Vehicle and Machinery Sale
አዲስ ባንክ አ.ማ. መኪና ለመሸጥ ይፈልጋል
More tags
Description
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ
አዲስ ባንክ አ.ማ. ለሰጠዉ ብድር በዋስትና የያዘዉን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 መሰረት በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት ማንኛዉም ተጫራች ሐራጁ በሚካሄድበት ቀንና ሰዓት ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ በመገኘት በጨረታዉ ተወዳድሮ ንብረቱን እንዲገዛ ተጋብዟል፡፡
|
የተበዳሪዉ ስም |
የንብረት አስያዥ ስም |
አበዳሪው ቅርንጫፍ |
ለጨረታ የቀረበዉ የመያዣ ንብረት አይነት እና ሞዴል |
የሰሌዳ ቁጥር |
የሞተር ቁጥር |
የሻንሲ ቁጥር |
የጨረታዉ መነሻ ዋጋ |
ጨረታዉ የሚከናወንበት ቦታ |
ጨረታዉ የሚከናወንበ ቀንና ሰዓት |
|
|
ግሪን ላንድ ኃ/የተ/የግ/ማህበር |
ግሪን ፊልድስ ኃ.የተ.የግ.ማህበር |
አብይ ቅርንጫፍ |
ተሸከርካሪ-ላንድ ክሩዘር (ሀርድ ቶፕ) ጃፓን ሰራሽ ቶዮታ፤ ማኑዋል የ08/2016 ምርት |
ኮድ 3-A40790 አ.አ |
1HZ-0860011 |
JTEEB71J407034476 |
7,315,000 |
የባንኩ መኪና ማቆያ በሚገኝበት አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 05 ቁስቋም ማርያም ቤተክርስቲያን ፍትለፊት |
ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 4.00-6.00 ሰዓት |
|
- ተጫራቾች የጨረታዉን መነሻ ዋጋ 25% በባንኩ የክፍያ ማዘዣ ሰነድ(cpo) አሰርቶ በጨረታዉ ቀን ጨረታው በሚካሄድበት ቦታ በመቅረብ ወይም ጥሬ ገንዘብ በማስያዝ መመዝገብ ይችላሉ፡፡
- ጨረታዉ በማስታወቂያዉ ላይ በተጠቀሰዉ ቀንና ሰዓት ባለዕዳዎቹ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸዉ፣ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸዉ፣ታዛቢዎች በተገኙበት፣የመያዣ ንብረቱ በሚገኝበት የሚካሄድ ይሆናል፡፡
- የጨረታዉ አሸናፊ ያሸነፈበትን ዋጋ ጨረታዉ ከተከናወነበት ማግስት ጀምሮ በሚቆጠር 15 ቀን ዉስጥ ለባንኩ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ በእነዚህ ቀናት ዉስጥ ካልከፈለ ግን ለጨረታ ያስያዘዉ ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታዉ ተሰርዞ ለሐራጅ የሚቀርብ ይሆናል፡፡ በጨረታዉ ተሳትፈዉ ላላሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ጥሬ ገንዘብ ወይም ሲፒኦ ወዲያኑ ተመላሽ ይደረግላቸኋል፡፡
- ኃ/የተ/የግል ማህበርን ወይም አክሲዮን ማህበርን ወክሎ መጫረት የሚፈልግ ሥራ አስኪያጅ ወይም ም/ሥራ አስኪያጅ የድርጅት የመመስረቻ ጽሑፍ እና መተዳደሪያ ደንብ ይዞ መቅረብ ያለበት ሲሆን የሥራ አስኪያጅ ወይም የም/ሥራ አስኪያጅ ለዉጥ ተደርጎ ከሆነ ይህንኑ የሚገልጽ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት ቃለ ጉባኤ ከመመስረቻ ጽሑፍ እና መተዳደሪያ ደንብ ጋር ይዞ መቅረብ አለበት፡፡
- የጨረታዉ አሸናፊ ለመንግስት የሚከፈለዉን አስፈላጊ ግብር እና ተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲሁም የሊዝ ክፍያ ይከፍላል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ የቀረበዉ ንብረት ያለበትን ሁኔታ በተመለከተ ከጨረታዉ ቀን በፊት ባሉ የስራ ቀናት እና ሰዓት በባንኩ አበዳሪ ቅርንጫፍ በመቅረብ በሚያዘጋጀዉ ፕሮግራም መሰረት ንብረቱ ያለበትን ሁኔታ መመልከት ይችላሉ፡፡
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
ለተጨማሪ መረጃ አዲስ ባንክ አ/ማ ሕግ አገልግሎት መምሪያ በስልክ ቁጥር 0115571934፣ አብይ ቅርንጫፍ 0118276004 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
አዲስ ባንክ አ.ማ.
Tender details
- Deadline: 2026-09-04
- Bid closing time: 12:00
- Bid opening: 2026-09-04 12:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Addis Bank S.C.
- Bid bond: 25%
- Published on: Reporter (Aug 19, 2026)
- Posted at: 2026-08-19T14:25:58.000Z