Stationery
በጉራጌ ዞን የጉንችሬ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
ብሔራዊ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የግልፅ ጨረታ ቁጥር 0126/14/2018ዓ.ም
በጉራጌ ዞን የጉንችሬ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በከተማው ለሚገኙት ሴ/መ/ቤቶች በ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩት እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- 1. ሎት-1 የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎች
- 2. ሎት-2 የተለያዩ የጽዳት ዕቃዎች
- 3. ሎት 3 የተለያዩ የደንብ ልብሶችና ጫማዎች
- 4. ሎት-4 የተለያዩ ሞተር ሳይክሎች
- 5. ሎት 5 የተለያዩ ፈርኒቸሮች
- 6: ሎት 6 የተለያዩ ኤሌክትሮኒክሶች
በዚሁ መሰረት ተጫራቾች፦
1. በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያላችሁና የዘመኑን ግብር በመክፈል ፍቃድ ያሳደሳችሁ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /ቲን/ ማቅረብ የሚችሉ
2. በእቃ አቅራቢነት የተመዘገቡ የተጨማሪ አሴት ታክስ የተመዘገቡበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
3. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ከጠቅላላ ገንዘብ ለሎት-1 ብር 20,000/ሀያ ሺ ብቻ/ ለሎት-2 ብር5,000/ አምስት ሺ/ ስሎት-3 ብር 5,000/አምስት ሺ/ ለሎት-4 ብር 15,000/አስራ አምስት ሺ/ ለሎት-5 ብር 10,000/አስር ሺ ብር/ ለሎት-6 ብር 10,000/አስር ሺ ብር ብቻ/ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ/በጥሬ ገንዘብ/ በጉንችሬ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም ማቅረብ አለባቸው።
4. ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑባቸው አቃዎች ጉ/ከ/አስ/ፋ/ጽ/ቤት መጋዘን ድረስ አጠቃለው በአንድ ጊዜ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
5. ተጫራቾች በእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 400(አራት መቶ ብቻ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ ከጉ/ከተማ አስ/ፋይናንስ ጽ/ቤት መውሰድ ይችላሉ።
6. ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከተገለፀ ቀን ጀምሮ ከ07 የስራ ቀናት በኋላ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ውል መፈፀም አለባቸው ::
7. ተጫራቾች ውል እንዲገቡ ጥሪ በተደረገ በ07 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ቀርበው ውል ለመግባት ፈቃደኛ ካልሆኑና ውል ካልፈፀሙ መስርያ ቤቱ የጨረታ ማስከበርያውን የማውርስ መብት አለው፡፡
8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን አንደ ኦርጅናል አና ሁለት ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ከ16/12/18 ቀን ጀምሮ አስከ 02/13/18 አስከ ከቀኑ 8፡00 ድረስ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ።
9. ጨረታው በዚህ እለት ከቀኑ 8፡10 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ነገር ግን ተጫራቾች ወደም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አስመገኘት ጨረታው ከመክፈት አያሰተጓጉለውም፡፡
10. ተጫራቾች የሚሞሉት የጨረታ ዋጋ ጨረታው ከተከፈተ ቀን ጀምሮ ስ45 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል።
11. አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች የተጫረቱባቸው እቃዎች ሳምፕል ማቅረብ አለባቸው።
12. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስቁ 011 332 0641 ይደውሉ።
በጉራጌ ዞን የጉንችሬ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-07
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-09-07 14:10
- Region: Central Ethiopia
- Publishing entity: Gurage Zone Gunchire City Administration FEDB
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: በእያንዳንዱ ሎት 400 (አራት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Aug 22, 2026)
- Posted at: 2026-08-22T09:53:39.000Z