Cleaning and Janitorial Equipment and Service

የሸኖ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት እንደኛ ዙር ግዥ በሸኖ ከተማ ስር ላሉ ባለ በጀት መ/ቤቶች የተለያዩ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡- ግ/ጨ/ቁ 01/2019

የሸኖ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት እንደኛ ዙር ግዥ በሸኖ ከተማ ስር ላሉ ባለ በጀት መ/ቤቶች የተለያዩ፡

  • የጽህፈት መሳሪያ እና ቋሚ አላቂ የቢሮ እቃዎች
  • የጽዳት እቃዎች
  • የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
  • የመኪና ጎማዎች
  • የደንብ ልብስ
  • የተለያዩ የግንባታ እቃዎች
  • የኤሌክትሪክ መሳሪያዎችና ተዛማጅ እቃዎች
  • የተለያዩ የቢሮ ቋሚ እቃዎች፡- ወንብር፤ ጠረጴዛ እና የመሳሰሉትን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ በየስራ ዘርፉ የዘመኑን ግብር የከፈላችሁ፤ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላችሁ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ “VAT 15%” ተመዝጋቢ የሆናችሁ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር “TIN” ያላችሁ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር ዉስጥ የተመዘገቡ ለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በሸኖ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በግንባር በመቅረብ ዝርዝር መጠይቆችን የያዘውን ሰነድ በማይመለስ በብር 1000 በካሽ መግዛት ይችላሉ።

ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ በዝርዝር የተመለከተውን የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና በካሽ ወይም ሲፒኦ “CPO” ማስያዝ አለባቸው፡፡

ይህ ጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው ቀን በ8:00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ተወካዮች በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።

ማሳሰቢያ

  • ጨረታውን ያሸነፈ ድርጅት ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ውሉን ፈጽሞ እቃዎችን የማስገባት ግዴታ አለበት፡፡
  • መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ (አማራጭ) ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡ ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ በሚወስደው መንገድ 78 ኪሎ ሜትር ሸኖ ከተማ ነው::

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0910 093 362 በመደወል ጠይቆ መረዳት ይቻላል።

በኦሮሚያ ክልል የሸኖ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-05
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ይህ ጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከቀኑ በ8:00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-05 14:30
  • Bid opening (note): ይህ ጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Sheno City Administration Finance & Economic Development Office
  • Bid document price: 1,000.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 19, 2026)
  • Posted at: 2026-08-19T12:31:21.000Z
← Back to all tenders