Cleaning and Janitorial Equipment and Service

የኮ/ቀ/ክ/ከተማ አስተዳደር የወረዳ 02 ጤና ጣቢያ ፅ/ቤት የመንግሥት ግዥ ቡድን የተለያዩ ግዥዎችን በግልፅ ጨረታ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2018

የኮ/ቀ/ክ/ከተማ አስተዳደር የወረዳ 02 ጤና ጣቢያ ፅ/ቤት የመንግሥት ግዥ ቡድን የተለያዩ ግዥዎችን በተቋሙ ተጠቃሚ ለሆኑት ዲፓርትመንቶች የእቃ ግዥዎችን በ13 ምድብ ከፍሎ በግልፅ ጨረታ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

  • ሎት1 ፅዳት ዕቃዎች
  • ሎት2 የጽሕፈት ዕቃዎች
  • ሎት3 የደንብ ልብስ
  • ሎት4 ቋሚ አላቂ ዕቃዎች
  • ሎት5 ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
  • ሎት6 ፈርኒቸር
  • ሎት7 የጥገና እና ፓርቲሽን ሥራዎች
  • ሎት8. የህትመት ሥራዎች
  • ሎት9. መድኃኒት ማስወገድ
  • ሎት10. የሕክምና መሣሪያዎች
  • ሎት11. የኤኤክትሮኒክስ ዕቃዎች ጥገና
  • ሎት12. የጉልበት፣ የጭነትና የትራንስፖርት አገልግሎት
  • ሎት13. የሠራተኞች ካፍቴሪያ አገልግሎት

በዚሁ መሠረት ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበትንና አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ፣ ቲን ሰርተፍኬት ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም ከፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በእቃ አቅራቢነት የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት እና የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

2. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ በማቅረብ ዘወትር በሥራ ሰዓት መውሰድ ይችላሉ።

3. የጨረታ ሰነዱ በኢንቨሎፕ ታሽጎ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን ለየብቻው በፖስታ ታሽጎ የኮ/ቀ/ክ/ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 02 ጤና ጣቢያ ጽ/ቤት የመንግሥት ግዥ ቡድን 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 64 ማስገባት ይኖርበታል።

4. አንዱ ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መሰጠት አይቻልም።

5. ጨረታው በ11ኛው ቀን 3፡30 ሠዓት ሰነዱ ተመላሽ ተደርጎ በ4፡00 ሠዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

6. ተጫራቾች በጋዜጣው ላይ በተገለጹት የጨረታ ዓይነቶች በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ።

7. ተጫራቾች በገዙት ጨረታ ሰነድ ላይ ፊርማቸውን የድርጅቱን ማህተም በእያንዳንዱ ገጽ ላይ በመፈረም ማቅረብና ማረጋገጥ አለባቸው።

8. የጨረታ ማስከበሪያ ከሎት1፤2፤3፤7፤8፤9፤10፤11፤13 ያሉት 10,000 (አስር ሺ ብር) ለሎት 5 እና 6 20,000 (ሃያ ሺ ብር) እንዲሁም ሎት4 እና 12 5,000 (አምስት ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ከሆነ ከአደራጃቸው አካል የድጋፍ ደብዳቤ በፅ/ቤቱ ኃላፊ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 02 ጤና ጣቢያ በፅ/ቤቱ ስም ተሠርቶ መቅረብ ይኖርበታል።

9. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ጨረታ የጨረታ ዓይነቶች ውስጥ የተዘረዘሩትን ያንዱ ዋጋ እና የጠቅላላውን ዋጋ በግልጽ ከጽ/ቤት ገዝተው በወሰዱት ሰነድ ላይ ማስፈር ይኖርባቸዋል።

10. ተጫራቾች ሎት 1 እስከ 4 በተገለፁት ጨረታ ዓይነቶች ናሙና ማቅረብ ግዴታ ሲሆን ሌሎቹ ናሙና ለማይቀርብባቸው ሎቶች ስፔስፊኬሽን ካታሎግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

11. በሎት 12 ለተጠቀሰው የጉልበት ሥራ አገልግሎት የቫት ሰርተፊኬትና የአቅራቢነት ሰነድ ግዴታ አይደለም።

12. የሎት 7 ጥገናና ፓርቲሽን ደረጃ 7 በላይ መሆን ይኖርበታል።

13. የጨረታ አሸናፊዎች ማሸነፋቸውን የሚገልፅ ደብዳቤ የሚደርሳቸው ሲሆን ውል ማስከበሪያ ለአሸነፉበት ዋጋ 10% cpo ማስያዝ አለባቸው።

14. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆኖ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ ፡- ኮ/ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ካራ ቆሬ ወደ መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን መውጫ ወረዳ 02 ጤና ጣቢያ በሚገኘው 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 64

በኮ/ቀ/ክ/ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት የወረዳ 02 ጤና ጣቢያ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-03
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ በ11ኛው ቀን 3፡30 ሠዓት
  • Bid opening: 2026-09-03 12:00
  • Bid opening (note): በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሠዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Kolfe Keranyo Woreda 02 Health Post
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 22, 2026)
  • Posted at: 2026-08-22T09:48:48.000Z
← Back to all tenders