Equipment and Accessories
የዴራ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት በከተማው ዉስጥ ለሚገኙ ሴክተር መስርያ ቤቶች አገልግሎት የሚዉሉ የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ ቁ-01/2019
የዴራ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት በከተማው ዉስጥ ለሚገኙ ሴክቴር መስርያ ቤቶች አገልግሎት የሚዉሉ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፤ኤሌክትሮክኒስ ፤ የጽሕፈት መሣሪያዎች፤ የቢሮ ዉስጥ ልዩ ልዩ አላቂ ዕቃዎች ፤የጽዳት ዕቃዎች : የሠራተኞች ደንብ ልብስ እና ለመኪና ጎማዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም፡-
1. ለተጠየቁት የግዢ እቃዎች ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለቸዉና የዘመኑን ግብር ከፍለዉ የንግድ ፍቃዳቸዉን ያሳደሱ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ(VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tax payer Registration number)ያለቸዉ እና በፌዴራል ፤በክልል ወይም በዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ወይም በግዢዎችና ንብረት ማስወገድ ኤጄንሲ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያለቸዉ ዋናዉና ኮፒዉን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. ተጫራቾች ለቋሚ የቢሮ ዕቃዎች ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ፤ ለጽሕፈት መሣሪያዎች ፤ለጽዳት እቃዎች ለሠራተኞች የደንብ ልብስ እና ለመኪና ጎማዎች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በጽሕፈት ቤቱ ስም በ ሲንቄ ባንክ በሂሳብ ቁጥር 1071392621217 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጽሕፈት ቤቱ የግዢና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 4 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት በዝግ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 15ኛዉ የሥራ ቀን ከረፋዱ በ 4፡00 ሰአት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከረፋዱ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት የጽሕፈት ቤቱ የግዢና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 4 ይከፈታል።
4. እለቱ የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተራ ቁጥር 3 በተጠቀሰዉ መሰረት ጫረታዉ ይከፈታል።
5. ማንኛውም ተጫራች ለእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 (አስር ሺህ) በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የታወቀ ባንክ በክፍያ ማዘዣ(CPO) ብቻ ማቅረብ ይኖርበታል።
6. አሸናፊዉ ተጫራች ያለ ምንም የአቅርቦት ችግር አስተማማኝ አስፈላጊ የሆነ የዕቃ ክምችት ያለዉና ዕቃዎቹን በራሱ የማጓጓዣ ወጪ ዴራ ከተማ ዉስጥ በሚገኘዉ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ አምጥቶ ማስረከብ ይኖርበታል።
7. ማንኛዉም ተጫራች እስክሪብቶዎች ፤የፒሪንተር ቀለሞች እና ደንብ ልብስ ለይ የሚወዳደር ለሚወዳደሩበት እቃ ናሙና(ሣምፕል) ማቅረብ አለበት።
8. ተጫራቹ አሸናፊ ከሆነ ላሸነፈበት ዕቃ ከመስሪያ ቤቱ ጋር ዉል መግባት ይጠበቅበታል፤ ለዉል ማስከበሪያም ያሸነፈበት ከእቃ ዋጋ 10% በካሽ ወይም በ(CPO) ማስያዝ ይጠበቅበታል።
ዴራ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት አርሲ ዴራ ከ አዳማ በአሰላ መስመር 25 ኪ.ሜ
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር (0912 263 311)(0910 770 359) (0982 517 409)ይጠይቁ።
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በአርሲ ዞን
የዴራ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-04
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 15ኛዉ የሥራ ቀን ከረፋዱ በ 4፡00 ሰአት
- Bid opening: 2026-09-04 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 15ኛዉ የሥራ ቀን ከረፋዱ በ 4፡30 ሰአት
- Region: Oromia
- Publishing entity: የዴራ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
- Bid bond: 10,000.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Bid document price: 300.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Published on: Addis Zemen (Aug 19, 2026)
- Posted at: 2026-08-19T09:11:35.000Z