Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ፋይናንስ ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎች እና አገልግሎት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የ1ኛ ዙር ብሄራዊ ግልጽ ጨረታ ግዥ ማስታወቂያ

የግዥ ጨረታ መለያ ቁጥር: ጉ/ክ/ከ/ወ8/001/2019

በጉለሌ ከ/ከተማ ወረዳ 8 ፋይናንስ ጽ/ቤት የጽህፈት መሳሪያ፤ የደንብ ልብስ የጽዳት እቃዎችን፤ ቋሚ የቢሮ እቃዎች፤ የትራንስፖርት አገልግሎት የኤሌክትሮኒክስ እና ሌሎች የቢሮ መገልገያ ጥገና አገልግሎቶች፤የመስተንግዶ አገልግሎት፤ የደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት እና የሞንታርቦ፤ ድንኳን ጀኔሬተር እና ሌሎች ኪራይ አገልግሎት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሰረት ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሕጋዊ ተጫራቾች የሚከተለውን መሰፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።

1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋገጥ የምሰክር ወረቀት እና ቲን ነምበር ያላቸው መሆን አለባቸው።

2. Tot 3%፤ እና 10% ተመዝጋቢዎች የመስተንግዶ አገልግሎት፤የኤሌክትሮኒክስ እና ሌሎች የቢሮ መገልገያ እቃዎች ጥገና አገልግሎት የሞንታርቦ፤ ድንኳን ጀኔሬተር እና ሌሎች ኪራይ አገልግሎት እና ትራንስፖርት አገልግሎቶች ላይ መወዳደር ይችላሉ።

3. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ወይም በአዲስ አበባ ፋይናንስ ቢሮ ያቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

4 ለሚጫረቱባቸው እቃዎች እንዳስፈላጊነቱ ናሙና ማቅረብ አለባቸው።

5. የታደሰ ንግድ ፋቃድ እና የንግድ ፍቃድ የምስክር ወረቀት ያላቸው በተሰጠበት የንግድ ዘርፍ ብቻ መሳተፍ ይችላሉ።

6. ተጫራቾች የተጠቀሰዉን የጨረታ ማስከበሪያ በጽ/ቤቱ ስም የተዘጋጀ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ማቅረብ አለባቸው።

7. ተጫራቾች ከአንድ ሎት በላይ የሚወዳደሩ ከሆነ የጨረታ ማሰከበሪውን በተናጠል ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

ሎት ቁጥር

አላቂ የጽህፈት መሳሪያ

የተጠየቀዉ የጨረታ ማስከበሪያ (በኢትዮጵያ ብር)

1

አላቂ የጽህፈት መሳሪያ

81,200

2

የፅዳት ዕቃዎች

75,600

3

የደንብ ልብስ

77,000

4

ቋሚ የቢሮ እቃዎች

20,000

5

ህትመት

7,400

6

የትራንስፖርት አገልግሎት

5,000

7

የኤሌክትሮኒከስ እና ሌሎች የቢሮ መገልገያ እቃዎች ጥገና አገልግሎት

5,000

8

የመስተንግዶ አገልግሎት

52,460

9

የደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት

5,000

10

የሞንታርቦ፡ ድንኳን ጀኔሬተር አና ሌሎች ኪራይ አገልግሎት

16,500

11

የጉልበት ስራ

1,500

8. በጨረታው ያላሸነፉ ድርጅቶች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ይመለሰላቸዋል።

9. ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚውል ሲሆን ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) የኢትዮጵያ ብር በመክፍል የጨረታ ሰነዱ ጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ-8 ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 መውሰድ ትችላላችሁ።

10. ተጫራቶች የጨረታ ሰነድ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በማሽግ በተዘጋጀዉ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት አለባቸዉ።

11. በአምራች ዘርፍ የተሰማሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ብቻ መወዳደር ከፈለጉ ከአደራጃቸው ተቋም በጽ/ቤት ኃላፊ የተፈረመ የዋስትና ደብዳቤ ሲያቀርቡ የጨረታ ሰነድ በመውሰድ ማስረጃ መወዳደር ይችላሉ።

12. በአምራች ዘርፍ የተሰማሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ተደራጅተው ማስረጃ በማቅረብ የሚወዳደሩ ድርጅቶች ለውል ማስከበሪያ የሚሆን በጽ/ቤት ኃላፊ የተፈረመ የዋስትና ደብዳቤ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።

13. ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ-8 ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

14 ጨረታው በ10ኛው ቀን በ10፤30 ታሽጎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

15. አንዱ በአንዱ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።

16. ተጫራቾች የአንዱ ነጠላ ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆኑን ወይም አለመሆኑን መጠቀስ አለበት፡፡ ያልተጠቀሰ ከሆነ ቫት እንዳካተተ ተደርጎ ይወሰዳል።

17. አሸናፊዉ ያሸነፈባቸዉን ንብረቶች የወረዳው ንብረት ከፍል ድረስ ገቢ ማድረግ አለበት (የሰራተኛ እና የትራንስፖርት ወጪ አቅራቢ ድርጅቱ የሚችል ይሆናል)።

18. አድራሻችን ጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 8 አስተዳደር አዲሱ ገቢያ ጤና ጣቢያ በስተጀርባ 100 ሜትር ገባ ብሎ ነው።

19. ፖስታዎቹ መታሸግ ና በላያቸው ላይ ማህተም መደረግ ይኖርባቸዋል።

20. ለሰራተኞች የካፌ አገልግሎት ለመስጠት የሚጫረቱ ድርጅቶች የሻይ ማሽን፤ ፍሪጅ ፤ ቴሌቪዥን፤ ወንበር፤ ጠረጴዛ እንዲሁም አስፈላጊ የሆነ ምግብ ማብሰያ እና ማቅረቢያ በራሱ ማቅረብ ይኖርበታል

21. መስሪያ ቤቱ በጨረታ በተገለፀው የዕቃ መጠን ላይ 20% የመጨመር ወይንም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው

22, መ/ቤቱ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመስረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ጉለሌ ከ/ከተማ ወረዳ 8 ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2

ለበለጠ መረጃ : በስልክ ቁጥር 0111 547 450 መደወል ይችላሉ።

ጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ፋይናንስ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-02
  • Bid closing time: 16:30
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን በ10፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-03 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Gulele Sub City Administration Woreda 08 Finance Office
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 22, 2026)
  • Posted at: 2026-08-22T10:05:10.000Z
← Back to all tenders