Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በቦሌ ከ/ከተማ ወረዳ 12 ውስጥ የሚገኘው የቦሌ ቡልቡላ 2ኛ ደ/ት/ቤት ለት/ቤቱ አገልግሎት የተለያዩ ዕቃዎችን ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

መለያ ቁጥር 001/2018

በቦሌ ከ/ከተማ ወረዳ 12 ውስጥ የሚገኘው የቦሌ ቡልቡላ 2ኛ ደ/ት/ቤት ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውል ቋሚ ዕቃዎች እና አላቂ ዕቃ ሎት1. የጽህፈት መሣሪያዎች፣ ሎት2. የጽዳት መገልገያዎች፣ ሎት 3. የኤሌክትሮኒክ ዕቃዎችን፣ ሎት 4 ፈርኒቸር፣ ሎት 5. የህንፃ መሳሪያ፣ ሎት 6. የደንብ ልብስ፣ ሎት7. የስፖርት ማቴሪያል፣ ሎት8. መፃህፍት ሎት.9 ጭነት፣ ሎት 10. ትራንስፖርት ስራዎች፣ ሎት 11. ጭነት ፣ ሎት 12. ትራንስፖርት ፣ ሎት 13. ውሃና ቆሎ፣ ሎት 14. መፅሀፍ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ስለሆነም፡-

1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያስው፣ቫት ተመዝጋቢ የሆነ ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል እንዲሁም በገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገቡ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።

2. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የጨረታውን ዝርዝር ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመከፈል መግዛት አለባቸው።

3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ስሚወዳደሩበት ዕቃ በዕያንዳንዱ ሎት1. የፅህፈት 12,500 ሎት2. የፅዳት 7,500 ሎት 3. ኤሌክትሮኒክስ 15,000 ሎት 4. ፈርኒቸር 15,000 ሎት5. የህንፃ መሳሪያ 2,000 ሎት 6 ደንብ ልብስ 8,000 ሎት 7. የስፖርት ማቴሪያል 7,500 ሎት 8. ህትመት 1,000 ሎት 9. ጥገና 1,000 ሎት 10. ልብስ ስፌት 1,000 ሎት 11. ጭነት 4,000 ሎት 12. ትራንስፖርት 4,000 ሎት 13. ውሃና ቆሎ 2,000 ሎት 14. መፅሐፍ 2,000 በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ CPO ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

4. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ ለማስገባት በሚመጣበት ጊዜ ሳምፕል ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች አብሮ ማስገባት ሳምፕል ማምጣት ለማይችል በፎቶ አብሮ ማስገባት ስስበት። ሳምፕል ያላቀረበ ተጫራች የጨረታውን ሰነድ የማናወዳድር መሆኑን በቅድሚያ ት/ቤቱ ይገልፃል።

5. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውን እና ኮፒውን በታሸገ ኤንቨሎፕ የድርጅቱን ማህተብ በማድረግና በፊርማ በማረጋገጥ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2:30 -11፡00 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 04 በመቅረብ በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በማግስቱ ማለትም በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ታሽጎ በዚሁ እለት በ4፡30 ሰዓት በቦሌ ቡልቡላ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በቢሮ ቁጥር 04 ይከፈታል።

6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ሲቀመጥ ቫትን ያካተተ መሆኑን መግለፅ አለበት።

7. በጨረታው አሸናፊ የሆነ አቅራቢ የውል ማስከበሪያ የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ (10%) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ CPO ማስያዝ ይኖርበታል።

8. ት/ቤቱ አሸናፊው ተጫራች ያቀረበው ዋጋ ሳይቀይር 20% መቀነስ ወይም መጨመር ይችላል።

9. አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃ ውል ከተፈራረመበት ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ እስከ ት/ቤቱ ንብረት ክፍል በራሱ ትራንስፖርት ማድረስ ይኖርበታል።

10. ት/ቤቱ በጨረታው የተሻለ ዘዴ ወይም አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

11. በማስታወቂያ ላይ ያልተገለፁ ነገሮች ቢኖሩም በግዥ መመሪያ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል።

12. ሳንፕል ማቅረብ ያልቻለ ተወዳዳሪ ከውድድሩ ውጪ መሆኑን እናሳስባለን።

አድራሻ፡- ቦሌ ክ/ከ/ወረዳ 12 ቦሌ ቡልቡላ 2ኛ ደ/ት/ቤት ዳሮን ባርና ሬስቶራንስ ጀርባ

ለበለጠ መረጃ፡- 011 440 5879

የቦሌ ቡልቡላ 2ኛ/ደ/ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-31
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-31 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Bole Bulbula Secondary School
  • Buyer address: ቦሌ ክ/ከ/ቡልቡላ ኮንዶሚኒየም ብሎክ 154 አጠገብ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 19, 2026)
  • Posted at: 2026-08-19T13:31:14.000Z
← Back to all tenders