Cleaning and Janitorial Equipment and Service
ኮ/ቀ/ክ/ከተማ የወረዳ 5 ፋይናንስ ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ የስራ ሂደት በ2019 የበጀት ዓመት ባለው በጀት የተለያዩ እቃዎችን ለመግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2019
ኮ/ቀ/ክ/ከተማ የወረዳ 5 ፋይናንስ ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ የስራ ሂደት በ2019 የበጀት ዓመት ባለው በጀት የተለያዩ እቃዎችን ለመግዛት ይፈልጋል።
ሎት አንድ የተለያዩ አላቂ የጽህፈት መሳሪያ እስቴሽነሪ፣ ሎት ሁለት የተለያዩ የደንብ ልብስ ፣ ሎት ሶስት የተለያዩ የጽዳት እቃዎች ፣ ሎት አራት ኤሌክትሮኒከስ ጥገና ፣ ሎት አምስት የህትመት አገልግሎት ፣ ሎት ስድስት መስተንግዶ አገልግሎት ፣ ሎት ሰባት የጉልበት ስራ አገልግሎት ፣ ሎት ስምንት የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ፣ ሎት ዘጠኝ የጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት ፣ ሎት አስር የፈርኒቸር ጥገና አገልግሎት ፣ ሎት አስራ አንድ የዲኮር አገልግሎት ፣ ሎት አስራ ሁለት የግብርና ግብአቶች ዘር፣ ሎት አስራ ሶስት የተለያዩ ደንብ ልብሶችን መስፋት ለመግዛት ስለፈለግን ተጫራቾች የሚከተሉትን ነጥቦች በሚገባ በመረዳት በጨረታ ሰነድ ላይ መሙላት ያስፈልጋል።
1. የጨረታ ሰነዱ በኤንቨሎፕ ታሽጎ በኦርጂናል ኮፒ በማድረግ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀ ሳጥን መግባት ይኖርበታል።
2. ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያ ላይ ከተራ ቁጥር 1 እሰከ 13 ባሉት የጨረታ ዓይነቶች በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት በእያንዳንዱ ሎት ላይ የጨረታ አይነት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት አንድ 22,300.00 ብር / ለሎት ሁለት 17,800.00 ብር / ለሎት ሶስት 23,000.00 ብር / ለሎት አራት 6,000.00 ብር / ሎት አምስት 8,500.00 ብር / ሎት ስድስት 24,000.00 ብር / ሎት ሰባት 10,500.00 ብር / ሎት ስምንት 8,000.00 ብር / ሎት ዘጠኝ 8,000.00 ብር / ሎት አስር 6000.00 ብር / ሎት አስራ አንድ 8000.00 ብር / ሎት አስራ ሁለት 7000.00 / ሎት አስራ ሶስት 5000.00 ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በመስሪያ ቤታችን ስም በማዘጋጀት ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በታሸገ ፖስታ ማስገባት ይኖባቸዋል።
4. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ሎት የጨረታውን ማስከበሪያ CPO በጥቃቅንና አነስተኛ ተቋም የተደራጁ ከሆነ በአደራጁ ተቋም ሀላፊ የተፈረመ ደብዳቤ ማምጣት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ካልሆነ ጨረታው ውድቅ ይሆናል።
5. ጨረታውን ለማዛበት የሚሞከር ተጫራች ከጨረታው ውጪ እንደሚሆንና የጨረታው ማስከበሪያ ሲፒኦ እንደሚወረስ ማወቅ አለባቸው።
6. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት የጨረታ አይነት ውስጥ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች የእያንዳንዱን ዋጋ ቫትን ጨምሮ በግልፅ ማስፈር ይኖርበታል።
7. በጥቃቀንና አነስተኛ ተቋም የተደራጁ ከሆነ ከጥቃቅንና አነስተኛ አደራጅ ተቋም በሀላፊው የተጻፈ ወቅታዊ የሆነ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፡፡ በባለሙያ የተጻፈ ከሆነ ተቀባይነት የለውም።
8. በጥቃቅንና አነስተኛ ተቋም የተደራጁ ከሆነ አሸንፈው በገቡት ውል መሰረት ማቅረብ ካልቻሉ አደራጁ ተቋም /ደብዳቤውን የጻፈው አካል ሀላፊነቱን የሚወስድ ይሆናል።
9. የጨረታ ሰነዱ የተዘጋጀው በአማረኛ ቋንቋ ነው።
10. በጨረታ ሰነድ ማቅረቢያ መጨረሻ ቀን ማለትም በ11ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረዳው አስተዳደር ጽ/ቤት ሁለገብ አዳራሽ ወይም በፋ/ጽ/ቤት ወስጥ ይከፈታል።
11. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበትንና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይንም ከፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በዕቃው አቅራቢነት የተመዘገቡበትን የምስከር ወረቀት እና የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
12. በጨረታው አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ድርጅት ዕቃዎቹን ከጽ/ቤቱ ጋር በሚገባው ውል መሰረት እንዲያስገባ ሲታዘዝ በወረዳ 05 ዕቃ ግምጃ ቤታችን ድረስ በራሱ ወጪ ማስረከብ የሚችል መሆን አለበት።
13. አሸናፊው ተጫራች የውል ማስከበሪያ ጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርበታል።
14. በጨረታው ያሸነፈው ድርጅት ከጽ/ቤቱ ጋር ውል እንደፈጸመ ውል ማስከበሪያውን እንዳስያዘ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘውን ገንዘብ ተመላሽ ይደረግለታል።
15. ማንኛውም ተጫራች የመ/ቤቱ የዕቃ /የጥራት/ ተቆጣጣሪ ኮሚቴ የዕቃዎችን ጥራት አይቶ መ/ቤቱ ካወጣው የጨረታ ሰነድ እና በጨረታ እንዲያልፍ ከተደረገው የዕቃው ቴክኒካል ስፔስፊኬሽን ወይም ከገባው ናሙና ጋር የማይጣጣም ከሆነና ጥራት የጎደለው ነው ብሎ ካመነ ጨረታውን አሸንፎ እንዲያቀርብ የታዘዘው ድርጅት ዕቃውን የመመለስ ግዴታ አለበት።
16. በጨረታው ያሸነፈው ተጫራች ማሸነፉን እንደተገለጸለት ከመ/ቤቱ ጋር ከ7ኛው - 15ኛው ቀን ባሉት 8 የስራ ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውል መፈጸም አለበት።
17. በጨረታው ያሸነፈባቸው ዕቃዎች ውል ከፈጸመ በኋላ በሚቀጥሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዕቃዎችን በወረዳ 05 ዕቃ ግምጃ ቤት ገቢ ማድረግ አለበት።
18. የግዥ ውል በሚፈጸምበት ጊዜ ሰነዱ ላይ የተሰጠው የዕቃ ብዛት በተወሰነ መጠን 20% ሊጨምርም ወይም ሊቀንስ የሚችል መሆኑን ተጫራቹ አውቆ የመጫረት ግዴታ አለበት።
19. ተጫራቾች ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት ቀደም ብሎ ለሚጫረቱባቸው ዕቃዎች ናሙና ለግዥ ባለሙያ ማስረከብ አለባቸው።
20. አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የጨረታ ኮሚቴው የዕቃዎችን ጥራት በድርጅቱ የስራ ቦታ በመገኘት ለማየት ቢፈልግ ድርጅቱ ተገቢውን ትብብር የማድረግ ግዴታ አለበት።
21. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ወይም ድርጅቶች ማሸነፋቸው እንደተገለጸለት በተሰጠው ጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርቦ ውል ካልፈጸመ ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ሆኖ መ/ቤቱ እንደምርጫው ሁለተኛ የወጣውን ተወዳዳሪ ሊጋብዝ ይችላል፡፡
22. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
23. የጨረታውን ሰነድ ከወረዳ 05 ፋይናንስ ጽ/ቤት 500 ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
ማሳሰቢያ
- ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ተጫራቾች ናሙና ማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት እቃዎች ልዩ መለያ ማቅረብ ከፈለጉ ምርመራ በሚለው ቦታ መፃፍ ይችላሉ።
- አስፈላጊ ሲሆን የጨረታ ኮሚቴው ወይም የግዢ ሰራተኛው በቂ ስቶክ መኖሩን ለማረጋገጥ መጋዘን ማየት ይችላሉ።
- ለበለጠ መረጃ ዘነብ ወርቅ ታክሲ ማቆሚያ ከፍ ብሎ በስልክ ቁጥር፡ 01118-32-98-49 / 09-13-15 29-22/09-73-98-04-70
ኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ የወረዳ 5 ፋይናንስ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-03
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ጨረታው በ11ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-03 14:30
- Bid opening (note): ጨረታው በ11ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Kolfe Keranio Sub City Administration Woreda 5 FEDB
- Buyer address: ዘነብ ወርቅ ታክሲ ማቆሚያ ከፍ ብሎ
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 22, 2026)
- Posted at: 2026-08-22T10:25:18.000Z