Cleaning and Janitorial Equipment and Service

የመተባበር አንደኛና መካከለኛ ደ/ት/ቤት በ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል

Description

የመተባበር አንደኛና መካከለኛ ደ/ት/ቤት በ2019 በጀት ዓመት

  • ሎት 1 አላቂ የቢሮ እቃ የበጀት ርዕስ 6212 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 11500
  • ሎት 2. ልዩ ልዩ መሳሪያዎች የበጀት ርዕስ 6219 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 280.38
  • ሎት 3. የፅዳት መሪዎች የበጀት ርዕስ 6218 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 12,000
  • ሎት 4 አላቂ የትምህርት መሳሪያዎ የበጀት ርዕስ 6215 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 4,195.4
  • ሎት 5 የሰራተኞች የደንብ ልብስ እና ስፊት የበጀት ርዕስ 6211 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 13000
  • ሎት 6. ህትመት የበጀት ርዕስ 6213 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 1,400
  • ሎት 7. ለህንጻና፣ ለቁሳቁስ እና ተገጣጣሚዎች መግዥያ የበጀት ርዕስ 6314 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,803.06
  • ሎት 8. ለፕላንት፣ ማሸነሪና መሳሪያ መግዥያ የበጀት ርዕስ 6313 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 6,000
  • ሎት 9. ልዩ ልዩ ክፍያዎች የበጀት ርዕስ 6419 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 908.37

በዘርፉ የተሰማሩ አቅራቢዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚሁም መሰረት፡-

1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የቲን እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ ፣ በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድህረ ገፅ ላይ በዕቃ አቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል።

2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ተመላሽ የሚሆን በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (CPO) ከጨረታ ሰነዳችሁ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ አዲስ ልሳን ጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ ለአስር ተከታታይ ቀናት በስራ ሰዓት ት/ቤቱ ግዥ ክፍል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ አንድ ቀን በፊት ለተወዳደሩባቸው ሎቶች በሙሉ ናሙና ማቅረብ ማዘጋጀትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች የምታቀርቡትን ዋጋ ዝርዝር በሰነዱ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በግልፅ የአንዱን እና ጠቅላላ ዋጋ እስከ ቫቱ ሞልታችሁ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በታሸገ ኢንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን 11፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።

6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 4፡30 በት/ቤቱ ቤተ- መፅሐፍት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የበዓል ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡

7. አሸናፊው ተጫራች ዕቃውን ከማስገባቱ በፊት ከት/ቤቱ ጋር ውል በመፈፀም የውል ማስከበሪያ የዕቃውን 10 ፐርሰንት በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (CPO) ማስያዝ እና ያሸነፏቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚ መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበቸዋል፡፡

8. የዘገዩ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡

9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

10. በጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅተው እቃ የሚያቀርቡ ድርጅቶች በደብዳቤ መወዳደር የምትችሉት በምታመርቱት ምርት ላይ ብቻ ይሆናል፡፡

አድራሻ፡- ከአብነት ወደ ሰባተኛ በሚወስደው መንገድ ከብሌን ሆቴል ፊት ለፊት በሚያስገባው አስፋልት ልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 03

ስ.ቁ - 0112 78 85 79

በአ/አ ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ በልደታ ክ/ከተማ ት/ጽ/ቤት

መተባበር አንደኛና መካከለኛ ደ/ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-01
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-01 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Metebaber Elementary School
  • Buyer address: ከአብነት ወደ ሰባተኛ በሚወስደው መንገድ ከብሌን ሆቴል ፊት ለፊት በሚያስገባው አስፋልት ልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 03
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Lessan (Aug 22, 2026)
  • Posted at: 2026-08-22T11:06:26.000Z
← Back to all tenders