Cleaning and Janitorial Equipment and Service
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የዶዶላ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉትን የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የዶዶላ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉትን
1. አላቂ የጽህፈት መሳሪያ
2. የጽዳት ዕቃዎች
3. ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች
4. የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች
5. የሰራተኞች የደንብ ልብስ
6. ሞተር ሳይክሎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡
1. ተወዳዳሪዎች የዘመኑን የመንግሥት ግብር ማጠናቀቃቸውን የሚገልጽ ማስረጃና ንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ መሆን አለባቸው፡፡
2. ተወዳዳሪዎች በዕቃ አቅራቢነት ዝርዝር መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ከሚመለከተው አካል ማቅረብ የሚችሉና እንዲሁም የተእታ ተጠቃሚ መሆናቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን ነምበር) ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
4. ተወዳዳሪዎች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 (ሃያ አንድ) ተከታታይ የሥራ ቀናት ሊወዳደሩበት የሚችሉትን ዕቃዎች ለእያንዳንዳቸው የጨረታ ሰነድ በማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ) ከዶዶላ ከተማ አስ/ ገቢዎች ጽ/ቤት መግዛት ይችላሉ፡፡
5. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ፖስታው ታሽጎ በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ ሆኖ በዚሁ ዕለት በ4፡30 ሰዓት ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ባይገኙም ጨረታውን ከመከፈት አያግድም፡፡ዕለቱ በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
6. ተወዳዳሪዎች የጨረታውን ሰነድ አንድ ኦርጂናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ በአንድ እናት ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
7. ተጫራቾች /ተወዳዳሪዎች/ ተወዳድረው አሸናፊ በሆኑበት ዕቃዎች እስከ መ/ቤቱ ድረስ በራሳቸው ማጓጓዣ ማድረስ ይጠበቅባቸዋል፡፡
8. ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉት አስፈላጊ የሆኑት ማስረጃዎችና ከላይ የተጠቀሱትን ዝርዝር ነገሮችን አሟልተው ሲገኙ ብቻ ይሆናል።
9. ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለጸላቸው በ5 ቀን ውስጥ ከመ/ቤቱ ጋር ውል መፈራረም ግዴታ አለባቸው፡፡
10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-6 ለተጠቀሱት ለእያንዳንዳቸው ብር % 1.5 ፐርሰንት በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
11. ተጫራቾች ውል በሚፈርሙበት ጊዜ አጠቃላይ ካሸነፉት ዕቃ ላይ 10 ፐርሰንት የጨረታ ማስከበሪያ በጽ/ቤቱ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
12. በዋጋ ማቅረቢያ ፎርም ላይ የቀረቡት የእቃዎች ብዛት በያንዳንዱ 25 ፐርሰንት ከፍና ዝቅ ሊል ይችላል፡፡
13. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ አድራሻ፣ ስም፣ ፊርማ ማህተምና ስልክ ቁጥር ማስፈር ይጠበቅባቸዋል፡፡
14. ተወዳዳሪዎች የሚያቀርቡት ማንኛውንም ዕቃ ጥራታቸው በኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ የተረጋገጠ መሆን አለባቸው፡፡
15. ተጫራቾች ያስገቡትን መረጃና ሰነድ የእኔ አይደለም ማለት አይችሉም፡፡
16. ተጫራቾች ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ ከሰነዳቸው ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡
17. ተወዳዳሪዎች በገዙት ሰነድ ላይ ያለ ምንም ስርዝ ድልዝ በተዘጋጀ ቦታ ላይ መሙላትና ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
18. ተጫራቾች ከዚህ በፊት ተወዳድረው ካሸነፉ በኋላ ዕቃውን ያላቀረቡ መወዳደር አይችሉም፡፡
19. ተጫራቾች ያሸነፉትን ዕቃ አጠናቀው ገቢ ሲያደርጉ ብቻ ክፍያ ይፈፀማል፡፡
20. መ/ቤቱ ናሙና እንዲቀርብባቸው ከሰነድ ጋር ተያይዞ የቀረቡትን ዕቃዎች የማምጣት ግዴታ አለባቸው፡፡
21. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
22. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥሮች 0911 492 949 እና 0913 447 850 ደውሎ ማረጋገጥ ይቻላል፡፡
የዶዶላ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-12
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 (ሃያ አንድ) ተከታታይ የሥራ ቀናት ቆይቶ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-12 10:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 (ሃያ አንድ) ተከታታይ የሥራ ቀናት ቆይቶ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: Dodola City Administration Finance and Economic Development Bureau
- Bid bond: 1.5% ለእያንዳንዳቸው
- Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዱ ሰነድ
- Published on: Addis Zemen (Aug 19, 2026)
- Posted at: 2026-08-19T14:23:45.000Z