Cleaning and Janitorial Equipment and Service
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ-7 ፋይናንስ ጽ/ቤት በ209 በጀት አመት 1ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ቁጥር ግ/ጨ/ቁ 001/2019
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ-7 ፋይናንስ ጽ/ቤት በ209 በጀት አመት 1ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ ሎት-1 ግዥ አላቂ የጽህፈት እቃዎች ፤ ሎት-2 የጽዳት እቃዎች፤ ሎት 3 የደንብ ልብስ፤ ሎት 4 ህትመት አገልግሎት፤ ሎት 5 ኮምፒውተር ጥገና፤ ፤ሎት 6 ድንኳን፤ዲኮር ሞንታርቦ፤ሎት 7 መኪና ኪራይ፤ሎት 8 የኃላፊ መስተንግዶ፤ሎት 9 ደንብ ልብስ ስፌት፤ ሎት 10 ኤሌክትሮኒክስ ግዥ፤ሎት 11 የመኪና ጎማ ፤ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም ከዚህ በታች ያለውን መስፈረት የምታሟሉ አመልካቾች መወዳደር ትችላላችሁ።
1, በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድና የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የቫት / VAT/ ተመዝጋቢ የሆናችሁ
2. ተጫራጮች ለሚጫረቱባቸው እቃዎች በሙሉ ናሙና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። ናሙና ማቅረብ ለማይቻልባቸው እቃዎች ብቻ በፎቶ የተደገፈ መሆን አለበት ናሙናዎቹንም ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ማስገባት አለባቸው። ያስገቧቸውን ናሙናዎች እስከ ስድስት /6/ ወር ድረስ መልሰው ካልወሰዱ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
3. የመንግስት ግዥ አስተዳደር የግዥ አቅራቢነት ተመዝጋቢ መሆንይኖርባቸዋል።
4. አንዱ በሌላው ዋጋ ላይ ተተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከታች በሰንጠረዡ በእያንዳዱ ሎት ለየብቻ መሰረት በባንክ በተረጋገጠው ሲ.ፒ.ኦ /CPO/ ወይም ባንክ ጋራንቲ ብቻ ማስያዝ አለባቸው። ሲ.ፒ.ኦ /CPO/ የባንክ ጋራንቲ ከኦርጂናል ሰነድ ጋር ተያየይዞ መቅረብ አለበት፡፤
|
ተ.ቁ |
የጨረታ አይነት |
የሎት ዝርዝር |
ማስያዝ ያለባቸው የሲ.ፒ.ኦ የብር መጠን |
|
1 |
አላቂ የጽህፈት እቃዎች |
ሎት-1 |
40,000.00 |
|
2 |
የጽዳት እቃዎች |
ሎት-2 |
50,000.00 |
|
3 |
የደንብ ልብስ |
ሎት-3 |
60,000.00 |
|
4 |
ህትመት አገልግሎት |
ሎት 4 |
10,000.00 |
|
5 |
ኮምፒውተር ጥገና |
ሎት-5 |
10,000.00 |
|
6 |
ድንኳን ፤ዲኮር ፤ ሞንታርቦ |
ሎት 6 |
5,000.00 |
|
7 |
የመኪና ኪራይ |
ሎት 7 |
10,000.00 |
|
8 |
የኃላፊ መስተንግዶ |
ሎት 8 |
4,000.00 |
|
9 |
ደንብ ልብስ ስፌት |
ሎት 9 |
3,000.00 |
|
10 |
ኤሌክትሮኒክስ ግዥ |
ሎት-10 |
10,000.00 |
|
11 |
የመኪና ጎማ |
ሎት 11 |
20,000.00 |
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ድረስ በመንግስት የስራ ሰዓት ለእያንዳንዱ የጨረታ አይነቶች በሎት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ዋጋ 300.00(ሶስት መቶ ብር በመክፈል በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን የቢሮ ቁጥር 15 በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
7. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ልዩ አስተያየት የሚደረግላቸው እራሳቸው ባመረቱት ምርት ላይ ብቻ ሲሆን ከዚህ ውጪ እደማንኛውም ተጫራች የሚታዩ ይሆናል፡፤ ከተደራጁበት ለወረዳችን መደራጀታቸውን የሚገልጽ እና አምራች ለሆኑት ብቻ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።
8. ተጫራቾች ሁሉንም የጨረታ ሰነዱን በመሙላት ኦርጂናል እና ኮፒውን ለየብቻ ታሽጎ በሚመለከተው ሀላፊ ተፈርሞ እና የድርጅቱን ማህተም ያረፈበት ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ዋጋ ሲሞሉም የቫት/VAT/ ዋጋን ጨምሮ ማካተት አለበት። ነገር ግን ለአገልግሎት ግዥ ለሆኑት ቲ.ኦ.ቲ ተመዝጋቢ ቢሆኑም መወዳደር ይችላሉ።
9. ጽ/ቤቱ የሚገዛቸው ግዥዎች ከውል በፊት የእቃውን ብዛት በ20% መጨመርም ሆነ መቀነስ ይችላል፡፤
10. ተጫራቾች ባሸነፉት አጠቃላይ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
11, አሸናፊ ድርጅቶች ያሸነፏቸውን እቃዎች በውላቸው መሰረት ሙሉ በሙሉ በራሱ ትራንስፖርት ጽ/ቤት ድርስ ንብረት ክፍል ገቢ የማድረግ ግዴታ አለባቸው፡፤
12. ህትመት አገልግሎት; ኮምፒውተር ጥገና; ድንኳን፤ ዲኮር፤ ሞንታርቦ; የመኪና ኪራይ;የ ኃላፊ መስተንግዶ, ለአንድ አመት ውል ለመግባት ፍቃደኛ የሆነ
13. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ10ኛው ቀን በእለቱ 11፡30 ታሽጎ በማግስቱ በ11ኛው ቀን 3፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ሆኖም ግን ተጫራቾች ባይገኙም በመመሪያው መሰረት ይከፈታል፤፤ ነገር ግን የመግንስት ስራ በማይኖርበት በመግስት መገናኛ ብዙኃን በግልጽ የተረጋገጠ ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ይከፈታል።
14. አሸናፊ ተጫራች አሸናፊነታቸው በደብዳቤ በተገለጽላቸው 7 የቅሬታ ቀናት ካለቀ በኃላ ከ8-15 ባሉት ቀናት ውስጥ ውል መዋዋል አለባቸው።
15. መስሪያ ቤቱ (ወረዳው) በጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መበቱ የተጠበቀ ነው።
16. በጨረታ ማስታወቂያ ያልተገለጹ ካሉ በግዥ መመሪያ መሰረት ተፈጻሚ ይሆናሉ።
17። ጨረታው ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ ለ 45 ቀን ይሆናል።
አድራሻ፡- ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 አስተዳደር አዲሱ ገበያ ወደ ቀጨኔ በሚያስኬደው መንገድ 200 ሜትር ገባ ብሎ ሀምሌ 19/67 ት/ቤት አጠገብ
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 011 127-5265 / 011 126 8179 /
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ-7 ፋይናንስ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-01
- Bid closing time: 17:30
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ10ኛው ቀን በእለቱ 11፡30
- Bid opening: 2026-09-02 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ11ኛው ቀን 3፡00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Gulele Sub City Woreda 7 FEDB
- Buyer address: ጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 7 አስተዳደር አዲሱ ገበያ ወደ ቀጨኔ በሚያስኬደው መንገድ 200 ሜትር ገባ ብሎ ሐምሌ 19/67 ት/ቤት አጠገብ
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 300.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Published on: Addis Zemen (Aug 21, 2026)
- Posted at: 2026-08-21T11:42:11.000Z