House and Building Sale
የቦታ ስፋት በካርታቸው መሠረት 310 ካ/ሜ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት የምስራች ለማ እና የፍ/ባለዕዳ እነ ሰብለ ብርሃኑ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/209899 በ03/07/2018 ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/215599 በ8/8/2018ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 08 የቤት ቁጥር 1658 የካርታ ቁጥር 11/27/17890/18145/01 የተመዘገበ ካርታ ያለው የቦታ ስፋት በካርታቸው መሠረት 310 ካ/ሜ የሆነ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 8,206,780 (ስምንት ሚሊዮን ሁለት መቶ ስድስት ሺህ ሰባት መቶ ሰማንያ ብር) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 8፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሦስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ ቤት ስም CPO አሠርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን 15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ንብረቱን ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት በሐራጅ መንገድ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 112 730 852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-28
- Bid closing time: 14:30
- Bid opening: 2026-09-28 14:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published on: Addis Zemen (Aug 22, 2026)
- Posted at: 2026-08-22T10:07:36.000Z