Building Construction

በደ/ምዕ/ኢ/ህ/ክ/መ/ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የግንባታ እና ዙሪያ አጥር ስራ በ2019 በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል

Description

ለ2ተኛ ጊዜ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በደ/ምዕ/ኢ/ህ/ክ/መ/ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በአውሮፓ ህብረት አደጋ ቅነሳ ፕሮግራም በጀት በዳውሮ ዞን ማሪ ማንሳ ወረዳ የጨልሾ የእንስሳት ጤና ኬላ አንድ ብሎክ ህንፃ ግንባታ፤ አንድ የእንስሳት ማዳቀያ ግንባታ እና ዙሪያ አጥር ስራ በ2019 በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት ለመጫረት የምትፈልጉ፡-

1/ በዘርፉ ለ2018 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለው

2/ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል

3/ በመንግስት ግዥ ላይ የአቅራቢነት ሰርተፍኬት ያለው

4/ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN no) ያለው

5/ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ምስክር ወረቀት

6/ ለበጀት ዓመቱ የሚያገለግል ከኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የተሠጠ የታደሰ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችልና ደረጃውን በተመለከተ 5 (አምስት) እና ከዛ በላይ GC፣ BC መሆን አለበት።

7/ ከማንኛውም ታክስ ዕዳ ነፃ ስለመሆኑ ከባለስልጣኑ መ/ቤት የታክስ ክሊራንስ በ2018 ዓ.ም የተጻፈ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል።

8/ የመልካም ሥራ አፈጻጸም (Good Performance Certificate) ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ የመንግሥት ወይም መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ላይ የሰራበትን የሚያሳይ የመልካም ሥራ አፈጻጸም ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል።

9/ ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ 100,000(አንድ መቶ ሺህ ብር) CPO /የባንክ ጋራንቲ/ ጥሬ ገንዘብ ከታወቀ ባንክ በአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ስም በማዘጋጀት በቴክኒካል ኦርጅናል ዶክመንት ውስጥ አስገብቶ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

10/ ተጫራቾች የጨረታ ዶክመንት ግዥ የማይመለስ 500 (አምስት መቶ ብር) ብቻ በአካውንት ቁጥር 1000521691305 በማስገባት የባንክ አድቫይስ ይዞ በመምጣት በዳውሮ ዞን ተርጫ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የደ/ም/ኢት/ህ/ክ/መንግስት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ከግዥ ፋይናንስ ንብረት አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ሰነድ መውሰድ ይኖርባቸዋል።

11/ ተጫራቾች ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ እስከ 21ኛው ቀን ድረስ የደ/ም/ኢት/ህ/ክ/መንግስት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ የጨረታ ዶክመንቶች በመግዛትና በዋጋ ማቅረቢያ በመሙላት ቴክኒካል ኦርጅናል 1 እና ኮፒ 1 ፋይናንሻል ኦርጅናል 1 እና ኮፒ 2 በድምሩ 5 ፖስታ የድርጅታችሁን ማህተም በማድረግ በአንድ እናት የጨረታ ፖስታ ውስጥ በማስገባት የደ/ም/ኢት/ህ/ክ/መንግስት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

12/ ተጫረቾች በእያንዳንዱ ዶክመንት ላይ በመፈረም ማህተም በማድረግ በፖስታ ጀርባው ላይ በሚታይ ጽሑፍ ኦርጅናል እና ኮፒ ለይቶ መጻፍ አለበት።

13/ የጨረታ ሣጥን የሚከፈተው በ22ኛው ቀን ሲሆን ይህ ቀን የመንግሥት ሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሸጎ በዚሁ ዕለት በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የደ/ም/ኢት/ህ/ክ/መንግስት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል።

14/ በጨረታ ማስታወቂያ ያልተገለጹ ሌሎች የመወዳደሪያ ነጥቦች (መስፈርቶች) በጨረታ ዶክመንቱ መሠረት ተግባራዊ ይደረጋል።

15/ ተጫራቾች unconditional letters (በሁኔታ ላይ ያልተገደበ ደብዳቤ) ከታወቀ ባንክ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።

16/ የሂሳብ ስህተት ከጠቅላላ ድምር ከፍታ እና ዝቅታ 5% በመመሪያው መሠረት ተግባራዊ ይሆናል።

17/ በጨረታ ማስታውቂያ እና ዶክመንቱ ላይ የተገለፁትን የመወዳደሪያ ነጥቦችን ያሟላ ተጫራች ብቻ ወደ ድህረ ግምገማ ያልፋል።

18/ ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቦታው ላይ ያለመገኘት የጨረታ አከፋፈትን አያስተጓጉልም።

19/ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡-በቢሮ ስልክ ቁጥር፡-0920 925 053

አድራሻችን- በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/ዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ ውስጥ የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ቢሮ ከጅማ ከተማ በስተደቡብ 145 ኪ.ሜ ከወላይታ ሶዶ ከተማ በስተምዕራብ 165 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በታርጫ ከተማ ይገኛል።

በደ/ምዕ/ኢ/ህ/ክ/መ/ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-09-12
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው ቀን ሲሆን ይህ ቀን የመንግሥት ሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-12 14:30
  • Bid opening (note): ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው ቀን ሲሆን ይህ ቀን የመንግሥት ሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
  • Region: South West Ethiopia Region
  • Publishing entity: South West Ethiopia Peoples Regional State Disaster and Risk Management Commission
  • Bid bond: 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር)
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 22, 2026)
  • Posted at: 2026-08-22T07:55:01.000Z
← Back to all tenders