Stationery

በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 01 ፋይናንስ ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ በጨረታ ቁጥር 01/2019 ዓ.ም

በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 01 ፋይናንስ ጽ/ቤት በወረዳው ስር ለሚገኙ ጽ/ቤቶች በ 2019 በጀት አመት በ 1ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም የሚመለከታቸው ድርጅቶች ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሰረት መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

  • ሎት 1 የጽሕፈት መሳሪያዎች
  • ሎት 2 የፅዳት ዕቃዎች
  • ሎት 3 የደንብ ልብስ
  • ሎት 4 የህትመት ስራዎች
  • ሎት 5 የኮምፒውተር ጥገና አገልግሎት
  • ሎት 6 የመስተንግዶ አገልግሎት 
  • ሎት 7 ቋሚ ዕቃ
  • ሎት 8 የትራንስፖርት አገልግሎት 
  • ሎት 9 የድንኳን ኪራይ
  • ሎት 10 የጭነት አገልግሎት

ከላይ የተገለጹትን እቃዎች መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች ቀርበው ሰነድ ገዝተው መወዳደር ይችላሉ።

  • ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችል የዘመኑ ግብር የገበረ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና ምዝገባ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል።
  • የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ የተጫራቾች የምስክር ወረቀት ያላቸው ተጫራቾች እያንዳንዱ የሚወዳደሩበት ጨረታው የእቃውን ዝርዝር ሰነዱን ላይ ያለውን ብቻ መሰረት ማድረግ ይኖርባችዋል።
  • የጨረታ ማስከበሪያ በእያንዳንዱ ሎት 1) 30,000 ብር ሎት 2 ) 30,000 ብር ሎት 3) 30,000 ብር  ሎት 4) 2,000 ብር ሎት 5) 2,000 ሎት 6 ) 2,000 ሎት 7) 20,000 ሎት 8) 2,000 ከላይ የተቀመጠው የማስከበሪያ ብር CPO ብቻ ማቅረብ አለባቸው።
  • ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ሲያስገቡ የሚጫረቱባቸውን የእቃዎች በሙሉ ሳምፕል (ናሙና) ማቅረብ አለባቸው።
  • የጨረታ ማስከበሪያ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ለአንድ ጨረታ ሰነድ በመከፈል በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 1 ፋይናንስ/ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ መውሰድ ይችላል።
  • የጨረታ አሸናፊዎች ያሸነፉበት እቃዎችን በራሳቸው ትራንስፖርት ማቅረብ አለባቸው።
  • መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • በጨረታው ሰነድ ውስጥ መ/ቤቱ ከጠቀሳቸው የእቃዎች ዝርዝር ውጪ ያስገቡ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ ይሆናሉ።
  • የጨረታ አሸናፊዎች ያሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው ዋጋው ጸንቶ የሚቆይበት አሸናፊዉ ከተለየበት አንስቶ ለ60 ቀናት ይሆናል።
  • ተጫራቾች የጨረታዉ ፖስታ ላይ የድርጅቱ ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡ ለእያንዳንዱ ለተወዳደሩበት በየሎቱ CPO ማስያዝ አለባችሁ ጥቅል CPO ካስገቡ ከጨረታ ውጭ ይሆናሉ በጥቃቅን የተደራጁ ከሆነ በሚያመርቱት ምርት ከሆነ ጨረታ ሰነድ በነጻ የሚወስዱ ይሆናል በማያመርቱ ምርት ላይ ሰነድ የሚገዙ ይሆናል።
  • በጨረታ ሂደት ላይ ለማሳሳትና የማጭበርበር ስራ ላይ የሚሳተፉ ተጫራቾች ህጉ በሚያዘው በኢትዮጵያ ህግ የሚዳኝ ይሆናል።
  • ለቋሚ እቃዎች ናሙና ለማይቀርብላቸዉ የእቃዎቹ እስፔፊኬሽን ከኦርጅናል ሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸው።
  • ተጫራቾች የጨረታ ፖስታው ኮፒ ና ኦርጅናል በማሸግ ማስገባት አለባቸው፡፡ CPO ውን ኦርጅናሉን ሰነድ ላይ ማያያዝ አለበት ኮፒ ላይ ከተደረገ ከጨረታው ላይ ተሳታፊ አይሆኑም ተጫራቾች የሚያስገቡት ዋጋ ቫትን የጨመረ መሆን አለበት።
  • ማንኛውም ተጫራች በጨረታው አፈጻጸም ሂደት ላይ ቅሬታ ቢኖረዉ በ 5 የስራ ቀናቶች ውስጥ ቅሬታ ማስገባት ይችላሉ፡፡ በ 6ኛው ቀን ቅሬታ ማቅረብ አይችሉም።
  • ለጨረታ የቀረቡትን የእቃ ናሙናዎች ውጤት በተገለጸ በ 10 ቀናት ውስጥ እቃዎችን መውሰድ አለባችሁ ይህ ባይሆን እቃዎቹ ለመስሪያቤቱ ገቢ ይሆናል።
  • ጨረታውም አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ 10 የስራ ቀናቶች የሚቆይ ይሆናል 10ኛ ቀን ላይ 11፡00 ሰዓት ላይ የሚዘጋ ይሆናል በ11ኛው ቀን ሰነድ ማስገባት አይቻልም በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ሲሆን ቀኑ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ተጫራቾች ወይም ወኪሎች ቢኖሩም ባይኖሩም የሚከፈት ይሆናል።

አድራሻ ቦሌ ሚካኤል ከጉምሩክ ወረድ ብሎ ኮንደምንም ጀርባ ቦሌ ክፍለ
ከተማ ወረዳ 1 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡-011 816 0211
በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 01 ፋይናንስ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-29
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ጨረታውም አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ 10 የስራ ቀናቶች የሚቆይ ይሆናል 10ኛ ቀን ላይ 11፡00 ሰዓት ላይ የሚዘጋ ይሆናል
  • Bid opening: 2026-08-31 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታውም አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Bole sub-city woreda 01 finance office
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር) ለአንድ ጨረታ ሰነድ
  • Published on: Addis Zemen (Aug 19, 2026)
  • Posted at: 2026-08-19T08:53:48.000Z
← Back to all tenders