Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 የሽሮ ሜዳ ጤና ጣቢያ በ2019 ዓ.ም 1ኛ ዙር ግዥ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች መግዛት ይፈልጋል

Description

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 የሽሮ ሜዳ ጤና ጣቢያ በ2019 ዓ.ም 1ኛ ዙር ግዥ አገልግሎት የሚውሉ፡- ቁጥር 001 /2019 ፣ የጽዳት እቃዎች፤ የጽፈት መሳሪያዎች፤ የደንብ ልብስ እና የደንብ ልብስ ስፊት፤ መዳኒት እና የመዳኒት እቃዎች፤ ቋሚ እቃዎች ፤ ህትመት፤ የ ጭነትና ትራንስፖርት አገልግሎት ፤ ጉልበት ፤የኮምፒተርና የፕሪንተር ጥገና የካፌ አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ 

1. ተጫራቾች ለ2019 ዓ.ም. በ ጀት ዓመት የታደሰ ንግድ ፍቃድ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው በአቅራቢነት የተመዘገቡ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን ይገባቸዋል፡፡

2. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) እና ከዛ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን ይገባቸዋል፡፡

3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ ሰነድ በመክፈል በሽሮ ሜዳ በሚገኘው ጉ/ክ/ከ/ወ/3 ሽሮ ሜዳ ጤና ጣቢያ ገንዘብ ቤት ቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡

4. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በታሸገ ፖስታ ሆኖ በሚመለከተው ሃላፊ ተፈርሞና የድርጅቱ ማህተም ያረፈበትን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡በመሆኑም ተጫራቾች ከዚህ በታች ያለውን የጨረታ መስከበርያ በእያንዳንዱ ሎት ማስያዝ ይኖርባቸዋል

5.

  • ለሎት1 ..... 10,000 ብር (የጽዳት እቃዎች)
  • ለሎት2........ 15,000 ብር (የጽህፈት መሳሪያዎች,
  • ሎት 3 ... 10,000 ብር (የደንብ ልብስ እና የደንብ ልብስ ስፊት )
  • ሎት 4........ 25,000ብር ( መዳኒት እና የመዳኒት እቃዎች )
  • ሎት 5 ..... 10,000 ብር ( ቋሚ ዕቃ)
  • ለሎት 6..... 5,000 ብር ( ህትመት )
  • ለሎት 7. 5000 የጭነት ትራንስፖርት)
  • ለሎት 8... 5,000 ብር (ጉልበት)
  • ለሎት 9. 2,000 ብር (ኮምፒዩተር ፕሪንተርና ኮፒ ማሽን ጥገና)
  • ለሎት 10----- 5,000 ብር ( የካፌ አገልግሎት)

ተጫራቾች በሎት ከላይ በተገለፀው መሰረት በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል

6. መስሪያ ቤቱ ተጫራቾች ከአሸነፉት እቃ ላይ 20% መጨመር ወይም የመቀነስ መብት አለው፡፡

7. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ( አስር ) ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በዚያው እለት ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በቀጣይ ቀን 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፋይናስ ክፍል ቁጥር 50 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የመንግስት ሥራ የማይኖርበት በመንግስት መገናኛ ብዙሃን በመግለፅ የተረጋገጠ ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡

8. ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተመስርቶ የሚቀርብ ዋጋ ተቀባይነት የለውም፡፡

9. ተጫራቾች አሸናፊ የሆነባቸውን እቃዎች በውላቸው መሠረት ሙሉ በሙሉ ገቢ የማድረግ ግዴታ አለባቸው፡፡

10. ጤና ጣቢያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

11. ተጫራቾች እስፔስፊኬሽን ከቀረበባቸው እቃዎች ውጪ ላሉት በሙሉ ናሙና (Sample) ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

12. የጨረታ ሰነዳችሁን ዋናውንና ኮፒውን ማስገባት ይጠበቅባችኃል፡፡

13. የሞላችሁበትን የጨረታ ፖስታ ቢሮ ቁጥር 50 ቀርባችሁ ማስገባት አለባችሁ፡፡

14. ጨረታውን ያሸነፈ በራሱ ትራንስፖርት የሚያቀርብ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 011- 123 6663/62

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 የሽሮ ሜዳ ጤና ጣቢያ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-02
  • Bid closing time: 16:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ( አስር ) ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በዚያው እለት ከቀኑ 10፡00
  • Bid opening: 2026-09-03 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ( አስር ) ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በዚያው እለት ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በቀጣይ ቀን 4፡00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Gulele Sub City Woreda 3 Shiromeda Health Center
  • Buyer address: ከመነን አደባባይ ወደ ሽሮ ሜዳ በሚወስደው መንገድ ከጸሐይ ጮራ ት/ቤት 100 ሜትር ያህል ገባ ብሎ ወደ ግራ የሚታጠፍ የኮብልስቶን መንገድ መጨረሻ ላይ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ ሰነድ
  • Published on: Addis Zemen (Aug 22, 2026)
  • Posted at: 2026-08-22T08:31:14.000Z
← Back to all tenders