Materials

የሰፈረ ሰላም ቅድመ-አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም. 1ኛ (አንደኛ) ዙር ግልፅ ጨረታ የሚፈልጋቸውን የተለያዩ ዕቃዎች አጫርቶ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የሰፈረ ሰላም ቅድመ-አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2018ዓ.ም 1ኛ (አንደኛ) ዙር ግልፅ ጨረታ የሚፈልጋቸውን የፅዳት እቃዎች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ የደንብ ልብሶች፣ የትምህርት መሳሪያዎች፣ የተለያዩ መፅሀፍት፣ የተለያዩ ዕድሳቶች፣ ቋሚ እቃዎች ፈርኒቸሮች፣ ቋሚ ዕቃዎች የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ አይነቶች፣እና የተለያዩ የሙዚቃ መሳሪያዎች አገልግሎቶች ግዢን አጫርቶ መግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት በጨረታ መወዳደር የሚችሉ አቅራቢዎች፡-

1. የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው

2. የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ

3. በአቅራቢነት የተመዘገቡ እና የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ በወቅቱ ከአቅራቢነት ያልታገዱ

4. ቫት የተመዘገቡ እና የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ

5. 5 ሁሉም ተጫራቾች ጨረታ አሸንፈ ዕቃ ሲያቀረቡ የገቢዎች ሚኒስቴር ባወጣዉ መመሪያ መሰረት በብርሃንና ሰላም ማተሚያ የተተመዉ QR CODE.ደረሰኝ ማቀረብ የሚችሉ መሆን አለበቸዉ።

6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ በሚያቀርቡት ገንዘብ ዋጋ፡- በሎት የተቀመጡት የገንዛቡ መጠን በ1.5 እስከ 2 ፐርሰንት ተበዝቶ ነዉ የተቀመጠ ነው።

ሎት

የዕቃ ዓይነት

የብር መጠን (..)

ሎት.1

አላቂ የቢሮ ዕቃዎች

2500.00

ሎት.2

ልዩ ልዩ የትምህርት መሳሪያዎች

2000.00

ሎት3

ሌሎች ልዩ ልዩ መጠቀሚያ መሳሪያዎች

2000.00

ሎት.4

የፅዳት ዕቃዎች

1000.00

ሎት5

ቋሚ ዕቃዎች የተለያዩ ፈርኒቸሮች

2000.00

ሎት.6

ቋሚ ዕቃዎች የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ አይነቶች

5000.00

ሎት.7

የደንብ ልብስ

2000.00

ሎት.8

የደንብ ልብስ ስፌት

1500.00

ሎት.9

የስፖርት መምህራን ትጥቅ

2000.00

ሎት10

የህትመት አገልግሎት

1000.00

ሎት.11

የተለያዩ የሙዚቃ መሳሪያዎች

3000.00

ሎት.12

የተለያዩ የላብራቶሪ ዕቃዎች

2000.00

ሎት.13

የተለያዩ ፕላንትና ማሽነሪ ዕድሳትና ጥገና

1500.00

ሎት.14

ለህንፃና ቁሳቁስ ተገጣጣሚዎች ዕድሳትና ጥገና

2000.00

7. የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።

8. ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10(አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በሠፈረ ሠላም ቅድመ-አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ቢሮ በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት እና በግዢ ቢሮ ለዙሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

9. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሰነድ በእያንዳንዱ ገፅ ላይ ፊርማና ማህተህ በማሳረፍ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።

10. የጨረታ ሰነዱ በተጫራቾች መሞላት ያለባቸው ክፍሎች በሙሉ መሞላት አለባቸው።

11. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ዋናውን እና ከላይ ከ1-4 የተጠቀሱትን ሰነዶች እና በባንክ በተመሰከረለት የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) በአንድ ላይ በማሸግ ኮፒዎችንም ለየብቻ በማሸግ እና ቴክኒካል ሰነድ ወይም ናሙና ለማቅረብ ለማያስፈልግ ለብቻ በማሸግ ሙሉ አድራሻ በትክከል በመሙላት ሁሉንም ሰነዶች በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

12. የጨረታ ሰነዱን እና የዋጋ ማቅረቢያው ሳይለወጥና ሳይቀነስ በሙሉ የማይመልስ አቅራቢ ከጨረታው ይሰረዛል።

13. በጥቃቅን እና አነስተኛ በስራ ኢንተርፕራይዝ የተደራጃችሁ በምታመርቱት ምርት ላይ ብቻ ልዩ አስተያየት ስለምናደርግ አምራች መሆናችሁን ካደራጃችሁ አካል የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ አለባችሁ።

14. ጨረታው የሚያበቀዉ በ10ኛ ቀን እስከ 11፡30 የሚያበቀ ይሆናል ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚያውኑ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል! 11ኛው ቀን ስራ የሌለበት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።

15. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ 2(ሁለት) ቀን በፊት ለሁሉም ዕቃዎች ናሙና ወይንም ስፔስፊኬሽን ስለ ዕቃው በደንብ በሚገልፅ መልኩ ተዘጋጅቶ ማቅረብ መቻል አለባቸው! የናሙና መቀበያ ቅፅ በ2 ኮፒ አዘጋጅቶ የድርጅቱን ማህተብ በማድረግ አብሮ ማቅረብ መቻል አለባቸው።

16. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ ያለ ስርዝ ድልዝ በትከክል መሞላት አለበት።

17. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋ የማይነበብ እና ስርዝ ድልዝ ያለው ከሆነ ተቀባይነት የለውም።

18. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ማሻሻያ ማድረግ እና ከጨረታው እራስን ማግለል አይቻልም።

19. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- በአዲስ ከተማ ክ/ከ ወረዳ 4 ፅ/ቤት ፊት ለፊት በድሮው ጭማድ በአዲሱ ኢትዮ ጠቢብ ሆስፒታል ፊት ለፊት 200 ሜትር ገባ ብሎ የሰፈረ ሰላም ቅድመ-አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት።

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0112 733 497፣ 0112 136 221፣ 0112 135 898

ሰላም ቅድመ-አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-03
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10(አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00
  • Bid opening: 2026-09-03 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10(አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Sefere Selam Kindergarten & Elementary School
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 400.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 22, 2026)
  • Posted at: 2026-08-22T09:09:39.000Z
← Back to all tenders