaterialsAmharic2merkatoበአርሲ ዞን የጢዮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Description
የጨረታ ማስታወቂያ ቁ-01
በአርሲ ዞን የጢዮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚዉሉ
- ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ፣
- ፈርኒቸር፣
- የጽህፈት መሣሪያዎች፤
- ለመንግስት ሠራተኞች የደንብ ልብስ፣
- የጽዳት እቃዎች እና የመኪና ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም:
- ለተጠየቁት የግዥ እቃዎች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ የዘመኑን ግብር ከፍለዉ የንግድ ፈቃዳቸዉን ያሳደሱና በፌደራል፣ በክልል ወይም በዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ወይም በግዥዎችና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ በአቅራቢነት ሊስት የተመዘገቡበትን፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸዉ እንዲሁም የግብር ክፉይነት መለያ ቁጥር (Tax Payer Registration No.) ዋናዉንና ኮፒዉን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች ለቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ለቋሚ የቢሮ ፈርኒቸር እቃዎች እና ለጽህፈት መሣሪያዎች ለመንግስት ሠራተኞች የደንብ ልብስ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር)እንዲሁም ለጽዳት እቃዎች እና ለመኪና ጎማዎች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በጽ/ቤቱ ስም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሂሳብ ቁጥር 1000022874466 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ድረስ የጽ/ቤቱ የግዥና ንብረት አስተዳደርየሥራ ሂደትቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ከግብር ሰብሳቢዉ መ/ቤት የዘመኑን ግብር አጠናቀው ለመክፈላቸው እና ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ደብዳቤ መቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት በዝግ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 15ኛው የሥራ ቀናት ማቅረብ የሚኖርባቸዉ ሲሆን፤ ጨረታዉም በ16ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ በ7፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ጽ/ቤቱ አዳራሽ ይከፈታል።
- ማንኛዉም ተጫራች ለቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፤ ለቋሚ የቢሮ ፈርኒቸር እቃዎች እና ለጽህፈት መሣሪያዎች እና ለመንግስት ሠራተኞች የደንብ ልብስ ለእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ) እንዲሁም፤ ለጽዳት እቃዎች እና ለመኪና ጎማዎች ለእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ) በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የታጠቀ ባንክ በክፍያ ማዘዛ ወይም ሲፒኦ (CPO.) ብቻ ማቅረብ ይኖርበታል።
- አሸናፊዉ ተጫራች ያለምንም የአቅርቦት ችግር አስተማማኝ የሆነ የዕቃ ክምችት ያለዉና እቃዎቹን በራሱ የማጓጓዣ ወጪ አሰላ ከተማ ዉስጥ በሚገኘዉ የወረዳዉ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ አምጥቶ ማስረከብ ይኖርበታል።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር (0911005877)(0943351752) (0944630894) ይጠይቁ።
በአርሲ ዞን የጢዩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-04
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-04 13:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 7፡30 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: በአርሲ ዞን የጢዮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
- Bid bond: 20,000.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Published on: Addis Zemen (Aug 18, 2026)
- Posted at: 2026-08-18T13:42:11.000Z