Stationery
የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ መፈጸም ይፈልጋል
Description
የብሄራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በ2019 በጀት ዓመት የሚከተሉትን ግዥዎች በግልጽ ጨረታ አገልግሎት አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም፡- በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ሰነድ ጋር፡
- በዘመኑ የታደሰ እና በዘርፉ አግባብነት ያለው ህጋዊ ንግድ ፈቃድ፣
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበት ሰርተፍኬት፤
- በአቅራቢዎች ዝርዝር ላይ የተመዘገቡበትን የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ፣ የግብር ክሊራንስ ደብደቤ ከገቢዎች ማቅረብ የሚችሉ ሆኖ
|
የሎት ቁጥር |
የግዥ አገልግሎት ዓይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
ሠነድ ግዥ |
ጨረታው የሚቆይበት ቀን፤ ወር፤ዓ/ም ሰዓት |
|
|
የሚታሸግበት |
የሚከፈትበት |
||||
|
01 |
የሴቶች የውበት ሳሎን አገልግሎት |
20,000 |
300 |
25/12/2018 ዓ/ም 4:00 |
25/12/2018 ዓ/ም 4:30 |
|
02 |
የጽህፈት መሳሪያ |
20,000 |
300 |
||
|
03 |
ሻይ እና ቡና አገልግሎት |
20,000 |
300 |
||
|
04 |
የተማሪዎች ካፊቴሪያ እና ሪስቶራንት |
100,000 |
300 |
||
|
05 |
የመምህራን ካፊቴሪያ እና ሪስቶራንት |
100,000 |
300 |
||
|
06 |
Mini super market |
100,000 |
300 |
||
|
07 |
ሸቀጣ ሸቀጥ ሱቅ |
100,000 |
300 |
||
|
08 |
ካፊቴሪያ እና ጁሳጁስ አገልግሎት |
50,000 |
300 |
||
|
09 |
የወንዶች የውበት ሳሎን |
20,000 |
300 |
||
|
10 |
የመዝናኛ አገልግሎት/ pool,Table tense |
20,000 |
300 |
||
|
11 |
ኮስሞቲክስ |
20,000 |
300 |
||
1. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ከዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ኢንትርፕራይዝ የገቢ ልማት ሕንፃ ቁጥር 304 ክፍል 154 በመቅረብ በተጠቀሱ የስራ ቀናት በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የገቢ ልማት ኢንትርፕራይዝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000510745028 ገቢ ያደረጉትን የባንክ ደረሰኝ ኮፒ በመያዝ ወይም በዩኒቨርሲቲ ፋይናንስ በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፤
2. ተጫራቾቹ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አባሪ አድርገው በተሰጠው ስፔሲፊኬሽን ላይ በመሙላትና የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ በሁሉም ገጾች ላይ በማሳረፍ 1(አንድ) ኦርጅናልና 2 (ሁለት) ኮፒ በማድረግ ግዥ ሥራ አስፈጸሚ ቢሮ ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፤
3. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ባንክ ጋራንቲ በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ስም አዘጋጅተው ለብቻው በፖስታ በማሸግ ከኦርጅናል ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
4. የጨረታው ውጤት ጨረታው ተገምግሞ እንዳለቀ በደብዳቤ፣ ወይም በውስጥ ማስታወቂያ የሚገለጽ ይሆናል፤
5. ማንኛውም ተጫራች በውል ውስጥ የተካተቱትን ህጎች ማክበር አለበት፤
6. ዩኒቨርሲቲው የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጨማሪ ማስረጃ ቢያስፈልግ በስልክ ቁጥር 0996 893 024 / 0910 456 434 / 0968 705 245 ደውሎ ማግኘት ይቻላል።
ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ
ሆሳዕና
Tender details
- Deadline: 2026-08-31
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-08-31 10:30
- Region: Central Ethiopia
- Publishing entity: Wachemo University
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 300.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Published on: Addis Zemen (Aug 21, 2026)
- Posted at: 2026-08-21T11:21:47.000Z