Stationery

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜናዊ ሲዳማ ዞን የወንዶ ገነት ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ እና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት የቢሮ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜናዊ ሲዳማ ዞን የወንዶ ገነት ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ እና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ለሴክተር መ/ቤቶች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን የቢሮ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  • 1. ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ
  • 2. ሎት 2 የጽዳት እቃዎች
  • 3. ሎት 3 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
  • 4. ሎት-4 የፈርኒቸር እቃዎች

በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ፡-

1. የታደሰ የዘርፉ ንግድ ስራ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እና የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው።

2. የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ በባንክ የተረጋገጠ ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) ለብቻ ከግዴታ ሰነዶች ጋር አሽገው ማስገባት ይኖርባቸዋል።

3. የጨረታ ሰነዱን በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ የእቃዎቹን ዋጋ መሙያ ሰነድ ፋይናንሽያል አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ ለብቻው በማሸግ እና እንዲሁም የግዴታ ሰነዶችን ከጨረታ ማስከበሪያው ጋር ለብቻው በአንድ ፖስታ ውስጥ በማድረግ በሁሉም ዶክመንት ላይ ህጋዊ የሆነ የድርጅቱን ማህተብ በማሳረፍ እና አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በመሙላት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት በየሎቱ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በወንዶ ገነት ከተማ ገቢዎች ቅ/ጽ/ቤት ከፍለው የከፈሉትን ደረሰኝ በማሳየት የጨረታ ዶክመንቱን ከወንዶ ገነት ከተማ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት መውሰድ ይችላል።

4. የጨረታው ሳጥኑ ጋዜጣው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጨምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የስራ ቀናት እስከ መጨረሻው ቀን 11፡30 ድረስ ሲሸጥ ይቆይ እና በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል።

5. በጨረታው ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ወይም ለመለየት አሻሚ ነገር መኖር የለበትም። ካለም ተጫራቹ ፓራፍ ማድረግ አለበት።

6. የወቅቱን ዋጋ ያላገናዘበ የጨረታ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ ከቀረቡም የወቅቱን ዋጋ ትንታኔ እንዲያቀርቡ ይደረጋል።

7. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸው እቃዎች እስከ ወንዶ ገነት ከተማ አስተዳደር ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ድረስ በራሳቸው ወጪ አጓጉዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

8. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በጨረታው አይገደድም።

ማሳሰቢያ፡- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜናዊ ሲዳማ ዞን የወንዶ ገነት ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ እና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት

ለበለጠ መረጃ
ስልክ ቁጥር 0916134401/ 0916046074 ደውስው መጠየቅ ይችላሉ።
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜናዊ ሲዳማ ዞን የወንዶ ገነት ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ እና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-08
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 4፡00
  • Bid opening: 2026-09-08 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 4፡30
  • Region: Sidama
  • Publishing entity: Wendo Genet City Administration FEDB
  • Bid bond: 20,000 (ሃያ ሺህ ብር)
  • Bid document price: 200.00 ብር በየሎቱ
  • Published on: Addis Zemen (Aug 21, 2026)
  • Posted at: 2026-08-21T10:03:19.000Z
← Back to all tenders