Cleaning and Janitorial Equipment and Service
በደ/ም/ኢት/ሕ/ክልል መንግሥት የኮንታ ዞን ፋ/መምሪያ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት እና ግንባታ ለማስገንባት ይፈልጋል
More tags
Description
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ም /ኢት/ ሕ/ክልል መንግሥት የኮንታ ዞን ፋ/መምሪያ የተለያዩ ሴክተር መ/ቤት በሎት1፣ ጽ/መሣሪያ በሎት2፣ ኤሌክትሮኒክስ ሎት3፣ ደንብ ልብስ ሎት4፣ የጽዳት ዕቃዎች ሎት5፣ ፈርኒቸር ሎት6፣ ሞተር ሳይክል ሎት7፣ የመኪና ጥገና የእጅ ዋጋ በሎት 8፣ የኮንታ ኮይሻ ወረዳ ለሚገነባው 5 የደሃ ደሃ ቤት ግንባታ፣ ሎት9፣ ባከ ሰዳ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ሶላር አቅርቦት ከነተከላ እና በሎት 10፣ ለቁታ ሞዴል ገጠር መንደር ሶላር ግዥ ከነተከላ በ2019 በጀት ዓመት በካፒታልና በመደበኛ በጀት ሲሆን ሎት 8 ደረጃ 9 GC/BC በአካባቢ የተደራጁ ማህበራት ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማስገንባት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት ለመጫረት የምትፈልጉ፡-
1. በበጀት ዓመት የታደሰ ንግድ ፍቃድ 2/ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት 3/ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር 4/ በመንግስት ግዥ ላይ አቅራቢነት ሰርተፍኬት 5/ተጨማሪ እሴት ታክስ 6/ የታደስ ግንባታ ፍቃድ ሰርተፊኬት 7/ ከግብር ዕዳ ነፃ ስለመሆን የሚገልጽ ታክስ ክሊራንስ እና 8/መልካም ሥራ አፈፃፀም በየዘርፉ የ2016 ወይም 2017 ወይም 2018 ዓ.ም ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችል፤ በ2019 በጀት ዓመት ፍቃድ ያወጡትን የመልካም ሥራ አፈፃፀም አይመለከትም።
2. ተጫራቾች ለሎት1፣ ሎት2፣ ሎት3፣ ሎት4፣ ሎት5፣ ሎት6፣ ሎት7፣ ሎት9 እና ሎት 10 እያንዳንዱ የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ብር 70.000 /ሰባ ሺህ/ ብር ብቻ ስሆን ለሎት8፣ የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ብር 150,000(አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ) ብር ብቻ ከታወቀ ባንክ በCPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች ሎት8፣ ሎት9 እና ሎት10 ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ 15ኛው ቀን ድረስ እና ለሎት1፣ ሎት2፣ ሎት 3፣ሎት4፣ ሎት5፣ሎት6፣ሎት7 21ኛ ቀን ድረስ በኮንታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የጨረታ ዶክመንት በመግዛት እና በዋጋ ማቅረቢያ በመሙላት ቴክኒካል ኦርጅናል1 እና ኮፒ 1 ፣ፋይናንሻል ኦርጂናል እና ኮፒ2 በድምሩ 5 ፖስታ የድርጅታችሁን ማህተም በማድረግ የጨረታ ፖስታ በማሸግ በኮንታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
4. በተራ ቁጥር9 መሠረት ሎት8፣ ሎት 9 ፣ ሎት 10 የጨረታ ሳጥን ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛው ቀን እና ሎት1፣ ሎት2፣ ሎት 3 ፣ ሎት4 ፤ ሎት 5 ፣ ሎት6፣ ሎት7 የጨረታ ሣጥን የሚከፈተው 22ኛ ቀን የመንግሥት ሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ በዕለት በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮንታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ይከፈታል።
5. ተጫራቾች የጨረታ ዶክመንት የማይመለስ 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ከኮንታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 9 መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡
6. ተጫራቾች ጨረታውን አሸንፈው ውል በመግባት ንብረቱን ሎት1፣ሎት2፣ ሎት3፤ሎት4፣ ሎት5፣ ሎት6፣ ሎት7 እስከ ኮንታ ዞን ፋይናንሰ መምሪያ አመያ ከተማ እና፤ሎት9 እና ሎት10 የሚተከልበት ቦታ ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
7. በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ ላይ የተገለፁ መስፈርቶችን የማያሟላ ተጫራች ለቴክኒካል ግምገማ እንዲቀርብ አይደረግም፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
የበለጠ መረጃ በቢሮ ስልክ ቁጥር፡- 047 227 0007 /0917 388 691/ 0917 161 785/0935 138 008
አድራሻችን፡- በደ/ም/ኢ/ህ ክልል ኮንታ ዞን ፋ/መምሪያ ከጅማ ከተማ በስተ ደቡብ 102 ኪ/ሜ በአመያ ከተማ ይገኛል፡፡
በደ/ም /ኢት/ ሕ/ክልል መንግሥት የኮንታ ዞን ፋ/መምሪያ
Tender details
- Deadline: 2026-09-09
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-09-09 14:30
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
- Region: South West Ethiopia Region
- Publishing entity: Konta Zone Finance and Economic Development Command
- Buyer address: በደ/ም/ኢ/ህ/ክልል ኮንታ ዞን ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ከጅማ ከተማ በስተደቡብ 102 ኪ.ሜ በአመያ ከተማ ይገኛል
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 19, 2026)
- Posted at: 2026-08-19T14:11:41.000Z