Stationery
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር በምዕራብ አርሲ ዞን የነጌሌ አርሲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር በምዕራብ አርሲ ዞን የነጌሌ አርሲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳችን ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች በ1ኛ ዙር በ2019 በጀት ዓመት ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች
ማለትም፡-
- ጽህፈት መሳሪያዎች
- ኤሌክትሮኒክስ
- ፈርኒቸር
- የፅዳት ዕቃዎች
- የደንብ ልብሶችን
- መኪና የሞተር ሳይክል ጎማዎች
ከዚህ በታች በተገለጸው በግልጽ ጨረታ መስፈርት ድርጅቶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ተጫራቶች ከኢህ በታች ያለውን መስፈርት በመከተል ይህን ጨረታ እንድትሳተፉ ተጋብዘዋል፡፡
1. ተጫራቾች በጨረታው ለመካፈል በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸዉና የዘመኑን ግብር (2018) የከፈሉ እንድሁም የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውን ቫት ከፋይ የሆኑ Tin Number ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2. ማንኛውም ተጫራች ወደ ጨረታው ሂደት ከገባ በኃላ በሰነድ ላይ የተገለፁትን ማንኛውንም ሁኔታዎች ማሻሽል መቀየር እንድሁም ሀሳቤን ቀይራለው ማለት አይቻልም፡፡
3. ማንኛውም ዕጩ ተወዳደሪ የጨረታውን ሂደት ለመስተጓጓል ቢሞክር ከጨራተው ውጭ እንድሆን ተደርጎ ወደ ፊት በሚደረገው የመንግስት ግዥ ላይ እንደይሳተፍ የሚደረግ እና ያስየዘው የጫረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ የሚሆን ይሆናል፡፡
4. ማንኛውም ተጫራች በመንግስት ግዥ ለመሳተፍ እንዲችል የሚገልጽ ከህጋዊ አካል የተሰጠ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለበት፡፡
5. ተጫራቾች በሚሰሩበት የንግድ እና በንግድ ፍቃዳቸው ዘርፍ ብቻ ነው መወዳደር የሚችሉት።
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለያንዱዱ የግዥ መደብ ብር (15,000) አስራ አምስት ሺህ ብር ብቻ በባንክ የተረጋገጠ CPO ማቅረብ አለበት።
7. አሸናፊ ድርጅት ዕቃውን ጭነው እስከ መ/ቤታችን ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለበት ፡፡
8. ተጫራቾች ዕቃው የተሰራበትን/ የተመረተበትን ሀገርና የጥራት ደረጃ የመስራት አቅሙን እንዲሁም ሞዴሉንና የተመረተበት ዓ.ም መግለጽ አለባቸው ::
9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኮፒና ኦርጂናል በተለያዩ ፖስታ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው
10.ተጫራቾች የጨረታ ዋጋውን መሙላት ያላባቸው በተሸጠላቸው ሰነድ ላይ ብቻ መሆን አለበት፡፡ እንዲሁም ኢያንዳንዱ ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት፡፡ በራሳቸው ሰነድ ላይ የሚሞላ ለስራችን አመቺ ስለማይሆን ተቀባይነት የለውም ፡፡
11. ጽ/ቤታችን የሚያጫርታቸውን የአንዱ ዋጋ ስለሆነ አሸናፊውን የሚፈልገውን የዕቃ ብዛት ማዘዝ ይችላል።
12. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፤ ሙሉ አድራሻቸውን፣ ስልክ ቁጥራቸውንን ፋክስ ቁጥራቸውን በትክክል ጽፈው መፈረምና ማህተም ማድረግ አላባቸው ።
13. ተወዳዳሪዎች የሚሰጡት የጫረታ ዋጋው ጫርተው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ90 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡
14. መ/ቤቱ ጨረታውን ገምግሞ ለማሳለፍ ወይም ውድቅ ለማድረግ የሚጠቀምበት ዘዴ እንደ ዕቃው አይነት ወይም የምፈለገው አገልግሎትን መሰረት በማድረግ ጥራትን ወይም ዋጋን ከግንዛቤ በማስገባት ተወዳዳሪዎችን አሸናፊ ወይም ውድቅ የምደረግ ሲሆን ሁለት እኩል ዋጋ ቢያቀርቡ በብዘት ላሸነፈው የሚሰጥ ይሆናል፡፡
15. ሰነዱ ለሽያጭ የሚቆይበት ቀን ከ 15/12/2018 እስከ 29/12/2018 ሲሆን ጨረተዉ የሚከፈተው በ 02/13/2018 ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ላይ ሳጥኑ ተዘግቶ ተጫራቹ ወይም ህጋዊ ወኪል በተገኘበት በዚው እለት 4:00 ሰዓት በነጌሌ አርሲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ውስጥ በይፋ ይከፈታል፡፡
16. የጨረታ ሰነዱ ዝርዝር በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በነጌሌ አርሲ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት ሰነድ ሺያጭ በማይመለስ ብር (500) አምስት መቶ ብር ብቻ ከነጌሌ አርሊ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት በባንክ መደበኛ ሂሳብ ቁጥር 1000026657028 በኢትዮጽያ ንግድ ባንክ ገቢ በማድረግ ስሊፕ በመያዝ ሰነዱን መግዛት የሚቻል ስሆን ተወዳዳር ድርጅቶች ሰነድ ከገዙበት ቀን ጀምሮ በተዘጋጀለት የጨረታ ሳጥን ውስጥ በስራ ሰዓት የሰነዱን ሽያጭ እስከሚያበቃበት ቀን ድረስ ማስገባት ይችላል፡፡
17. የጨረታው ውል ከጨረታ ስነድ ጋር ስለሚሽጥ በውል መሰረት ጨረታውን ያሸነፈው ድርጅቶች ለውሉ ተገዥ መሆን አለበት።
18. ጽ/ቤቱ የተሸላ መንገድ ከገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
19. አሸናፊ ድርጅቶች ካሸነፉ ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 10% የውል ማስከበሪያ በመያዝ ውል መግባት ይኖርባቸዋል፡፡
ለበለጠ መረጃ:- 0916139200/0911065757 /0913436641/ 0949420689
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር በምዕራብ አርሲ ዞን የነጌሌ አርሲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-07
- Bid closing time: 09:30
- Bid opening: 2026-09-07 10:00
- Region: Oromia
- Publishing entity: West Arsi Zone Negele Arsi Woreda FEDB
- Bid bond: 15,000.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Aug 21, 2026)
- Posted at: 2026-08-21T10:43:42.000Z