Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 አስተዳደር ለሚ አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ልዩ ልዩ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 አስተዳደር ለሚ አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በ2019 በጀት ዓመት የ1ኛ ዙር ጥቅል ግዥ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የጨረታ ማስታወቂያ ቁ ነሐሴ/2018

ተ.ቁ

የዕቃ ዝርዝር

የጨረታ ማስከበሪያ

ሎት 1

የደንብ ልብስ

10,000.00

ሎት 2

አላቂ የቢሮ እቃ

8,000.00

ሎት 3

ህትመት

3,000.00

ሎት 4

የህክምና ዕቃዎች

3,000.00

ሎት 5

አላቂ የትምህርት ዕቃዎች

6,000.00

ሎት 6

የፅዳት ዕቃ

10,000.00

ሎት 7

ልዩ ልዩ መሳሪያ ግዥ

3,000.00

ሎት 8

የህንፃ ቁሳቁስ እና ተገጣጣሚ መግዣ

6,000.00

ሎት 9

የማሽነሪ ጥገና

4,000.00

ሎት 10

ኤሌክትሮኒክ

10,000.00

ሎት 11

ፈርኒቸር

10,000.00

ሎት 12

የጭነት አገልግሎት

3,000.00

ሎት 13

የህንፃ ቁሳቁስና ተገጣጣሚ

4,000.00

ስለሆነም መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

1. ሀጋዊ የሆነና የታደሰ የንግድ ፈቃድ እንዲሁም የግብር መለያ ቁጥር (TIN NO) ሊኖራቸውና ሊያቀርቡ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።

2. ለሚያቀርቡት ዕቃ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ሊሆኑ ይገባቸዋል።

3. በጨረታው ለመሳተፍ በአቅራቢዎች ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ እና የተጫራቾች የምስክር ወረቀት ያላቸው ሊሆኑ ይገባል።

4. ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 6 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከዋጋ ማቅረቢያ ኦርጅናል ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር ከላይ የተዘረዘሩት እቃዎች ለእያንዳንዳቸዉ የዋጋ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በለሚ አፀደ ህፃናት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ግዥና ን/አስ/ደ/የስ/ ሂደት ቢሮ ድረስ በመቅረብ መግዛትና መጫረት ይችላሉ።

7. ተጫራቾች ዋጋ የሞሉበትን ሰነድ ኮፒ በማድረግ ኦርጅናልና ኮፒ ብለው በመለየትና በ2 ፖስታ በማሸግ እንዲሁም የተጠቀሱትን ማስረጃዎች አሟልተው በለሚ አፀደ ህፃናት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ግዥና ን/አስ/ደ/የስ/ ሂደት ቢሮ ውስጥ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ 10ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

8. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል። ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በቀኑ ባይገኙም ጨረታው የሚከፈት ይሆናል።

9. በጨረታ አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ

10. መስሪያ ቤቱ የሚገዛው እቃ ላይ 20% መጨመር እና መቀነስ ይችላል።

11. ከት/ቤቱ ጋር የግዥ ውል ስምምነት መያዝ ይኖርባቸዋል።

12. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

13. ተጫራቾች ከመከፈቱ በፊት ሁሉም ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃ ሳምኘል ሲያቀርቡ ምንም አይነት የድርጅቱን ማንነት የሚገልጽ ምልክት መኖር የለበትም።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 667 7635 -ወይም በአካል ለሚ አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ሰሚት ኮንደሚኒየም 3ኛ በር ገባ ብሎ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ በ ትንሽ ወረድ ብሎ ፋይናንስ ግዥና ን/አስ/ደ/የስ/ሂደት በመቅረብ መጠየቅ ይቻላል።

የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 አስተዳደር ለሚ አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-01
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-02 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Lemi Kindergarten and Elementary School
  • Buyer address: ሰሚት ኮንደሚኒየም 3ኛ በር ገባ ብሎ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ትንሽ ወረድ ብሎ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/
  • Published on: Addis Zemen (Aug 21, 2026)
  • Posted at: 2026-08-21T11:05:23.000Z
← Back to all tenders