Construction Machinery
በሸገር ከተማ የመልካ ኖኖ ክ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ የመንገድ ሥራ ማሽነሪዎች ዶዘር፣ ኤስካቫተር፣ ግሬድር፣ ሎደር፣ ሮለር፣ ደምፕ ትራክ፣ ሸዋር ትራክ፣ ሎቤድ እና የተለያዩ የፒካፕ መኪናዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል
Description
በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር፡ 001/2019
በሸገር ከተማ የመልካ ኖኖ ክ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ የመንገድ ሥራ ማሽነሪዎች ዶዘር፣ ኤሰክቨቴር፣ ግሬድር፣ ሎደር፣ ሮለር፣ ደምፕ ትራክ፣ ሸዋር ትራክ፣ ሎቤድ እና የተለያዩ የፒካፕ መኪናዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ስለሚፈልግ ህጋዊ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው የተጫራቾች መመሪያ መሠረት ጨረታውን እንድትካፈሉ ተጋብዘዋል፡፡
የጨረታ ዝርዝር ሁኔታዎች
የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከመልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺህ) በሲንቄ ባንክ በተከፈተው ሂሳብ ቁጥር 1054472341218 ገቢ በማድረግ ገንዘብ ገቢ የተደረገበትን የባንክ ስልፕ በመያዝ ወደ መልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት በመሄድ የገቢ ደረሰኝ በማስቆረጥ የጨረታ ሰነዱን ከመልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ክፍል መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
የተጫራቾ ግዴታዎች
1. በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለዚሁም ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
2. የንግድ ምስገባ ምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN No ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡
4. የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT ተመዝጋቢ መሆናቸውንና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡
5. በፌዴራል ገንዘብ ሚኒስቴር ወይም በኦሮሚያ ገንዘብ ቢሮ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡
6. ማንኛውም ተጫራች በባንክ የተመሰከረ የጨረታ ማስከበርያ CPO 250,000 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ) ብር ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ የሚችል፡፡
7. በማሽነሪ ኪራይ ላይ የሚሳተፍ ማንኛውም ተጫራች በሚያቀርባው ዋጋ ላይ የነዳጅ፤ የመኪና ቅባት፤ የጥገና፤ የሹፌርና የረዳት የውሎ አበል እና ሌሎች ተዛማች ወጭዎችን በተጫራቹ (በአከራይ) ድርጅት የሚሸፈን ይሆናል፡
8. ተጫራች ጨረታውን ካሸነፋ ቦኃላ ማሽነሪዎችን በራሱ ወጪ መልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ መስርያ ቤት ባዘጋጃው የልማት ቦታ (ሥራ የሚሠራበት ቦታ) ድረስ ማቅረብ የሚችል፡
9. ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ላይ የሚያቀርበው ማሽነሪ ወይም የፒካፕ መኪና ደረጃውን የጠበቃ ሆኖ የባለቤትነት ማስረጃ ወይም ሊብሬ ወይም ሕጋዊ የክራይ ውል አያይዞ ማቅረብ የሚችል፡
10. አሸናፊ ተጫራች የውል ማስከበርያ ዋስትና 10% ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት፡
11. ተጫራች የሚወዳደርበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በትክክል በማሙላት ኦርጅናልና ኮፒ በመለየት በፖስታ በታሽጋ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ተከታታይ የመንግስት የሥራ ቀናት ውስጥ በመልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ክፍል ለዚሁ ሥራ በተዘጋጃው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር ይችላል፡
12. ጨረታው በ16ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡
ማሳሰብያ: ጽ/ቤቱ የተሻላ አማራጭ ካገኛ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
መልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-05
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ተከታታይ የመንግስት የሥራ ቀናት ቆይቶ በ16ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-05 12:00
- Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ተከታታይ የመንግስት የሥራ ቀናት ቆይቶ በ16ኛው ቀን ጠዋት 4፡30 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: Sheger City Administration Melka Nono Sub-City Finance Office
- Bid bond: 250,000.00 ብር
- Bid document price: 1,000.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 19, 2026)
- Posted at: 2026-08-19T14:33:22.000Z