Stationery

የነገሌ አርሲ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የግዥ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2019

የነገሌ አርሲ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ለነጌሌ አርሲ ከተማ ለመንግስት መ/ቤቶች ለ2019 በጀት አመት በ1ኛ ዙር ግዥ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት አንድ(1) የተለያዩ የፕሪንተር ቀለሞች
  • ሎት ሁለት(2) አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች
  • ሎት ሶስት(3) የቢሮ የጽዳት እቃዎች
  • ሎት አራት(4) የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች
  • ሎት አምስት(5) ቋሚ የቢሮ እቃዎችን(ፍርኒቸሮች)
  • ሎት ስድስት(6) የቀላል እና ከባድ መኪና ጎማዎች
  • ሎት ሰባት(7) ሞተር ሳይክል
  • ሎት ስምንት(8) የደንብ ልብስ

ስለዚህ ዕጩ ተጫራቾች ሊያውቁት የሚገባቸው መመሪያ፡-

1. ተጫራቾች በዘርፉ የተመዘገቡ እና ሕጋዊ የሆነ የታደሰ የ2018/2019 ዓ.ም የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ እና የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት(TIN NO..) ያለቸው መሆን ይኖርባቸዋል።

2. ተጫራቾች የመንግሥት ግዥ ላይ ለመሳተፍ በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታክስ(VAT) የግብር ከፋይነት የተመዘገቡ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

4 መስሪያ ቤታችን የተጨማሪ እሴት ታክስ(VAT 15%) 50%ቱን ቆርጦ የሚያስቀር መሆኑን እናሳውቃለን።

5. እያንዳንዱ ተጫራች ከላይ በየሎቱ ለተዘረዘሩት እቃዎች በየሎቱ በተጠቀሰው መሰረት ለሚወዳደሩባቸው ሎቶች ብቻ ለብቻ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የኢትዮጵያ ብር 15,000.00(አስራ አምስት ሺህ) ከሚያቀርቧቸው ሰነዶች CPO ጋር ማስያዝ አለባቸው፤ አዲስ የማይክሮ ድርጅቶች ኦርጅናል የዋስትና ደብዳቤ በህጋዊነት ካደራጃቸው አካል ማቅረብ አለባቸው። የዋስትና ደብዳቤው የሚያገለግለው አዲስ ለተደራጁ ማይክሮዎች ብቻ መሆኑን ለማስገንዘብ እንወዳለን።

6. ተጫራቾች በሚያቀርቡአቸው ፖስታዎች ላይ የሚወዳደሩባቸውን ሎቶች ቁጥራቸውን እና አይነት መፃፍ ይጠበቅባቸዋል።

7. ተጫራቾች የእቃዎቹን ዝርዝር የያዘ ሰነድ በየሎቱ ከሎት 1 እስከ ሎት 8 ለየብቻ ወይንም በተናጠል የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 500.00(አምስት መቶ )ብር በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ የስራ ቀን 10(አስር) ቀናት አርሲነጌሌ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥና ንብረት አስተዳደር ስራ ሂደት ቀርበው መውሰድ ይችላሉ።

8. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በነጠላ ዋጋ መግለፅ እና በጥንቃቄ ቫትን (VAT) ጨምሮ በመሙላት ኦርጅናሉንና ኮፒውን በተለያየ በታሸጉ ፖስታዎች ውስጥ በማድረግ ማቅረብ አለባቸው።

9. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የመጫረቻ ሰነድ በታሸገ ኤንቬሎፕ ዋና እና ኮፒ በነጌሌ አርሲ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው (02/13/2018) ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በነጌሌ አርሲ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥና ንብረት አስተዳደር ስራ ሂደት ክፍል ይከፈታል፤ካልተገኙም ጨረታው አይደናቀፍም። ዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ ጨረታው በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።

10. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ፊርማቸውን ስማቸውንና አድራሻቸውን በግልጽ መጻፍ እና የድርጅታቸውን ማህተም ማሳረፍ ይኖርባቸዋል።

11. አሸናፊው አሸናፊነቱ ከታወቀበት ከ6ኛው ቀን ጀምሮ በ4 ቀናት ውስጥ በነጌሌ አርሲ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በመቅረብ ካሸነፈው ዕቃ ላይ አስር ፐርሰንት /10%/ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ የዕቃዎቹን ናሙና በመያዝ ውል መፈራረም ይኖርባቸዋል።

12. በተራ ቁጥር 11 ላይ በተጠቀሰው ቀን መሰረት ውል የማይፈጽም አሸናፊ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ በመሆን መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ መጠቀም ይችላል።

13. አሸናፊ አቅራቢዎች ውል ተፈራርመው እስከ 15/አስራ አምስት/ ቀን ከላይ በተገለጸው አድራሻ በራሳቸው መጓጓዣ ዕቃዎቹን ማስረከብ ይኖርባቸዋል።

14. በጨረታው ላይ የቀረበው ዋጋ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60(ለስልሳ) ቀናት ጸንቶ የሚቆይ ይሆናል።

15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ለተጨማሪ ማብራሪያ የነጌሌ አርሲ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በግንባር በመቅረብ ወደም

 በስልክ ቁጥር፡- 0916824985/0916044213 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
የነገሌ አርሲ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-07
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-09-07 10:30
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Arsi Negele Woreda Finance and Economic Development Bureau
  • Bid bond: 15,000.00 ብር በየሎቱ
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ
  • Published on: Addis Zemen (Aug 21, 2026)
  • Posted at: 2026-08-21T10:13:46.000Z
← Back to all tenders