Cleaning and Janitorial Equipment and Service
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር ልዩ ልዩ የጽዳት ዕቃዎች (ፎጣ፣ አቡጅዲ) እና የፎቶና ቪዲዮ ካሜራ እንዲሁም የፎቶና ቪዲዮ ካሜራ አክሴሰሪዎች ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ ለመፈጸም ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
CN/NCB/01/19
የድርጅታችን ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር
- ሎት1፦ ልዩ ልዩ የጽዳት ዕቃዎች (ፎጣ፣ አቡጅዲ)
- ሎት 2፡- የፎቶና ቪዲዮ ካሜራ እንዲሁም የፎቶና ቪዲዮ ካሜራ አክሴሰሪዎች) ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ ለመፈጸም ይፈልጋል።
በመሆኑም ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣በጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡትን ማስረጃ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ እና የዕቃው ወይም የአገልግሎቱ ዝርዝር መግለጫ በተለየ በሰም በታሸገ ፖስታ እንዲሁም ዕቃዎቹን የምታቀርቡባቸውን ዋጋ በተለየ በሰም በታሸገ ሁለተኛ ፖስታ በማድረግ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል።
የጨረታ ዶክመንቱን ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ የግዢ ዋና ክፍል ብር 100.00 በመክፈል ከሰኞ እስከ ዓርብ (ጠዋት 2፡00-6፡00 እንዲሁም ከሠዓት 7፡00-11፡00) እና ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጠዋት ማግኘት ይቻላል። የጨረታ ማስከበሪያ ለያንዳንዱ ሎት ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከመጫረቻ ዶክመንት ጋር መቅረብ ይኖርበታል።
ተጫራቾች የመጫረቻ ዶክመንታቸውን ከላይ በተጠቀሰው አድራሻና የሥራ ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ነሃሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም 4:00 ጠዋት ድረስ ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው በዚሁ ዕለት በ 4፡30 ጠዋት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ያላሟላ ተጫራች ያለተጨማሪ ማስታወቂያ ከውድድሩ ዉጪ ይደረጋል።
ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ
ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ
ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ
ስልክ ቁጥር 011-156 9992
አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
Tender details
- Deadline: 2026-09-01
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-09-01 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Commercial Nominees P.L.C.
- Buyer TIN: 0000958158
- Buyer address: ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ
- Bid bond: 100,000.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 19, 2026)
- Posted at: 2026-08-19T07:23:26.000Z
- Buyer website: https://commercialnominees.com/