Building Construction
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት በትምህርት ጽ/ቤት አማካይነት ለሚያሰራው የደሳ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት አራት ክፍል (አንድ ብሎክ) ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Description
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ሀገር አቀፍ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
መለያ ቁጥር GGWW/0003/2019
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት በትምህርት ጽ/ቤት አማካይነት ለሚያሰራው የደሳ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት አራት ክፍል (አንድ ብሎክ) ስራ በግልጽ ጫረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች
1. የዘመኑን ንግድ ፈቃድ ያሳደሱ የቫትእና ቲን ነምበር ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡ የመወዳደሪያ ደረጃቸውም GC/BC ደረጃ 6 እና ከዛ በላይ የሆኑ ተቋራጮች።
2. ከገቢዎች መስሪያ ቤት የኦዲት ከሊራንስ ማምጣት የሚችሉ
3. ተወዳዳሪዎች የቫት 7.5% ተቀናሽ ለማድርግ ፍቃደኛ መሆን አለባቸው
4. በጫረታው ለመወዳዳር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች የሚገዙት ጫረታ ሰነዱን ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ የድርጀቱ ባለቤት መሆን አለባቸው እንዲሁም በወከልና ሰነዱን መውሰድና መወዳደር አይቻልም።
5. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 20ኛው ተከታታይ ቀናት እስከ 8፡00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ ብቻ በመከፈል የጨረታውን ሰነድ መሀል አምባ ገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
6. የጫረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ /200,000/ሁለት መቶ ሺህ/ ብር በገ/ጉ/ወ/ወ ፋይናንስ ፅ/ቤት ስም ማሰራት አለባቸው።
7. ተጫራቾች የጫረታውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመንት ሀ/ ለቴክኒካል ዶከመንት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ቴክኒካል በሚል በመለየት ለ/ ለፋይናንሻል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶኮፒ በማደረግ ፋይናንሻል በሚል በመለየት በሰም በማሸግ ከላይ በተጠቀሰው የጫረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ/ ከባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከቴክኒካል ኦርጅናል ዶክመንቱ ጋር በማድረግ በሰም በማሸግ ቴክኒካል ዶክመንት በሚል በመለየት ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20(ሀያ) ተከታታይ ቀናት መሀል አምባ የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በመምጣት ለጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
8. የጫረታው ሰነድ በ20ኛው ተከታታይ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይታሸጋል ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ከገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡-
1. በአፈፃፀም ምክንያት ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ድርጅቶች መወዳደር አይችሉም።
2. ተጫራቾች ተጫርተው ከሻነፉ በኃላ አገልግሎታቸው ጥራት ያለውና ቀልጣፋ ካልሆነ የውል ጊዜን የምናቋርጥ መሆነን እንገልፃለን።
3. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በአል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የስራ ቀን ይዘዋወራል።
4. ተወዳዳሪዎች ከአሸነፉ በኃላ ቅደመ ከፍያ ሳይጠይቁ ስራው መስራት የሚችሉ መሆን።
5. በወረዳው ውስጥ አንድም ፕሮጀክት የያዘ አካል መወዳደር አይችልም።
ለበለጠ መረጃ፡ የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ስልክ ቁጥር 0113 360 631/146 ይደውሉ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-07
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ20ኛው ተከታታይ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-07 14:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ20ኛው ተከታታይ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
- Region: Central Ethiopia
- Publishing entity: Gurage Zone Gedebano Gutazer Welene Woreda FEDB
- Bid bond: 200,000.00 ብር
- Bid document price: 400.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 19, 2026)
- Posted at: 2026-08-19T15:17:45.000Z