Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን የጨንቻ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ለጨንቻ ዙሪያ ወረዳ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን የጨንቻ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ለጨንቻ ዙሪያ ወረዳ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የተለያዩ አላቂ የጽሕፈት መሣሪያዎችን፣ የጽዳት ዕቃዎችን፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ የሕንፃ መሣሪያ ፈርኒቸሮች፣ የቤትና ቢሮ ቋሚ ዕቃዎችን፣ የፋብሪካ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የምታሟሉ ነጋዴዎች መወዳደር ትችላላችሁ።

1. በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው/ያላትና የዘመኑን ግብር የከፈሉበት የታደሰ መረጃ ማቅረብ የምችሉ

2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው/ያላት

3. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው/ያላት

4. የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ

5. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስከር ወረቀት ያለው/ያላት

6. ቫት በዋጋ ማቅረቢያ ላይ ካልተለገፀ እንደተገለፀ ተደርጎ ይወሰዳል

7. ተጫራቾች የቴከኒክና ፋይናንሻል ሰነድ አንድ (1) ኦርጅናልና አንድ (1) ኮፒ ጋር ማቅረብ አለባቸው፣ በእያንዳንዱ ጨረታ ሰነድ ላይ አድራሻ ተጽፎ ፊርማና የድርጅቱ ማህተም ተደርጎ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው።

8. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፋቸውን ዕቃዎች በራሱ ትራንስፖርት ወጪ ወደ ጨንቻ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት ማቅረብ ይኖርበታል።

9. ተጫራቾች የጨረታው ማስከበሪያ /Bid bond /20,000/ ሀያ ሺህ ብር /በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡ ፡በጥሬ ገንዘብ የማንቀበል መሆኑን እናሳስባለን።

10. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ የሚቆየው በጨረታ ያሸነፉትን ዕቃ ሙሉ በሙሉ እስኪያቀርቡ ድረስ ነው።

11. የጨረታውን ሰነድ ጨንቻ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 25 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ/ብር በጨንቻ ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ባ/ቅ/ጽ/ቤት በመክፈል መግዛት የሚችል /የምትችል መሆኑን እንገልጻለን።

12. ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ለ15 በሥራ ቀናት አየር ላይ ይውላል።

13. የጨረታው ሳጥን የሚታሸግበትና የሚከፈትበት ቀን በ16ኛው የሥራ ቀን ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቦታ ይከፈታል። ነገር ግን 16ተኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ቀጣይ በሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።

14. የአሸናፊ ድርጅት ውል ለመግባት ስመጣ የውል ማስከበሪያ ያሸነፈበት ዋጋ 10% CPO ማቅረብ የሚችል /የምትችል መሆን አለባቸው።

15 በጨረታ ሰነድ ላይ የተገለጸው ዋጋ ከውል ጊዜ ጀምሮ ለ 60 /ስልሳ/ ቀናት የፀና ይሆናል።

ማሳሰቢያ፡-

  • መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • በአንዱ ዋጋ ላይ ዋጋ ተንተርሶ መጫረት አይፈቀድም።
  • የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም።
  • ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 09 44 70 86 56 / 09 16 34 53 59

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን የጨንቻ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-08
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-08 14:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
  • Region: South Ethiopia Regional State
  • Publishing entity: Chencha Zuria Woreda FEDB
  • Bid bond: 20,000.00 ብር
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 21, 2026)
  • Posted at: 2026-08-21T11:35:21.000Z
← Back to all tenders