Wood and Wood Working
ቢ ኤንድ ቢ ኢንጂነሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በአዲስ አበባ ከተማ በሚገነባው 2B+G+13 ሕንፃ ፕሮጀክት በንዑስ ተቋራጭነት (Subcontract) ለሚከተሉት የሥራ መደቦች አመልካቾችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል
Major contract
Wood and Wood WorkingContract Administration and SupervisionConstruction and Water Works
Addis Ababa
Description
- የድርጅቱ ስም፦ ቢ ኤንድ ቢ ኢንጂነሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
- ቀን፦ ነሐሴ 13 ቀን 2018 ዓ.ም
- የሥራ ቦታ፦ አዲስ አበባ
ቢ ኤንድ ቢ ኢንጂነሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በአዲስ አበባ ከተማ በሚገነባው 2B+G+13 ሕንፃ ፕሮጀክት በንዑስ ተቋራጭነት (Subcontract) ለሚከተሉት የሥራ መደቦች አመልካቾችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።
1. የፎርም ወርክ ካርፔንተር (Formwork Carpenter)
ተፈላጊ ችሎታ እና ልምድ፦
- የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሰርተፊኬት ያለው።
- ከሙያ እና ቴክኒክ (TVET) ወይም ከታወቀ ተቋም የተሰጠ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ያለው።
- በፎርም ወርክ ስራ በተለያዩ ሕንፃዎች ላይ ቢያንስ የ 5 ዓመት የሥራ ልምድ ያለው።
- የስትራክቸር እና የፎርም ወርክ ዲዛይን ማንበብ እና መተግበር የሚችል።
- ከዚህ ቀደም በህንፃ ስራዎች (በተለይም በፎቅ ህንፃዎች/High-rise buildings) ላይ የሰሩባቸውን ፕሮጀክቶች የሚያስረዱ ይፋዊ ደብዳቤዎች ማቅረብ የሚችል።
- የስራ ልምዳቸውን እና የሰሯቸውን ዋና ዋና ፕሮጀክቶች ዝርዝር (company profile) ማቅረብ የሚችል
የሥራ ቦታ፦ አዲስ አበባ
2. ባር ቤንደር / የብረት ሠራተኛ (Bar Bender & Steel Fixer)
ተፈላጊ ችሎታ እና ልምድ፦
- የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሰርተፊኬት ያለው።
- ከሙያ እና ቴክኒክ (TVET) ወይም ከታወቀ ተቋም የተሰጠ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ያለው።
- በኮንክሪት ብረት ስራ (Bar Bending & Fixing) በፎቅ ሕንፃዎች ላይ ቢያንስ 5 ዓመት የሥራ ልምድ ያለው።
- የብረት ዲዛይን (Bar Bending Schedule - BBS) ማንበብ፣ የብረት ብክነትን መቀነስ እና በትክክል ማሰር የሚችል።
- ከዚህ ቀደም በህንፃ ስራዎች (በተለይም በፎቅ ህንፃዎች/High-rise buildings) ላይ የሰሩባቸውን ፕሮጀክቶች የሚያስረዱ ይፋዊ ደብዳቤዎች።
- የስራ ልምዳቸውን እና የሰሯቸውን ዋና ዋና ፕሮጀክቶች ዝርዝር (company profile) ማቅረብ የሚችል
የሥራ ቦታ፦ አዲስ አበባ
የማመልከቻ ሁኔታ
መስፈርቱን የምታሟሉ እና በአንዱ ወይም በሁለቱም ስራዎች መሳተፍ የምትፈልጉ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የትምህርት እና የሥራ ልምድ ማስረጃችሁን ከህጋዊ የ VAT እና TIN ምዝገባ ሰነዶች ጋር በመያዝ ማመልከት ትችላላችሁ።
- አድራሻ - ጀሞ 1 ሃውዲ ሞል ቢሮ ቁጥር 410
- ስልክ ቁጥር - +251 911599715 ወይም +251 954556413
Tender details
- Deadline: 2026-08-29
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት
- Bid opening: 2026-08-29 17:00
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን እና ሰዓት አልተገለጸም
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: B and B Engineering PLC
- Buyer TIN: 0064248193
- Published on: 2merkato.com (Aug 19, 2026)
- Posted at: 2026-08-19T07:27:01.000Z