Building Construction
ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቨሎፕመንት /ECD/ ባለ 12 ቀዳዳ/ ክፍል የሴት ተማሪዎች (የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን ያካተተ) መጸዳጃ ቤት ሙሉ የግንባታ ሥራ የኮንስትራክሽን ሥራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ
ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቨሎፕመንት / ECD/ እና ፔስታሎዚ የህፃናት መርጃ ድርጅት /PCF/ በጋራ በመሆን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር በሚገኙ 16 የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተማሪዎችን ውጤት ማሻሻል' የሚል ሙሉ ትኩረቱን በትምህርት ጥራት ላይ ያደረገ ፕሮጀክት በመተግበር ላይ ይገኛሉ፡፡ በመሆኑም ድርጅታችን ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቨሎፕመንት /ECD/ ለተማሪዎች ምቹ የመማሪያ አካባቢን ለመፍጠር በሚያደርገው እንቅስቃሴ ቀጥሎ የተመለከተውን የኮንስትራክሽን ሥራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የግንባታው አይነት |
የግንባታው ቦታ |
የሚፈለገው የኮንትራክተር ደረጃ |
ጨረታው የሚያበቃበት ቀን |
ጨረታው የሚከፈትበት ቀን |
|
|
ባለ 12 ቀዳዳ/ ክፍል የሴት ተማሪዎች (የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን ያካተተ) መጸዳጃ ቤት ሙሉ የግንባታ ሥራ |
አዲስ አበባ፡ ኣዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8(መሳለሚያ ሰፈር) ዳግማዊ ብርሃን ቁ1 ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መለስተኛ ትምህርት ቤት |
ደረጃ 5 እና ከዚያበላይ |
ነሐሴ 22/2018 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት
|
በተመሳሳይ ቀን ነሐሴ 22/2018 ዓ.ም 8፡30 ሰዓት
|
ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
- ደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ የሆነ የግንባታ ፍቃድ ያላቸው እና የምዝገባ ሰርተፊኬታቸውን ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ የሚችሉ፤
- በዘርፉ ለመስራት የሚያስችላቸው የ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው
- ከገቢዎች ሚኒስቴር የተሰጠ የ2017 ዓ.ም የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የቫት (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑና ሰርተፊኬቱን ማቅረብ የሚችሉ፣
- ግንባታውን ለመሥራት የጠየቁት ጠቅላላ የገንዘብ መጠን 5% (አምስት በመቶ) በ Ethiopian Center for Development /ECD/ ስም የዋስትና ማስያዣ CPO ብቻ ማቅረብ የሚችሉ፣
- CPO ለብቻው በፖስታ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
- በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ተመሳሳይ የሥራ ልምድ ያላቸው ይህንኑ ማሳየት የሚችሉ ቢሆን ይመረጣል፡
- አግባብነት የሌላቸው ፎርጂድ ዶከመንቶችን ማቅረብ በህግ የተከለከለ ሲሆን ይህ ሆኖ ቢገኝ ከጨረታው ከማስወገድ ጀምሮ በህግ አካላት እንዲጠየቁ ይደረጋል፡፡ ሙሉ መረጃውንም ለህግ አካላት አሳልፈን የምንሰጥ ይሆናል፡፡ ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በድርጅታችን ዋና መሥሪያ ቤት በአካል በመገኘት የጨረታ ሰነዱን ስለመውሰዳችሁ በተዘጋጀው አቴንዳንስ ላይ ፈርማችሁ ድርጅቱ ያዘጋጀውን ኦሪጂናል ስካን ቢድ ዶክመንት በሶፍት ኮፒ ወዲያው በቴሌግራም በነጻ የሚላክላችሁ ሲሆን ከዚያም በሶፍት ኮፒ የወሰዳችሁትን ዶክመንት ፕሪንት በማድረግ አስፈላጊ መረጃዎችን በማሟላት የቴክኒካል እና የፋይናሻል ፕሮፖዛላችሁን በተለያዩ ኤንቨሎፖች በአንድ ትልቅ ኤንቨሎፕ በማሸግ በሁለት ኮፒ (ኦሪጂናል እና ኮፒ) በተጠቀሰው ቀን ገቢ እንድታደርጉ እና እንድትወዳደሩ እንገልጻለን፡፡ በትልቁ ኤንቨሎፕ ላይ የድርጅቱን ሙሉ ስም አድራሻ እና ማህተም መጻፍ ይኖርበታል።
አድራሻ፦ ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቨሎፕመንት /CD/
አዲስ አበባ፣ ቦሌ አለም ህንፃ 7ኛ ፎቅ
ስልክ፦ 0982 88 2826
ማሳሰቢያ፦
- በአካል ተገኝተው በጨረታ ሰነዱ መውሰጃ እና መመለሻ ቅጽ ላይ ካልፈረሙ መወዳደር አይቻልም።
- ድርጅታችን ያለ ምንም ቅድመ ማስጠንቀቂያ እና ማስታወቂያ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቨሎፕመንት / ECD/
Tender details
- Deadline: 2026-08-28
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-08-28 14:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Center for Development (ECD)
- Buyer address: Bole Road Haile Alem Building, 7th Floor
- Bid bond: 5%
- Published on: Addis Zemen (Aug 18, 2026)
- Posted at: 2026-08-18T14:30:40.000Z