Stationery

ሞሐ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ ማህበር የፅህፈት መሳሪያዎችና የጽዳት ዕቃዎች ሽሪንክ ፊልም፤ የተለያዩ ፕሪፎርሞች እና የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የፅህፈት መሳሪያዎች የፅዳት እቃዎች ሽሪንክ ፊልም፤የተለያዩ
ፕሪፎርሞች እና የትራንስፖርት
አገልግሎት የጨረታ ግዥ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር-Service 0004/2018

ሞሐየለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ ማህበር የፅህፈት መሳሪያዎችና የጽዳት ዕቃዎች ሽሪንክ ፊልም፤የተለያዩ ፕሪፎርሞች እና የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ የተጠቀሱትን አገልግሎት ማቅረብ የምትችሉ ተጫራች ድርጅቶች የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ሸገር ዱቄትና ዳቦ ፋብሪካ ቅጥር ግቢ አዲስ በተገነባው ህንጻ ሦስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 003 በመውሰድ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።

1. ተጫራቾች ጨረታ ላይ ለመሳተፍ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ፤VAT እና TIN ያላቸውና የግብር ግዴታቸውን የተወጡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡እቃዎች፤ ሽሪንክ ፊልም

2. ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡትን አገልግሎት የምትሰጡበትን ዋጋችሁን በታሸገ ኤንቨሎፕ የፅህፈት እና የፅዳት እቃዎች ጳጉሜ 02 ቀን 2018 ዓ.ም፣ የትራንስፖርት አገልግሎት ጳጉሜ 03 ቀን 2018 ዓ.ም እና ፕሪፎርም እና ሽሪንክ ፊልም ጳጉሜ 04 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ድረስ ከላይ በተገለፀው መ/ቤት አድራሻ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

3. ከተጠቀሰው ሰዓት በኋላ ዋጋ ለማቅረብ የሚመጣ አቅራቢ ተቀባነት አይኖረውም።

4. የፅህፈት እና የፅዳት እቃዎች ጳጉሜ 02 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ተዘግቶ 9፡00 ላይ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ በዋናው መ/ቤት መገኘት በሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ፊት ይከፈታል።

5. የትራንስፖርት አገልግሎት ጳጉሜ 03 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ሰዓት ላይ ተዘግቶ 9፡00 ሰዓት ላይ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ በዋናው መ/ቤት መገኘት በሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ፊት ይከፈታል።

6. ፕሪፎርም እና ሽሪንክ ፊልም ጳጉሜ 04 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ተዘግቶ 9፡00 ሰዓት ላይ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ በዋናው መ/ቤት መገኘት በሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ፊት ይከፈታል።

7. በጨረታው የሚሳተፍ ድርጅት 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

8. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ሸገር ዱቄትና ዳቦ ፋብሪካ ቅጥር ግቢ አዲስ በተገነባው ህንጻ ሶስተኛ ፎቅ የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግና የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር ይችላሉ።

ሞሐ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/


Tender details

  • Deadline: 2026-09-09
  • Bid closing time: 14:30
  • Bid closing (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-09-09 15:00
  • Bid opening (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Moha Soft Drinks Industry S.C.
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 22, 2026)
  • Posted at: 2026-08-22T08:13:00.000Z
← Back to all tenders