Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በጉ/ክ/ከ/መ/04 የጉቶ ሜዳ ጤና ጣቢያ በ2019 ዓ.ም የበጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሰራት ይፈልጋል

Description

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ጉ/ሜ/ጤ/ጣ/001/2019

በጉ/ክ/ከ/መ/04 የጉቶ ሜዳ ጤና ጣቢያ በ2019 ዓ.ም የበጀት ዓመት የተለያዩ

  • 1. የደንብ ልብስ ጨርቆች፤
  • 2.የደንብ ልብስ ስፌት፤
  • 3.የተለያዩ የጽዳት ዕቃዎች፤
  • 4.የፅህፈት መሳሪያወች፤
  • 5.የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፤
  • 6. የእጅ መሳሪያዎች፤
  • 7.የህትመት ውጤቶች አገልግሎት፤
  • 8. ፈርኒቸሮች፤
  • 9. ቋሚ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
  • 10.የጭነት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች፤
  • 11.የቤት ውስጥ ቁሳቁስን ዕቃዎች፤
  • 12 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችና ተዛማች ዕቃዎች ጥገና፤
  • 13. ካፌ አገልገሎት
  • 14.የህክምና ዕቃወችን ፤
  • 15.የመድህኒት፤
  • 16.የላቦራቶር ሬኤጀንትን
  • 17.ፓርተሸን/የቢሮ ጥገና ስራዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ፡-

1. ከሚገዛው ዕቃ /አገልግሎት/ ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ የዘመኑ ንግድ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር Tin No ማቅረብ የሚችሉ፣

2. በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚገልፅ የምዝገባ የምስክር ወረቀት /በዌብሳይት የተመዘገቡ ተጫራቾች ከዌብሳይቱ ላይ ኘሪንት አድርገው ማቅረብ የሚችሉ፣

3. ተጫራቾች በየዘርፉ የተወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ከ 5ዐ ሺህ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና/የሚወዳደሩበትን ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ የሎት,1 10,000.00ብር ሎት2, 10,000.00ብር ሎት3, 10,000.00 ሎት4,10,000.00 ሎት5, 10,000.00 ሎት6, 5,000.00 ሎት7, 10,000.00 ሎት8, 10,000.00 ሎት 9, 10,000.00 የሎት10, 5,000.00 ብር የሎት11, 5,000.00ብር የሎት12, 10,000.00ብር,የሎት 13, 10,000.00 ብር,የሎት 14, 20,000.00 ብር የሎት 15, 20,000.00 ብር የሎት 16, 20,000.00ብር የሎት 17, 20,000.00ብር በጤና ጣቢያው ስም በተዘጋጀ የክፍያ ትዕዛዝ /CPO/ ማስያዝ የሚገባቸው ሲሆን ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያሲያዙትን CPO ዋናውን ወይም ገንዘብ የከፈሉበትን ደረሰኝ ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸውጋር አያይዘው ማቅረብ የሚገባቸው ሲሆን የጨረታ ማስከበሪያ ያላስያዘ ተጫራች ከውድድሩ ውጪ ይሆናል፡፡

5. ተቋማችን የሚገዛቸውን የአገልገሎት /ዕቃዎች አይነት ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ውስጥ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን በየሎቱ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 500 በመክፈል 4ኛ ፎቅ ቁጥር 401 መግዛት ይችላሉ፡፡

6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ በመሙላት በአንድ ወጥ በታሸገ ፓስታ ኦርጅናልና ኮፒ ለዚሁ አገልግሎት ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 401 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

7. መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ቫትን ያላካተተ፣የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም አድርጐ የማያቀርብ፣ ስርዝድልዝ ያደረገ እና አማራጭ ጨረታ የተጠቀሙ ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዕቃ ጥራት በተመረጠው ናሙና ጥራት መሰረት ማቅረብ አለባቸው፡

8. የጨረታው ሣጥን በአስረኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ታሽጎ በአስራ አንደኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባይገኙም ጨረታው በግልጽ ይከፈታል፡፡

9. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያወች የተለያዩ የጽዳት ዕቃዎች፤ የደንብ ልብስ ጨርቆች፤ ቋሚ ዕቃዎች፤ ፈርኒቸሮች፤የተለያዩ የእጅ መሳሪያዎች፤ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፤ የህክምና ዕቃዎች የህትመት ውጤቶች አገልግሎትን ጥራት ለመለየት የሚያስችልና ጨረታው ከመከፈቱ ከአንድ ቀን በፊት 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 401 በሚገኘው ግዥ ክፍል ናሙና ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡ ናሙና ያላቀረበ ተወዳዳሪ) ተጫራቾ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡

10. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈውን እቃ በራሱ ትራንስፖርት አጓጉዞ ጤና ጣቢያ እቃ ግምጃ ቤት ማቅረብ ይኖርበታል፣

11. መ/ቤቱ እንደአስፈላጊነቱ ከውል በፊት 20%/ሀያ ከመቶ/ጨምሮ ወይም20%ቀንሶ እና 25% ጨምሮ መግዛት ይችላል፣

12. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ፦ የጥቃቅንና አነስተኛ ተወዳዳሪዎች ባመረቱትና አሴት በጨመሩበት ብቻ ይሳተፋሉ፡፡

አድራሻ፡- ጉቶ ሜዳ ጤናጣቢያ ኮሪያ ዘማቾች በስተቀኝ 100ሜትር ገባ ብሎ 0116680700

በጉለሌ ክፍለ ከተማ 04 ጉቶሜዳ ጤና ጣቢያ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-02
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስረኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-03 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Gulele Sub City Administration Woreda 4 Guto Meda Health Office
  • Buyer address: ችሎት አካባቢ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 22, 2026)
  • Posted at: 2026-08-22T09:41:50.000Z
← Back to all tenders