Stationery
በኦሮሚያ ክልል በምሥራቅ ወለጋ ዞን የኑኑ ቁምባ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በወረዳዉ ሥር ላሉት የመንግሥት መ/ቤቶች ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚዉል እቃዎችን ለመግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልል በምሥራቅ ወለጋ ዞን የኑኑ ቁምባ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በወረዳዉ ሥር ላሉት የመንግሥት መ/ቤቶች ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚዉል፡-
- የጽፈት መሣሪያዎችና የጽዳት ዕቃዎችን
- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ና ሞተር ሳይክሎችን
- የሠራተኞች ደንብ ልብስ
- ቋሚ የቢሮ ዕቃዎችን
- የመኪና ፤ የሞተር ሣይክል ጎማዎችና ካለመዳሪያዎችን
- ለቴክኒክና ሙያ ሥልጠና የሚያገለግሉ መሣሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ።
ስለዚህ የሚከተሉትን መሥፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን በጨረታዉ እንድሳተፉ ይጋብዛል።
1. በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉ የዘመኑ ግብር የከፈሉና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ።
2. ተጫራቾች የጨረታዉን ዝርዝር መግለጫ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20 ተከታታይ የመንግሥት የሥራ ቀናት የማይመለስ ለእያንዳንዱ ሰነድ/ሎት/ 1000.00(አንድ ሺህ) ብር በመክፈል ከኑኑ ቁምባ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት መግዛት ይችላሉ ።
3. በአቅራቢነት ዝርዝር ዉስጥ ስለመመዝገባቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
4. ተጫራቾች ለጨረታዉ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ከታወቀ ባንክ ተረጋግጦ በሚቀርብ ሲ.ፒ.ኦ(CPO) የሚመለስ ብር ለእያንዳንዱ ሰነድ /ሎት/ 5000(አምስት ሺህ) ብር ወይም በካሽ ከጨረታዉ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. አስተማማኝና ጥራት ለሌላቸዉ ዕቃዎች ተጠያቂነትን የሚወሰወዱ።
6. ተወዳዳሪዎች የተጠየቁትን ማስረጃ በሙሉ እያንዳንዱን ሎት ለየብቻ በማድረግ ቴክንካልና ፋይናንሻል ኦሪጅናልና ፎቶ ኮፒዉን ለየብቻ በማድረግ የዕቃዎቹን የዋጋ ዝርዝር መግለጫ በጨረታ ማወዳደሪያ ሰነድ ላይ ስማቸዉን፤ ፊርማቸዉን፤ አድራሻቸዉን በማስፈርና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ የጨረታ ዶክመንቶችን ኦርጂናልና ኮፒዉን ሁለቱን በአንድ ትልቅ በሰም በታሸጌ ፖስታ ዉስጥ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20 ተከታታይ ቀናት በቢሮ ቁጥር 1 (አንድ) በተዘጋጀዉ የጨረታ ሣጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
7. ተወዳዳሪዎች ፤ ሕጋዊ ወኪሎቻ ወይም እነሱ በሌሉበትም በ21ኛዉ ቀን ከረፋዱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ4፡30 ላይ ዉድድሩ ይካሄዳል ።
8. የጨረታ ሣጥኑ ከታሸገ ወይም ከተከፈተ በኋላ የሚቀርብ ማንኛዉንም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለዉም።
9. የጨረታ አሸናፊ በራሱ ወጭ ዕቃዎችን በወረዳዉ ገ/ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ገቢ አድርጎ ገንዘቡን ይቀበላል ።
10.ቲ.ኦ.ት (TOT) 3% (ፐርሰንት) የመቁረጥ ግዴታ አለበት ።
11.የ 2018 ዓ.ም ግብር የከፈሉበትን ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል ።
12. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 0922 195 233
የኑኑ ቁምባ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-10
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛዉ ቀን ከረፋዱ በ4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-10 12:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛዉ ቀን ከረፋዱ በ4፡30 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: East Wollega Zone Nunu Kumba Woreda F/E/D/Bureau
- Bid bond: 5000.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Bid document price: 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/ ለእያንዳንዱ
- Published on: Addis Zemen (Aug 18, 2026)
- Posted at: 2026-08-18T14:59:49.000Z