Building Construction
መድን ፋና ትራንስፖርት ሎጂስቲክስና ንግድ አክስዮን ማህበር ለሚገነባው ለቅይጥ አገልግሎት የሚውል 3B+G+16 ሕንፃ ተቋራጭና አማካሪ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
አ/ማህበራችን መድን ፋና ትራንስፖርት ሎጂስቲክስና ንግድ አክስዮን ማህበር ለሚገነባው ለቅይጥ አገልግሎት የሚውል 3B+G+16 ሕንፃ ተቋራጭና አማካሪ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ለስራው አስፈላጊ የሆኑ መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ቀጥሎ ባሉት ተከታታይ ቀናት ከአክስዮን ማህበሩ ዋና መስሪያ ቤት የጨረታ ሰነዱን በመውሰድ መወዳደር ይችላሉ።
|
ተ.ቁ |
የፕሮጀክት ስም |
የተቋራጭ ደረጃ |
የአማካሪ ደረጃ |
የጨረታ ዋስትና ብር መጠን |
ጨረታው ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ |
|
|
ተቋራጭ |
አማካሪ |
|||||
|
1 |
3B+G+16 ቅይጥ ሕንፃ |
GC(ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ) ደረጃ 1 እና ደረጃ 2 እንዲሁም BC(የሕንጻ ሥራ ተቋራጭ) ደረጃ 1 እና 2 |
(የሕንጻ፣ የመሀንዲሶች፣ የአርክቴክቶች እና የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት) ደረጃ 1 እና (የመሀንዲሶች እና የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት) ደረጃ 2 |
800,000.00 |
50,000.00 |
120 ቀን |
1. ለስራው ንግድ ምዝገባና ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የታደሰ የንግድ እና የብቃት ማረጋገጫ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው ከአዲስ አበባ ግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ለ2018 ዓ.ም የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት እንዲሁም በ2018 ዓ.ም በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ክሊራንስ ከሚመለከተው አካል ማቅረብ የሚችሉ፣ በአቅራቢዎች ምዝገባ (Supplier list) የተመዘገቡ፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑና እና የግበር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው።
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ፋይናሻል አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ፣ ቴክኒካል አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ እያንዳንዱን ለብቻው በፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ስም በግልጽ በመጻፍና ማህተም በማድረግና የፕሮጀክቱን ስም በግልጽ በማስፈር በአንድ እናት ፖስታ አድርገው የድርጅቱን ማህተም እና የሚወዳደሩበትን ፕሮጀክት ስም በመጻፍ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3. የተቋራጭ ጨረታ፡- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለሀያ አንድ ተከታታይ የመቁጠሪያ ቀናት (Calendar Days) የሚቆይ ሲሆን በዚሁ ቀን 8፡00 ላይ ተዘግቶ 8፡30 ላይ ይከፈታል።
4. የአማካሪ ጨረታ፡- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስራ ስምንት ተከታታይ የመቁጠሪያ ቀናት (Calendar Days) የሚቆይ ሲሆን በዚሁ ቀን 8፡00 ላይ ተዘግቶ 8፡30 ላይ ይከፈታል።
5. ተጫራቾች ለ150 ቀን የሚቆይ ወይም የሚያገለግል የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond or Bid Security) በባንክ ትእዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) በመድን ፋና ትራንስፖርት ሎጂስቲክስና ንግድ አ.ማ ስም የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
6. ተጫራቾች ለጨረታ የሚያቀርቡት ዋጋ ወቅታዊ የገበያ ዋጋን ያላገናዘበ እጅግ የተጋነነ ዝቅተኛ ወይም ከፍተኛ የሚሰራውን ስራ ያላማከለ ከሆነ ተጫራቹ የዋጋ ትንታኔ (Cost Break Down) ከተገቢው መረጃ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል። ሆኖም የቀረበው ዋጋ ከስራው ጋር ያልተመጣጠነ (unbalanced Rate) ከሆነ ተጫራቹ ከውድድር ውጭ ይደረጋል።
7. ተጫራቾች የሚያስገቡት ፋይናንሻል ሰነድ ነጠላ ዋጋ ላይ ያልተፈረመበት ስርዝ ድልዝ (Unsigned rate correction) እና ፍሉድ መጠቀም (to use Correction fluid for rate correction) ከጨረታ ተወዳዳሪነት ያሰርዛል።
8. በስራ ዝርዝር ዋጋ ማቅረቢያ ላይ ያልተሞላ ነጠላ ዋጋ ከተገኘ ተጫራቹ ስራውን በነጻ እንደሚሰራው ይቆጠራል።
9. የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ጎተራ በሚገኘው በአክስዮን ማህበሩ ዋና መስሪያ ቤት ቢሮ ቁጥር 13 በመቅረብ ለተቋራጭ ብር 5000 (አምስት ሺህ)፣ ለአማካሪ ደግሞ ብር 2000 (ሁለት ሺህ) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ
10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ ተጠበቀ ነው።
ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09 55 85 83 89 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ
Tender details
- Deadline: 2026-09-08
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-09-08 14:30
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: መድን ፋና ትራንስፖርት ሎጂስቲክስና ንግድ አ.ማ
- Bid bond: ለተቋራጭ 800,000.00 እና ለአማካሪ 50,000.00
- Bid document price: ለተቋራጭ ብር 5000 (አምስት ሺህ)፣ ለአማካሪ ደግሞ ብር 2000 (ሁለት ሺህ)
- Published on: Reporter (Aug 19, 2026)
- Posted at: 2026-08-19T11:42:37.000Z